Remedan yusuf

Remedan yusuf Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Remedan yusuf, Grocers, Harar.

15/05/2025

የጤና ባለሞያዎች በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ጫና ሳይዘናጉ ስራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ በመሆኑ የጤና ሚኒስቴር ምስጋና አቀረበ

የጤና ባለሞያዎች በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ጫና ሳይዘናጉ በገቡት ሙያዊ ቃልኪዳን መሰረት ማህበረሰቡን እያገለገሉ በመሆናቸው የጤና ሚኒስቴር ምስጋና አቅርቧል።

ሚኒስቴሩ መቼምና በምንም ሁኔታ መቋረጥ ከሌለባቸው ማኅበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የጤና አገልግሎት መሆኑንም በአጽንኦት ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በወቅታዊ የጤና አገልግሎት ዙሪያ የሰጠው መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የጤና ሚኒስቴር ለማኅበረሰባችን ጥራቱን የጠበቀ እና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመቅረጽ የኅብረተሰቡን ባለቤትነት ባረጋገጠ መልኩ ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑ የዐደባባይ ሐቅ ነው።

ምክንያቱም መቼምና በምንም ሁኔታ መቋረጥ ከሌለባቸው ማኅበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የጤና አገልግሎት በመሆኑ፤ ስለዚህም ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት በመላ ሀገራችን በሚገኙ የጤና ተቋማት እንደ ወትሮው ሁሉ መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ለማኅበረሰባችን ያለምንም መቆራረጥና መስተጓጎል እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡

ይሄንን የተረዳው የጤና ባለሞያ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ጫና ሳይገፋ የገባውን የሞያ ቃል ኪዳን እና መሐላ ጠብቆ ማኅበረሰቡን እያገለገለ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል፡፡

ይሁን እንጂ በጥቂት የማስተማሪያ የጤና ኮሌጆች/ተቋማት በመደበኛ የሥራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የተወሰኑ ባለሞያዎች እንዳሉ መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ ከእነዚህ የጤና ባለሞያዎች መካከል ብዙዎቹ በሐሰተኛ መረጃ የተወናበዱ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ ጥፋትን ዓላማቸው ያደረጉ ናቸው።

ድርጊቱ የራስን ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወገን እና መላውን ማኅበረሰብ ከመጉዳት ባለፈ ከሞያ ሥነ ምግባር፣ ከሰብአዊነት አኳያ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

ከሕግ አኳያም የጤና ሞያ የሥራ ማቆም አድማ ከማይደረጉባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑ በግልጽ ተደንግጓል። የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ እንኳን ቢኖራቸው በሥራ ገበታቸው ተገኝተው መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ ጉዳያቸውን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በመሆኑም እነዚህ የጤና ባለሞያዎች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው ማኅበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ በየተቋማቸው ጥሪ ተደርጓል።

መንግሥት የጤና ባለሞያውን ዘላቂ ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ለመስጠት ቀደም ብሎ የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1362 /2017 አጸድቆ ደንብና መመሪያዎችን በማውጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል።

በጎ ኅሊና ያላቸው የጤና ባለሞያዎች ይህንን በመገንዘብ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ያቀርባል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኅብረተሰቡ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በሚሠራጩ የሐሰት መረጃዎች ሳይረበሽ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት በተለመደው መልኩ በጤና ተቋማት ማግኘት እንደሚችል እናሳውቃለን ።

መንግሥት በሆደ ሰፊነት ችግሩን ለመፍታት ያሳየውን ትዕግሥት ወደጎን በመተው በሥራ ገበታቸው ላይ ባልተገኙ እንዲሁም በጤና ተቋሙም ሆነ ከጤና ተቋሙ ውጭ ሆነው ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩት ላይ አስፈላጊ የሆነ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ቀድመን እናሳውቃለን፡፡

የጤና ሚኒስቴር

14/05/2025
14/05/2025
14/05/2025
14/05/2025

በበጀት አመቱ የጀመርናቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘለት የጊዜ ገደብ እና ጥራት እንዲጠናቀቅ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እናደርጋለን።

ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

13/05/2025

"የጎርጎራ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የትናንት ታሪክ፣ የዛሬን ዕድልና የነገ ሕልም ደምሮ የያዘ ነው።" –
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በጎርጎራ ፕሮጀክት ጉብኝት ወቅት ያስተላለፉት መልዕክት
መጋቢት 25/2015 ዓ.ም

prosperity

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Remedan yusuf posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category