03/11/2025
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወደ ብዝኃ ዘርፍ የቀየረው የመንግስት አቅጣጫ
👉 2017 ዓ.ም ይቻላል ተብለው ያልታሰቡ ጉዳዮች የተከናወኑበት እና የስኬት ዓመት ነበር፣
👉 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የግብርና መር ፖሊሲ ይከተል ነበር፤ ይህንን ወደ ብዝኃ ዘርፍ ቀይረን በእጅጉ ውጤታማ ሆነናል፣
👉 በአንድ ሴክተር ላይ ተንተርሶ መስራት ከድህነት አረንቋ ስለማያወጣን ብዝኃ ዘርፍን በመከተላችን ውጤት አምጥተናል፣
👉 ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ሴክተሮች ብዝኃ ዘርፍ ሆነው ቢመሩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሊያሻሽሉ ይችላሉ የሚል እምነት ነበረን፣
👉 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስር ነቀል ውጤት እንዲያመጣ በብዝኃ ዘርፍ መንግስት ከአጋር ድርጅቶች ጋር ተሳስሮ የኢትዮጵያ ዕድገት ለማፋጠን ይሰራል፣
👉 መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ የኢትዮጵያን ልማት በየፈርጁ ማፋጠን አለበት፤ በመንግስት ደረጃ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠለት ከለውጡ በኋላ ነው፣
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከሰጡት ማብራሪያ(ኤፍ ኤም ሲ)