Daraaru qoola

Daraaru qoola Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Daraaru qoola, Grocers, Daraara, Hawassa.

2018 ዋንጫ የኛ ነው
22/01/2026

2018 ዋንጫ የኛ ነው

19/01/2026

ስለ ቀዶ ህክምና የሚያውቀው የህክምና ባለሙያው እና የሚሰራው ታካሚ ነው። ወንድሜ ከአተነፋፈስህ ጭንቀትህን ተረድቻለሁ ነገር ግን ከእግዚአብሄር ጋር ሁሉም ቀላል ሁኖ ያልቃል። አሁንም በድጋሚ ቸሩ መድሀኒአለም ከአንተ ጋር ይሁን🙏🇪🇹

የባዶነት ስንብት! (ለነፂ መታሰቢያ)ትላንት በፈገግታ "ደህና ሁኑ" ብሎ፣ለነገው ተስፋውን በደስታ አውግቶ፤"አምባሳደር" ሆኖ ስራውን ጀምሮ፣እንዴት ይሄዳል ሰው እንዲህ ተቸኩሎ?"ቤተሰብ ጨዋታ...
17/01/2026

የባዶነት ስንብት! (ለነፂ መታሰቢያ)

ትላንት በፈገግታ "ደህና ሁኑ" ብሎ፣
ለነገው ተስፋውን በደስታ አውግቶ፤
"አምባሳደር" ሆኖ ስራውን ጀምሮ፣
እንዴት ይሄዳል ሰው እንዲህ ተቸኩሎ?

"ቤተሰብ ጨዋታ" ቤታችን ገብተህ፣
ፈገግታን አዝንበህ ሀዘን አጥፍተህ፤
የዋህ ነህ ይሉሃል ምስኪን ነህ ሲገልጹህ፣
አላመንም ገና... ሞትህ ነው ብለውኝ ሳዝን ስሰማህ።

ነፂ...

ትላንት በንቃት በሳቅ ደምቀህ ታይተህ፣
ዛሬ ግን ሄደሃል ባዶነትን ትተህ።

ነፍስ በሰላም ትረፍ ነፂ...!

💔

🌴🌴🌴

09/01/2026

1. የውሸት በራስ መተማመን (fake confidence )

◍ብዙ ሰዎች በራስ መተማመን ያላቸውን ሰዎች ይወዳሉ ። ናርሲስቶች ደግም ባዶ ቢሆኑም ውጫዊ ማንነታቸው በከፍተኛ "በራስ መተማመን" የተሞላ ይመስላል።

◍ይህ ጠንካራ ስብዕና ስለሚመስል፣ ትዕቢታቸውን እንደ ጥንካሬ፣ ራስ ወዳድነታቸውን ደግሞ እንደ መሪነት እንድንቆጥር ያደርገናል

2. እኛን መስለው መቅረብ (mirroring)

◍ ናርሲስቶች በጣም ጎበዝ ተዋናዮች ናቸው። የእኛን ፍላጎት እምነት እና የህይወት እይታ በማጥናት ልክ እንደ እኛ መሆንን ይጀምራሉ።

◍እኛ የምንወደውን ይወዳሉ፣ እኛ የምንጠላውን ይጠላሉ በእዚህም ምክንያት "soulmate አገኘሁ" ብለን እንድናምን ያደርጉናል።

3.Love Bombing" (የፍቅር ናዳ)

◍ግኑኙነቱ በተጀመረበት ሰሞን ናርሲሲስቶች ከመጠን በላይ የሆነ ፍቅር፣ ትኩረት፣ ስጦታ እና ምስጋና ያዘንቡብናል።

◍ይህ ሲሆን እኛ "የህይወቴን ፍቅር አገኘሁ" ብለን እናስባለን እንጂ እየተወኑብን እንደሆነ አንጠራጠርም ።
ይህ ከመጠን ያለፈ የፍቅር ናዳ አይናችንን ስለሚጋርደው ቀይ መብራቶችን (Red flags) እንዳናይ ያደረገናል።

4.ለውጡ የሚመጣው ቀስ በቀስ ነው

◍ ናርሲሲስቶች እውነተኛ ማንነታቸውን ወዲያው አያወጡም መጀመሪያ ላይ በጣም ጥሩ ሆነው ይቆዩና፣ ለእነሱ በፍቅር እንደወደቅን ሲያዩ ..ቀስ በቀስ መርዛማ ባህሪያቸውን ማሳየት ይጀምራሉ ለውጡ በሂደት ስለሚመጣ ፣ "ተለወጠብኝ/ተለወጠችብኝ ብለን እናስብ ይሆናል እንጂ "መጀመሪያውኑ ማንነቱን/ቷ ይህ ነበር" ብሎ ለማሰብ እንቸገራለን ።

5. የእኛ ቅነንነት (projection)

◍ አብዛኛው ሰው ቅን ስለሆነ ፣ሌሎችም እንደ እሱ ቅን ናቸው
ብሎ ያስባል 🤷‍♀️

ቅድስት ✍️

18/12/2025

ውድ ወንድሜ Abinet kebede ለካ ከጥንካሬክ ጀርባ ትልቅ ህመም አለ አጠገብክ ሆኜ ያልታየኝ ከደግነትክ ጀርባ ትልቅ ስቃይ አለ ካጠገብክ ሆኜ ያልታየኝ ግን አንድ ነገር አምናለው እግዚአብሄር የልቤን አይቶ ካለብክ ህመም እንደሚፈውስክ ይሄ ለታሪክ ይቀመጥልኝ ። ሁላችንም ፀሎት እናርግለት ለወንድማችን

22/12/2024

¶የማይፈታው የዉሃ ጥም

ድምፅ ለዉሃ ልማት ጽህፈት ቤት እንዲሁም ጉዳዩ ለሚመለከተዉ ሁሉ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዉሃ ሽፋን 60% ደርሷል ተብሎ ሪፖርት በሚደረግበት ምድር በዳራራ ወረዳና አከባቢ ማህበረሰብ ዉስጥ የዉሃ ችግር የማይፈታ እንቆቅልሽ ሆኖ ሰንብቷል። ለምሳሌ ኦልካ ዳንሸ፣ ዳራራ ሻኤ፣ ዲላ አርከ፣ ዲላ አርፈ፣ ዳንሽ ስሬ የሚባሉ አከባቢወች ችግሩ የሚታይበት ናቸው። የነዚህ የመሬት አቀማመጥ መካከለኛ ቆላማ ቢሆንም አከባቢዉን አቋርጦ የሚያልፈዉ አዋዳ_ቦርቻ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ችግሩን መፍታት ቢችልም ትኩረት በማጣትና ባለመስጠት ህዝብ ከፍተኛ በዉሃ ችግር ላይ ወድቆ ይገኛል። በዚህ ወቅት ህዝቡ አንዱን ጄሪካን ዉሃ 20_30 ብር በመግዛት ላይ ይገኛል። ይሄን ችግር እንደችግር በመረዳት ተገቢዉን እልባት እንዲሰጠዉ በህዝቡ ጎን በመሆን ድምፄን አሰማለሁ።

Address

Daraara
Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daraaru qoola posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category