Yohannes Sahle

Yohannes Sahle Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yohannes Sahle, Grocers, Jimma.

22/11/2025
የጌሼ ልደታ ማርያምን ለመደገፍ አካውንት ቁጥር 1000342453973 ንግድ ባንክ እና 1075797750114 ስንቄ ባንክ (ጌሼ ልደታ ማርያም ቤተ ክርስትያን) ድጋፍ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን...
12/10/2025

የጌሼ ልደታ ማርያምን ለመደገፍ አካውንት ቁጥር 1000342453973 ንግድ ባንክ እና 1075797750114 ስንቄ ባንክ (ጌሼ ልደታ ማርያም ቤተ ክርስትያን) ድጋፍ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን በልደታ ስም እናሳስባለን።
Ijaarsa mana amantaa Geeshee Lidetaa Maarihamii deeggaruuf:- lakk account 1000342453973 baankii daldala Itoophiyaa fi 1075797750114 Baankii siinqee (Geeshee Lidetaa Mariyaam bete kiristiyaan ) irratii deeggarsa gochuu kan dandeessan ta'uu maqaa Lidetaa Mariyamiitin isin hubachiisna.
💚💚💚Please share it💚💚💚

Yaa Gooftaa koo akkan si galateeffadhuuf sababni koo baay'eedha. Cubbuu koo fi badii koo osoo hin lakkaa'in Mucaadha waa...
15/09/2025

Yaa Gooftaa koo akkan si galateeffadhuuf sababni koo baay'eedha. Cubbuu koo fi badii koo osoo hin lakkaa'in Mucaadha waan na eebbistef siin galateeffadha.

ጌታ ሆይ አመሰግንህ ዘንድ ምክንያተ ብዙ ነው። ሀጥያተንና ድክመተን ሳትመለከት በልጅ ስለባረክኝ አመሰግሀለው።

ውድ የእግዝአብሔር ቤተሰቦች ሁላችሁም ከፍታችን የካቲት 1እና 2 የመሰረት ድንጋይ የምጣልንትን ቀን ምክንያት በማድረግ ታላቅ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ስለተዘጋጀ በጌሼ ቅ/ልደታ ማርያም ቤተ ክር...
07/02/2025

ውድ የእግዝአብሔር ቤተሰቦች ሁላችሁም ከፍታችን የካቲት 1እና 2 የመሰረት ድንጋይ የምጣልንትን ቀን ምክንያት በማድረግ ታላቅ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ስለተዘጋጀ በጌሼ ቅ/ልደታ ማርያም ቤተ ክርስትያን እንድትገኙ በአክብሮት ተጠርታቹሀል። በአካል መገነት የማትችሉ በአካውንት ቁጥር 1000342453973 ንግድ ባንክ እና 1075797750114 ስንቄ ባንክ (ጌሼ ልደታ ማርያም ቤተ ክርስትያን) ድጋፍ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን በልደታ ስም እናሳስባለን።
Jallatamtoota maatii waaqayyoo hunda keessaniif akkam jirtu nagaa keessani jechaa fuldura keenya gaafa gurrandhala 1fi 2 guyyaa dhagaan bu'uuraa kaa'amu sababa godhachuudhan yaa'iin hafuurawaa qophaa'e jira waan ta'eef akka irratti hirmaatan isin hubachisna. Kannen qaamaan hirmaachuu hin fandeenye lakk account 1000342453973 baankii daldala Itoophiyaa fi 1075797750114 Baankii siinqee (Geeshee Lidetaa Mariyaam bete kiristiyaan ) irratii deeggarsa gochuu kan dandeessan ta'uu maqaa Lidetaa Mariyamiitin isin hubachiisna.

Baga ayyaana Masqalaatin nagaan geessan! እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችው!
27/09/2024

Baga ayyaana Masqalaatin nagaan geessan!
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችው!

++ የአዲስ ዓመት ሥነጹሑፍ !!       ( ይችን ዓመት ተወኝ ! )ከዓመት እስከ አመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ፤በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ፤አለሁ...
10/09/2024

++ የአዲስ ዓመት ሥነጹሑፍ !!
( ይችን ዓመት ተወኝ ! )
ከዓመት እስከ አመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ፤
በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ፤
አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እያጎሳቆልኩኝ፤
አውቃለሁ አምላኬ ፍሬየን ለመልቀም እንዳመላለስኩህ፤
ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅየ ደርቄ ጠበኩህ ፤
ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም፤
ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አልለየኝም ከአለም።
የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ፤
የኔን ክፋት ተወዉ መልአክህን ሰምተህ ይችን ዓመት ተወኝ።

አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር፤
ብዙ ግዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር።
ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይኸ ጊዜ ሰምተኸኝ ነበረ፤
ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮየ አልፎ ባዲስ ተቀየረ ።
ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ፤
እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጢአት መታመሙ።
የቃልህን ውሐ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳትታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ፤
ወደልቤ ሳይሰርግ ህይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈስሶ ቀረ።
ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ፤
በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ።
ብዙ ጥቅስ አገኝሁ ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ፤
ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁንኝ በበደል ተኝቼ ።
ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርጸኝ ተማሪ ብሆንም፤
ይችን ዓመት ተወኝ ተደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም።

እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ፤
ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መአዛ እንዲደርሰኝ።
የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሸከመኝ አትሰልቸኝ አደራ፤
ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት እየሰሩ ስሰራ።
አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ፤
ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ።
ቦታ የሚይዙት ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸው፤
ልክ እንደዘንባባ የተንዠረገገ ተጋድሎ ጽድቃቸው ።
ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው፤
እኔ አይደለሁም ቦታስ የምትይዘው የአንተው እናት ናት፤
ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት፤
ይችን አመት ተወኝ ከስሯ እሆናለሁ ባፈራ ምናልባት፤
ይቺን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት፤
ሺህ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ላንተ ዓመት ኢምንትህ ናት።
ይኸ ዓመት አልፎ ደግሞ ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ፤
እባክህ ጌታየ ይችን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ።

ጸሐፊ - (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
Please share and like this page

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
31/08/2024

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

Address

Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yohannes Sahle posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category