Abbaa Biyya's Post

Abbaa Biyya's Post Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abbaa Biyya's Post, Grocers, tesfabek37@gmail. com, Harar.

27/05/2023

የትምህርት ዕድል ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች

አምስት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የነጻ ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ሊያደርጉ ነው።

ሊሴ ገ/ማርያም ፣ ጣሊያን ት/ቤት፣ ቤንግሀም አካዳሚ፣ ሳንፎርድአለም አቀፍ ት/ቤትና አሜሪካን ማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች የመክፈል አቅም የሌላቸው ተማረዎችን ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ከማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉት የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች 10 በመቶ ተማሪዎችን ተቀብለው እንዲያስተምሩ ከስምምነት ደርሰዋል ብለዋል።

27/05/2023

የአሁኑ ጥቃት ከከዚህ ቀደሙ ከበድ ያለ ነበር "

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ፤ በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " በሰጠው ቃል ፤ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና 3 የአካባቢው ነዋሪዎች መገደላቸውን አረጋግጧል።

ፋብሪካው በተፈጸመበት በዚሁ ጥቃት እና ዘረፋ ምክንያት ስራ ማቋሙም ገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 12 ቀን 2015 መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ፤ ፋብሪካው ባለፈው 2014 ዓ.ም እና በዚህ ዓመት ተመሳሳይ ጥቃቶችን ቢያስተናግድም፤ የአሁኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት " ከበድ ያለ " እንደሆነ አመልክቷል።

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ እና በስሩ ያለው የሸንኮራ አገዳ እርሻ፤ በአጠቃላይ በ67 ሺህ ሄክታር ይዞታ ላይ ያረፈ ነው።

የቀደሙት ጥቃቶች ይበልጥኑ ኢላማ የሚያደርጉት የፋብሪካው እርሻ ላይ እንደነበር የገለፀው ግሩፑ ታጣቂዎቹ የአገዳ እና የእርሻ ማሽነሪዎችን የማቃጠል ድርጊት ይፈጽሙ እንደነበር አስታውሷል።

የአሁኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሚለየው ታጣቂዎቹ ወደ ፋብሪካ ጭምር በመግባት ጥቃቶቹን በመፈጸማቸው እንደሆነ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ጥቃቱን እንዲመረምር ያቋቋመው ግብረ ኃይል ፤ በጥቃቱ 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ ማረጋገጡን ኃላፊው አስታውቀዋል።

ሰኞ ዕለት ወደ አካባቢው የተሰማራው ይኸው ግብረ ኃይል፤ እንደ ልብ ተዘዋውሮ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ የደረሱ ሌሎች ጉዳቶችን እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ እንዳልቻለ ተነግሯል።

ሆኖም ግብረ ኃይሉ እስካሁን ባሰባሰበው መረጃ ፦

- በታጣቂዎች ከተገደሉት ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች አሉ።

- ውድመት እና ዘረፋ መፈፀሙ ተረጋግጧል።

- ቢሮዎች ወድመዋል። ፋብሪካው ውስጥ ያለ መቆጣጠሪያ ኮምፒውተር ተሰብሯል።

- የእርሻ ማሽነሪዎች፣ ትራክተሮች፣ አገዳ ወደ ፋብሪካው የሚያመላልሱ የተለያዩ [ተሽከርካሪዎች] ሙሉ ወድመዋል፤ የተጎዱም አሉ።

- የፋይናንስ ሰነዶች ወድመዋል።

- ከተዘረፉት ንብረቶች ውስጥ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ኮምፒውተሮች እና ፕሪንተሮች ይገኙበታል።

- ታጣቂዎቹ በፋብሪካው መጋዘን ውስጥ የተከማቹ ስኳር እና የአፈር ማዳበሪያ ዘርፈው ወስደዋል።

አጠቃላይ ጉዳቱን በዝርዝር ለማወቅ የሚያስችለው ምርመራ ገና አለመጠናቀቁ ተገልጿል።

ጥቃቱን ማነው የፈፀመው ?

ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች ማንነት በተመለከተ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የህዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ክፍል ኃላፊ አቶ ረታ ደመቀ ፤ በእርሳቸውን የስራ ኃላፊነት የታጣቂዎችን ማንነት ለይተው መናገር እንደማይችሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከቅዳሜው ጥቃት በኋላ ፋብሪካው ወደሚገኝበት አካባቢ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲገቡ በመደረጋቸው በአሁኑ ወቅት በስፍራው " የተሻለ ሁኔታ "መኖሩን ኃላፊው አስረድተዋል።

ሆኖም አሁንም ቢሆን " በእርሻ መንደሮች አካባቢ ታጣቂዎች አሉ " የሚል ስጋት በሰራተኞች ዘንድ እንዳለ አመልክተዋል።

Address

Tesfabek37@gmail. Com
Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abbaa Biyya's Post posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category