Ameya City Prosperity Party Branch Office

Website

Ameya City Prosperity Party Branch Office ራዕያችን በግልፀኝነት ታማኝና ፈጣን መረጃ ለህዝብ በማድረስ የሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ ነዉ።

የፀጥታ አካላት በከተማዋ ሰላምና ደህንነት ጥበቃ ላይ የሚያሳዩት ቁርጠኝነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ...
18/11/2026

የፀጥታ አካላት በከተማዋ ሰላምና ደህንነት ጥበቃ ላይ የሚያሳዩት ቁርጠኝነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የክንውን አፈፃፀም እና በ100 ቀን ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
‎
በዚህም በወንጀል መከላከል፣ በትራፊክ ደህንነት፣ በታክቲክ ምርመራ፣ በወንጀል መረጃ እና በሰው ሀብት አስተዳደር ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች በዝርዝር ቀርበዋል።
‎
በመድረኩ የአመያ ከተማ አስተዳደር ፍትህና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ኡቴ እንደገለጹት፤ የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረጉ ቅንጅታዊ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አክለውም፤ ፖሊስ ከህዝብና ከመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ ተቀብለው ለህብረተሰቡ በቀንም ሆነ በማታ ደከመኝ ሰለቸኝ ሣይል ሀይማኖትና ብሔርን ሣይለይ ለሁሉም እኩል የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑና ማህበረሰብም ለፖሊስ ስራ ስኬት ከጎናችሁ መሆን እንዳለበት ጥሪ አስተላልፏል።

ትክክለኛ የፍትህ ስርዓት እንዲሰፍን ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራትና የመረጃ ልውውጥ ልኖር ይገባል ብለዋል አቶ አየለ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሙስና ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኮማንደር መኮንን ምታ በበኩላቸው፤ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በየደረጃው በሚገኙ የፀጥታ መዋቅሮች መካከል ያለው የመረጃ ቅብብሎሽ ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።
‎
የፀጥታ ተግባራትን በቅንጅት መምራት ለከተማው ዘላቂ ሰላም ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረው በተቀናጀና በተደራጀ የፀጥታ መዋቅር ስምሪት የከተማውን አልፎም የህዝባችንን ሰላም ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆን እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል።

የአመያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር መንክሮ ታመነ እንዳሉት፤ ባለፉት ግዚያት በከተማው የህዝብን ሰላም ለመጠበቅ በርካታ ተግባራት ስለመከናወኑን የገለጹት ሲሆን የታዩ ለውጦችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሁላችንም ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በተለይም ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት በመከላከል፣ በወንጀል መረጃ ልውውጥ፣ በቅድመ ማስጠንቀቂያና በፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ላይ በጋራ በቀጣይ በከተማው ልዩ ቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
‎
በውይይቱም የተገኙ ጠንካራ ጎኖችን የበለጠ ማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን ማረምና በመጪው 100 ቀን የሥራ ዕቅድ ላይ የጋራ መግባባት የተደረሰ ሲሆን፣ ዕቅዱ በተቀመጡ የሥራ አቅጣጫዎች፣ በግልጽ የተግባር ኃላፊነቶችና በቅንጅት አሰራር ላይ ተመስርቶ እንዲፈፀም ተግባብተዋል።

ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ክህሎት ግብር ከፋዮች የድርጅታቸውን ገቢ እና ወጪ በአግባቡ እንዲይዙ በእጅጉ እንደሚያግዝ ተገለጸ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ አመያ ከተማ አስተዳደር ገቢ ዩኒት ጋራ በመተባ...
18/11/2026

የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ክህሎት ግብር ከፋዮች የድርጅታቸውን ገቢ እና ወጪ በአግባቡ እንዲይዙ በእጅጉ እንደሚያግዝ ተገለጸ

የዞኑ ገቢዎች መምሪያ አመያ ከተማ አስተዳደር ገቢ ዩኒት ጋራ በመተባበር በከተማው ለደረጃ”ሀ” ግብር ከፋዮች በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ዙሪያ የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል።

በመድረኩ የአመያ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የከንቲባ ተወካይ አቶ ታምራት ጫንያለው እንደተናገሩት፤ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ክህሎት ግብር ከፋዮች የድርጅታቸውን ገቢ እና ወጪ በአግባቡ እንዲይዙ በእጅጉ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

ግብር ከፋዮቹ ግብዓቶችን በአግባቡ በመምራትና በመቆጣጠር ውጤታማ ለመሆንና የድርጅታቸውን ህልውና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ከሚያስችላቸው መሠረታዊና ወሳኝ መሣሪያዎች አንዱ የሂሣብ መዝገብ አያያዝ ሥርዓት ነው ብለዋል።

