Farhan jamal

Farhan jamal Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Farhan jamal, Grocers, Harar.

30/05/2026

Ethiopia’s Election Matters to All of Africa, Says AU Mission Chief Uhuru Kenyatta

Ahead of Ethiopia’s June 1 general election, AU Election Observation Mission head Uhuru Kenyatta emphasized that the vote carries significance far beyond Ethiopia’s borders.

As the host of the African Union headquarters, Ethiopia plays a unique role in Africa’s political landscape. With more than 54 million registered voters, the election is among the largest democratic exercises on the continent.

Kenyatta said the AU’s election observation efforts are aimed at strengthening democracy through African-led solutions, shared learning, and the exchange of best practices among member states.

“Our situations are unique. We do not have to copy and paste from other parts of the world. We can create and replicate best practices across Africa as part of African solutions to African problems,” he said.

The AU mission, composed of observers from 37 African countries, will monitor the electoral process and contribute to efforts to deepen democratic governance across the continent.

Read more: https://pulseofafrica.info/news/3565

30/05/2026

በምርጫው ዕለት ለሀገር ልማት ይበጃል የምንለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል

ሀረር፤ ግንቦት 22/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላላ ምርጫው በሚካሄድበት ዕለት በካርዳችን ለሀገር ልማት ይበጃል የምንለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ የሐረር ከተማ ወጣቶች ገለጹ።

ከከተማው ወጣቶች መካከል ወጣት ዘይኑ አርጋው በህገ መንግስቱ የተሰጠኝን መብት ለመጠቀም የምርጫ ካርድ ወስጃለሁ ብሏል።

በድምጽ መስጫው ቀን ለሀገር እና ለህዝብ ይጠቅማል የምለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቼ ቀኑን በጉጉት እየጠበኩ እገኛለሁ ነው ያለው።

በምርጫ ሲሳተፍ የመጀመርያው በመሆኑ መደሰቱን የገለፀው ወጣት ኑረዲን ውሂብ ለሀገር ልማት ይበጃል የሚለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀቱን ተናግሯል።

በምርጫ ስትሳተፍ የመጀመሪያዋ መሆኑን የገለፀችው ሃናን ዮኒስ የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው ምርጫ ድምፅ ለመስጠት መጓጓቷን ገልጻለች።

ወጣት ሳላህ እስክንድር በበኩሉ በወሰድኩት ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብቴን በመጠቀም ይጠቅመኛል የምለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።

በምርጫው ቀን በምርጫ ጣብያ በመገኘት ድምጹን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል።

#ኢዜአ

30/05/2026
30/05/2026
30/05/2026
30/05/2026

Guyyaa filannoo dhaaba siyaasaa misooma biyyaa fayyadu filachuuf qophiidha

Caamsaa 22/2018 (ENA): Dargaggoonni magaalaa Harar guyyaa filannoo waliigalaa paartii siyaasaa misooma biyyaa fayyadu filachuuf qophii ta’uu ibsaniiru.

Dargaggoota magaalichaa keessaa Zayinuu Argaaw mirga heera mootummaatiin kennameef fayyadamuuf kaardii sagalee isaa itti kennu fudhachuu himeera.

Guyyaa filannoo paartii biyyaa fi ummata fayyadu filachuuf qophii ta'uu fi guyyaa sana hawwii guddaan eeggachaa jiraachuu himeera.
Filannoo kana irratti yeroo jalqabaaf hirmaachuu isaa waan ta’eef gammachuu isaa kan ibse dargaggoo Nuraddiin Muhiib paartii siyaasaa misooma biyyaa fayyadu filachuuf qophii ta’uu dubbateera.

Filannoo kana irratti yeroo jalqabaaf hirmaachuu ishee kan ibsite Hanaan Yoonis filannoo 7ffaa dhufu gaggeeffamu irratti sagalee kennuuf gammachuu guddaa akka qabdu ibsiteetti.
Dargaggoo Saalaah Iskindir gama isaatiin, paartii na fayyada jedhee amanu filachuuf mirga dimokraatawaa qabutti fayyadamuuf qophii ta’uu dubbateera.

Guyyaa filannoo buufata filannootti sagalee isaa kennuuf qophii ta’uus ibseera.

29/05/2026

ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ ማስተዋወቅ የቻሉበትን መድረክ በመፍጠር ተጨባጭ ተግባራት ተከናውነዋል

አዲስ አበባ፤ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ ማስተዋወቅ የቻሉበትን መድረክ በመፍጠር በኩል ተጨባጭ ተግባራት መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ ገለጹ።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት ቀን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫውም 47 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በመገናኛ ብዙኅን አማካኝነት የፖሊሲ አማራጭ ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ በስፋት የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው መድረክ ለምርጫ ክርክሩ በ19 ዙር ያካሄዱ ሲሆን፤ክርክሩም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ዲጂታል አማራጮች ለመራጩ ህዝብ ተደራሽ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ፤በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ ማስተዋወቅ የቻሉበትን መድረክ መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል።

