Usman Abdi

Usman Abdi Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Usman Abdi, Grocers, Harar.

03/06/2026
03/06/2026

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማጎልበት የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው - የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የቡድኑን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያ ግምገማ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ውቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሠራውን ሥራ እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።

አጠቃላይ የምርጫው ሂደትም የኢትዮጵያን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች ማዕቀፍን በተከተለ መልኩ መካሄዱን በግምገማው ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።

ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ የነበረው ሂደት አበረታች እንደነበር የገለጹት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የአፍሪካ ኅብረት ከምርጫው ዋዜማ አንሥቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ በተመለከተም ሕዝቡ እንዴት መምረጥ እንዳለበት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉን እና በምርጫው ዕለት የነበረው የተቀናጀ መናበብ ለመራጮች ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን አስረድተዋል።

በምርጫው ሂደት ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ በተለይም ለወጣቶች የፈጠረው ዕድል ከፍተኛ መሆኑን የታዛቢ ቡድኑ መሪ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

የድምፅ መስጫ ሰዓት መራዘሙ ለመራጮች ተጨማሪ ዕድል መፍጠሩን፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ቅድሚያ መሰጠቱ የዜጎችን ተሳትፎ በእጅጉ ማነቃቃቱንም ጠቁመዋል።

በመላው ኢትዮጵያ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና የፀጥታ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጥሩ ሁኔታ መወጣታቸውን፣ የመገናኛ ብዙኃንም በተመሳሳይ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ሥራቸውን ማከናወናቸውን አድንቀዋል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው ያሳየው ተሳትፎ እና ትልቁን ኃላፊነቱን በጀግንነት መወጣቱ እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።

03/06/2026

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ መርጣለች!

ሀገራችን ባከናወነችው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ረዣዥም የመራጮች ሰልፍ መስተዋሉ፣ ዜጎች በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ስለመሆናቸው ጉልህ ማሳያ ነው።

የዕድሜ መግፋት ፣ የጤና ሁኔታ መታወክ፣ አራስነት፣ ከቤት መቆየትን የግድ ያለው አሰገዳጅ ክስተት ሳይበግራቸው ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው ይበጀኛል ያሉትን መርጠዋል።

አንድ ድምፅ ዋጋ እንዳለው በመረዳት ከሌሊት እስከ ሌሊት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

በምርጫው ዕለት የታዩ ረዣዥም የመራጮች ሰልፎች የሕዝብ የፖለቲካ ፍላጎት እና የዴሞክራሲ ተሳትፎ መጉላትን የሚያሳዩ ናቸው።

03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

02/06/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ድምጹን በመስጠት ለዲሞክራሲዊ ግንባታ አስተዋጽዎ አድርጓል የሀረሪ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን

የሀረሪ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን በትላንትናው እለት የተካሄደውን 7ኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በሀረሪ ክልል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የክልሉ ፌዴሬሽን አመራሮች ጨምሮ 250 የሚጠጉ ወጣቶች በምርጫ ታዛቢነት ተሳትፈዋል።

የክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወጣት ረስተም ኡመር እንደገለጹት ፌዴሬሽኑ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የምልከታ ስራዎችን አከናውኗል።

በዚህም ምርጫው ፍፁም ሰላማዊና ነጻ ሆኖ መጠናቀቁን ተለያዩ አካላት የተሰበሰቡ መረጃዎች ያረጋገጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በተገኘው መረጃ መሰረትም ዜጎች የወደዱትንና የፈለጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ያለ ምንም ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ ሳይኖር በነጻነት መምረጥ መቻላቸውን አረጋግጠናል ብለዋል።

የክልሉ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ፣ ይበጀኛል ያለውን ፓርቲ በሰለጠነ መልኩ በድምጹ በመምረጥ ለዲሞክራሲ ግንባታ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ወጣት ረስተም ኡመር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የምርጫው ሂደት በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ፌዴሬሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።

02/06/2026

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Usman Abdi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category