ግብር ከፋዮች ለህግ ተገዢ እንዳይሆኑ ከሚያደርጋቸው ምክንያቶች ውስጥ ቀዳሚዎቹ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው የግንዛቤ መሆኑን ገልፀው ክፍተቶቹን በስልጠና መሙላት አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለደረጃ”ሀ” ግብር ከፋዮች በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ዙሪያ የክህሎት ስልጠና ስነድ ያቀረቡት የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ገለታ ጋንበሮ እንደጠቆሙት፤ ድርጅቱን ከስኬት ለማድረስ ከማቀድ ጀምሮ ለንግድ ስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችና ጥሬ ሀብቶች የማሰባሰብና የማደራጀት፣ የመምራትና የመቆጣጠር፤ ስራው የደረሰበትን ደረጃና ያገጠሙ ችግሮች በየጊዜው እየገመገመ በመለየት የመፍትሔ እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡

ግብር ከፋዮች የድርጅታቸውን ገቢ እና ወጪ በትክክል እንዲይዙና በሂሳብ ዘመኑ ማብቂያ ላይ ድርጅታቸው አትራፊ ወይም አክሳሪ መሆኑን በቀላሉ እንዲያውቁ ያስችላቸዋል ብሏል።

የግብር እና የታክስ ግዴታቸውን በተመለከተ ተዓማኒነትና ተቀባይነት ያለው መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል የመረጃ አደረጃጀትና አያያዝ ስለሚኖራቸው ከግብር አስገቢው መስሪያ ቤት ጋር መልካም የስራ ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ ከግብር ከፋዮች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ስልጠናውን በሰጡ ባለሙያዎች ጨምሮ የከተማው ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ታምራት ጫንያለው የተቋሙ ማናጅመንት በኩል ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸበኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊና ...
17/11/2026

የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊና መደበኛ የፓርቲና የመንግሥት የልማት ስራዎችና
የንቅናቄ ተግባራት አፈፃፀም ዙሪያ የከተማው ፑል አመራር አካላት በተገኙበት የግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

በዚህም የቀበሌ አፈፃፀም በምን ደረጃ ላይ እንዳለና የፓርቲ መዋጮ አፈፃፀም፣ የሰባዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም የመቻል፣ ዲጅታል ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ፣ የትምህርት ተግባራት ፣ የበጋ መስኖ፣ የመከላከያ ምልመላን ጨምሮ ሌሎች በንቅናቄ የተመሩ ተግባራት አፈፃፀም ተገምግመው የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ለአመራር ግብረ -መልስ ተሰጥቷል።

በመድረኩ የከተማው የመንግስት ረ/ተጠሪና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኮንን እንዳሉት፤ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

አያይዘውም አቶ ተስፋዬ፤ አመራሩ የመደበኛና የንቅናቄ ተግባራትን አቀናጅቶ መስራት ለውጤታማ አፈፃፀም ያለው ጠቀሜታ ወሳኝ እንደሆነ ገልፀው የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ድክመቶችን በማሻሻል አቅጣጫ እያስቀመጠ ህብረተሰብን የሚያሻግር ተግባር ሊያከናዉን እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በዋናነት ከተረጅነት አስተሳብ ፣ የመከላከያ ምልመላ፣ የትምህርት ተግባራት፣ ድጃታል መታወቂ፣ የበጋ መስኖ፣ የፓርቲ መዋጮ ስራዎችን አመራሩ በጊዜ የለኝም መንፈስ በልዩ ቁርጠኝነት መሠረት እንዳለበት ያሳሰቡት ስሆን ለሎችንም ተግባራት በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ መምራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የመንግስት ረ/ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ገብሬ በበኩላቸው፤ የፓርቲና የመንግሥት ስራዎች አፈጻጸም አኳያ አመራሩ ለውጤታማነት በከፍተኛ ቁርጠኝነት መሰራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ወቅታዊ የፓርቲና የመንግስት እንዲሁም በተለየ ሁኔታ የህብረተሰብ ተሳትፎን በማጠናከር የህብረተሰቡን ልማት ጥያቄ ለመመለስ እና በተቀመጠለትጊዜ ለማጠናቀቅና የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አመራሮች ተግባራትን ቆጥሮ የመምራት ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው ብለዋል።