መራጩ ህዝብም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ድምፅ በመስጠት ወኪሎቹን እንዲመርጥ ለማስቻል የምርጫ ቅስቀሳና ክርክር ክህሎት ማዳበሪያ የተግባር ልምምድ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰዋል።

በፖሊሲ ጥናት ምሁራንና ሙያተኞች በመታገዝ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አማራጭ ሃሳብ ልዩነትና ተመሳሳይነት የሚለካበትን መረጃ የመሰብሰብ ሥራ በጥንቃቄ መሰራቱን ተናግረዋል።

የክርክር ሂደቱን ቅርፅ ውጤታማነት ለማስጠበቅ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽ ሙያተኞች የተሳተፉበት ተከታታይ ውይይት በማድረግ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከተለምዷዊ ክርክር ወጣ ያለ ክርክር አካሂደዋል ብለዋል።

የክርክር ሂደቱ ተጋባዥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ገለልተኛ ተቋማት ወኪሎችም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄ የሚያቀርቡበት ዕድል እንደተፈጠረ አንስተዋል።

በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከታዳሚ በሚቀርብላቸው ጥያቄ የህዝብን ፍላጎት በመረዳት መለካት የሚችሉበትን የክርክር ቅርፅ መስጠት እንደተቻለ አብራርተዋል።

የክርክር መሪዎችም ረጅም ጊዜ በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን የሰሩና ገለልተኝነታቸውን ለማረጋገጥ ለፓርቲዎች በመላክ አስተያየት እንዲሰጡበት መደረጉን ጠቅሰዋል።

የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ፖሊሲና የፕሮግራም ዓላማ ለህዝብ በግልፅ በማስተዋወቅ መራጮች በቂ ግንዛቤ የሚያገኙበትን ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል።

በምርጫ ሂደቱ የጥሞና ጊዜም ዜጎች በየቤታቸው ለማን ድምፅ መስጠት እንዳለባቸው ሃሳብ የሚያሰላስሉበትና ፓርቲዎችም ዕጩዎች ያለውን ድባብ የሚከታተሉበት መሆኑን አንስተዋል።

በቀጣይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ተዓማኒ፣ ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው ምርጫም የአፍሪካ ሕብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እና የሀገር ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በታዛቢነት እንደሚታደሙ አስታውቀዋል።

የምርጫ ሂደቱን ለመጎብኘት ጥያቄ ያቀረቡ 16 የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትንም ምላሽ ለመስጠት በሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

#በምርጫብቻ #ኢትዮጵያትመርጣለች #ምርጫ

29/05/2026
29/05/2026

በየትኛውም የምርጫ ጣቢያ 200 ሜትር ርቀት ውስጥ ሆኖ ለመዘገብ ባጅ የተሰጣቸው የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የሚከተሉትን ግዴታዎች ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡-

👉 የሀገሪቱን እና የአካባቢውን ባህልና ልምድ ማክበር፤

👉 በቦርዱ የተሰጠውን የመታወቂያ ባጅ በሚታይ መልኩ በመያዝ መንቀሳቀስ፤

👉 የመራጭ ምዝገባ መረጃዎችን በሰነድ ላይ ሲሰፍሩ ወይም መራጩ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የምርጫ ምልክት ሲያደርግ አለመቅረጽ ወይም ፎቶግራፍ አለማንሣት፤

👉 ግለሰቡ በግልጽ እየተቃወመው መራጮችን እና ሌላ ማንኛውንም ሰው ፎቶ ወይም በተንቀሳቃሽ ምስል አለመቅረጽ እና ቃለ-መጠይቅ አለማድረግ፤

👉 የመራጮች ግላዊ ማንነትን በሚነካ አኳኃን መዝገብ፣ የመራጮችን ምዝገባ መታወቂያ ወይም ማንኛውንም ተመሳሳይ ሰነድ በፊልም አለመቅረጽ፣ ፎቶግራፍ አለማንሳት ወይም ኮፒ አለማድረግ፤

👉 የሕዝብን ሰብዓዊ መብትና መሠረታዊ ነፃነቶች ማክበር፤

👉 የቦርዱን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን፣ የፀጥታና የደኅንነት እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት አካላትን ሚና እና ሥልጣን ማክበር፣

👉 ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስለ ኃላፊነታቸው ምክር ወይም መመሪያ አለመስጠት፣

👉 መራጩ ድምፁን ለማን እንደሰጠ አለመጠየቅ፣

👉 የሕግ ጉዳዮችን በራስ አለመተርጎም እና የምርጫ ሂደትን የሚመለከት ሕጋዊ ያልሆነ መረጃ ወይም መመሪያ አለማስተላለፍ፣

👉 ለድምፅ መስጫ የተከለለ ቦታ ካሜራም ሆነ ሌላ የድምፅ ወይም የምስል መቅጃ መሣሪያ አለመጠቀም፣

👉 ከአድሎና ከወገንተኝነት በፀዳ አኳኋን ተግባራትን ማከናወን ይጠቀሳሉ።

21/09/18

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Farhan jamal posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category