በየደረጃው የታቀዱ የ90 ቀናት ዕቅዶች ግቡን ለማሳካት እየተሰራ እንደሆነ በየጊዜው እየተገመገመ ልመራ እንደሚያስፈልግ የገለፁት ሲሆን ተልዕኮዎችን ቆጥሮ በመውሰድ፣ ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት ልሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም እስከ አሁን በተከናወኑ ተግባራቶች በጥንካሬ የተገመገሙትን በማፅናት እና በጉድለት በተነሱ እና ቀጣይ እርምት ተወስዶ የሚከናወኑ ተግባራቶችን በጋራ በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በመግባባት ላይ ተደርሶዋል።

ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮችን በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት ይሰራል - አፈ -ጉባኤ አቶ ተስፋዬ ገዳዎበኮንታ ዞን የአመያ ...
17/11/2026

የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮችን በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት ይሰራል - አፈ -ጉባኤ አቶ ተስፋዬ ገዳዎ

በኮንታ ዞን የአመያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የተመረጡ የአስፈፃሚ ተቋማት የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ የተገኙት የአመያ ከተማ አስተዳደር ጊ/ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ተስፋዬ ገዳዎ እንደገለጹት፤ የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮችን በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋሌ።

አያይዘውም፤ ከህዝቡ ተጠቃሚነት አኳያ የህዝብን አስተያየት በመውሰድ ለቀጣይ መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት ለመስራት የታሰበ መድረክ መሆኑን ያብራሩት ሲሆን ተቋማት የህዝብ አገልጋይ እንደመሆናቸው የተሰሩ ተግባራት ለህዝብ በሪፖርት መቅረቡና አስተያየት መሰጠቱ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በታቀደው ዕቅድ መሰረት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አፈ ጉባኤው ከዚህ ሪፖርት ግምገማ መነሻ የአፈጻጸም ደካማ ጎኖችን በመቀበል ለቀጣይ በትጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአመያ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ተወካይ አቶ ታምራት ጫንያለው በበኩላቸው፤ በአመያ ከተማ በርካታ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው ከህብረተሰቡ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተዳዳር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ እየመለሱና በቀሪ የህዝብ ጥያቄዎች ላይ በትኩረት የሚሰሩ መሆናቸውን በአጽንኦት ገልጸዋል።

አክለውም አቶ ታምራት፤ ከዝህ አንጻር ተግባሩን ለማሳካት ከፍተኛና ሁሉ አቀፍ ርብርብ በማድረግ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ከአመራርና ከባለሙያዎች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሰው በየግዜው የታዩ ለውጦች እየተገመገመ የመጣ ቢሆንም አሁንም ከፍተኛ ክፍተቶች መኖራቸውን አስረድተዋል።

የከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ረ/የመንግሥት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ገብሬ እንደተናገሩት፤የተኛው ለልማት ስራዎች ላይ የህብረተሰብ ተሳትፎ ውሳኝ በመሆኑ በቀጣይ የህዝብ ተሳትፎን በማጠናከር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በጋራ ተቀናጅተን መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግሯል።

በከተማው ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ሎት ጽ/ቤት በኩል የ1ኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር መንግሥቱ መኩሪያ ያቀረቡት ሲሆን በበኩላቸው የአመያ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ገለጸዋል።

አካባቢውን ለስራ እና ለመኖሪያ ምቹ ከማድረግ አንጻር የአካባቢዉን ብክለት መከላከል ተገቢነት እንዳለው ታምኖበት ከተሞች ፅዱ፣ ውብ፣ አረንጓዴና ማራኪ ከስጋት ነፃ የሆኑ እንዲሁም በደን የተሸፈኑ ለማድረግ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እና ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተሰራው ስራ የታሰበውን ያህል ባይሆንም ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል።

የከተማው ኢንተርፕራይዝ ዩኒት አስተባባሪ አቶ መለሰ መኩሪያ በ1ኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ላይ የተዘጋጀ ሰነድ ባቀረቡት ወቅት እንደገለጹት፤ በከተማው ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሲሆን የስራ ስምሪት በከተማ እና በገጠር በ1ኛ ሩብ ዓመት 694 ታቅዶ 663 ተግባራዊ ስለሆኑን ገልጸው በቋሚ እና በጊዚያዊ የስራ ዕድል በ1ኛ ሩብ ዓመት 391 ታቅዶ 142 የሰራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተናግሯል።
‎በውይይቱ የተገኙት ተሳታፊዎች እንዳነሱት በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የተሰሩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀው በቀጣይም የሚታዩ ጉድለቶችን በማረም ቀልጣፋና ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል።
‎
‎በቀረበው የ1ኛ ሩብ ዓመት የተመረጡ ተቋማት ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ድከመቶችን በማረም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ገንቢ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
‎
‎ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በዘመቻ መልክ የሚከናወኑ ተግባራትን በተሳካ ሁኔታ ለማስፈጸም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት፣ ትብብርና ትኩረት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት የፖሊ...
17/11/2026

በዘመቻ መልክ የሚከናወኑ ተግባራትን በተሳካ ሁኔታ ለማስፈጸም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት፣ ትብብርና ትኩረት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ንቅናቄ እና የኢቮላ ቫይረስ በሽታ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የአመያ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የመንግሥት ረ/ተጠሪና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኮንን እንደተናገሩት፤ በዘመቻ መልክ የሚከናወኑ ተግባራትን በተሳካ ሁኔታ ለማስፈጸም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት፣ ትብብርና ትኩረት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማው የሚታዩ የጤና ክፍተቶችን ለመሙላትና ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

አያይዘውም አቶ ተስፋዬ፤ በዋናነት ከፖሊዮ ክትባቱ በከተማው በተሳካ ሆኔታ ለማከናወን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሀላፊነት መንፍስ መስራት እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት።

የከተማው የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ታምሩ ሳሙኤል በበኩላቸው፤ በአሁኑ ወቅት የሚታዩ በርካታ ተላላፊ በሽታዎች መንስኤያቸው የግልና የአካባቢ ንጽህና ጉድለት መሆኑን በማንሳት፣ ጤና ለሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ ሁሉም የየድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

አክለውም፤ በዋናነት የክትባት ዘመቻው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ ያሳሰቡት ሲሆን ለሁሉም ህፃናት ክትባቱ ተደራሽ እንዲሆን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ ለተሳታፊዎች የተዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ያቀረቡት የጤና ዩኒት አስተባባሪ አቶ ማሞ መሰለ፤ በዘመቻው ዙሪያ ለተሳታፊዎች ሰፊ ማብራሪያና ግንዛቤ የሰጡ ሲሆን፣ ዘመቻውን ስኬታማ ለማድረግና የአፈጻጸሙን ጥራት ለማሳደግ ሁሉም በባለቤትነት መስራት እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተናግሯል።

የኢቮላ ቫይረስ በሽታ በኢቦላ ቫይረስ አማካይነት የሚመጣ የደም መፍሰስ የሚያስከትል አልፎ አልፎ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት አደገኛ በሽታ መሆኑን ያብራሩት ሲሆን የበሽታው ምልክት በድንገት በሚከሰቱ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስምታት ድካም ስሜት እንደሚጀምርና ህብረተሰቡን በዝህ በሽታ ተጋላጭ እንዳይሆኑ መስራት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

አቶ ማሞ አያይዘውም፤ በከተማው የሚጀመረው የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በተያዘለት ጊዜ ውስጥ በውጤታማነት እንዲጠናቀቅና ሁሉም ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የክትባቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ርብርብና ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
‎
ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

ስራ አስኪያጅ በራሱ ቀበሌ ሁሉንም ተግባራትን ጠርንፎ ሳያንጠባጥብ ሊመራ ይገባል - አቶ ተስፋዬ መኮንን ስራ አስኪያጅ በራሱ ቀበሌ ሁሉንም ዘርፍ ጠርንፎ ሳያንጠባጥብ ሊመራ ይገባል አሉ ረ/የ...
15/11/2026

ስራ አስኪያጅ በራሱ ቀበሌ ሁሉንም ተግባራትን ጠርንፎ ሳያንጠባጥብ ሊመራ ይገባል - አቶ ተስፋዬ መኮንን

ስራ አስኪያጅ በራሱ ቀበሌ ሁሉንም ዘርፍ ጠርንፎ ሳያንጠባጥብ ሊመራ ይገባል አሉ ረ/የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኮንን።

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከቀበሌ ስራ አስኪያጆች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ረ/የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኮንን እንደገለጹት፤ የፓርቲና የመንግሥት ተልዕኮዎችን በመወጣት በቀበሌ ደረጃ የሕዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ስራ አስኪያጆች ከምን ጊዜው በላይ በቁርጠኝነት መመለስ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በቀበሌ ደረጃ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መኖሩን የገለፁት ስሆን የቀበሌ ስራ አስኪያጆች በቀበሌ ስር ነቀለ ለውጥ ለማምጣት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አያይዘውም፤ በየቀበሊያቱ ለሚወድቁ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት ቅድሚያ ተጠያቂ የቀበሌ ስራ አስኪያጅ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በቀበሌ ላይ የሚከናወኑ የትኛውም ተግባራት ትኩረት ተሰጥቶ ሊመራ ይገባል ብለዋል።

በቀበሌ ላይ ያለው የመንግስትና የፓርቲ አደረጃጀት ውጤታማ ነው አይደለም የሚለውን ነገር ሀላፊነት ወስደው መሄድ ያስፈልጋል ያሉት ረ/የመንግስት ተጠሪው ስራ አስኪያጆችን በየቀበሌው ማጠናከር የተጀመረውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።

አክለውም፤ በቀጣይ የታቀዱ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ ትናንትን በቁጭት ዛሬን በዝግጅት ከቀበሌ አመራርና ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት ቁርጠኛ ሁኖ መስራት ያስፈልጋል በማለት የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የከተማው የማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ሎት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር መንግሥቱ መኩሪያ በበኩላቸው፤ በየቀበሌ የመልካም አስተዳደር ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮች በመለየት ለህዝቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አያይዘውም ኢንጂነር መንግሥቱ፤ ስራ አስኪያጆች በየቀበሌ ከማህበረሰቡ ጋር ጤናማ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚገባ እና ሁሉንም ተልዕኮዎች ለማሳካት በቀበሌ ደረጃ ተተክለው ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸው ይህን የማያደረግና የማይፈፅም አካል ላይ መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት አስተዳደራዊ እርምዳ እንደሚወሰድ ጠቁመዋል።

ለልማት ሁሉ ጣሪያና ግድግዳ ግብር ጀርባ አጥንት በመሆኑ የመንግስት ገቢን የቀበሌ አመራሮች በልዩ ቁርጠኝነት መሥራት እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተናግሯል።

ስራአስኪያጆች በሰጡት ሀሳባቸው፤ በመድረኩ ክፍተቶቻችን የለየንበት በቀጣይ ለመስራት በቂ እና ትምህርት ያገኘንበት መድረክ ነበር በማለት በየቀበሊያችን የመልካም አስተዳደር ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮች በመለየት ለህዝቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ተግባቦት ተፈጥሯል።

️በመጨረሻም ከመድረኩ ቀበሊያትን በሚመለከት ስራ አስኪያጆች ምን እንደሚመስሉ በሰፊው አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ቀጣይ መሰራት ያለባቸው ተግባራት ላይ ከመድረኩ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጦ ተጠቃሏል።

ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በኮንታ ዞን የአመያ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዩኒት የግብርና ባለሙያዎች ግምገማ ነክ ስልጠና መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል።ግምገማ ነክ ስልጠናው ባለሙያዎች በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በተግባር...
14/11/2026

በኮንታ ዞን የአመያ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዩኒት የግብርና ባለሙያዎች ግምገማ ነክ ስልጠና መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ግምገማ ነክ ስልጠናው ባለሙያዎች በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በተግባር አፈጻጸም እንዲሁም በሙያውና በስነ ምግባር የታነጹ እንዲሆኑና የሳይንሳዊ ዕውቀትን አጎልብቶ የግብርና ተግባራት ውጤታማ ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል ።

በ2018 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራቶችን መነሻ ያደረገ መሆኑ የተገለጸ ስሆን በ2018 አፈጻጸም ወቅት የተስተዋሉ ጠንካሬዎችና ማነቆዎች ተለይው ለተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የግብርና ባለድርሻ አካላት በሙሉ ዲስፕሊን መከታተል እንዳለባቸው ተገልጿል።

በመድረኩም የከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ታምራት ጫንያለው፣ የመንግስት ረ/ተጠሪ አቶ ተስፋዬ መኮን፤ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ገብሬን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የፓርቲ አመራሮች፤ አጠቃላይ የቀበሌ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለማጠናከር የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ትልቅ ሚና አለው ፤ አፈ-ጉባኤ አቶ ተስፋዬ ገዳዎበኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ቀን "...
13/11/2026

ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለማጠናከር የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ትልቅ ሚና አለው ፤ አፈ-ጉባኤ አቶ ተስፋዬ ገዳዎ

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ቀን "ብዝሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ "በሚል ሚሪ ቃል ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ታሳቢ ያደረገ ማጠቃለያ ከመንግስት ሠራተኞች ጋር የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ የአመያ ከተማ አስተዳደር ጊ/ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ተስፋዬ ገዳዎ እንደገለጹት፤ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል መከበሩ አብሮነት እንዲጎለብትና የተሳሰረ ማንነት እንዲጠናከር፤ባህል፣ቋንቋ እንዲሁም በማንነቱ እንዲኮራ አድርጓል ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገለጫ ነው በማለት ገልፀዋል።

ሀገራችን የጀመረችውን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን ጉዞ ሁሉም ዜጋ በባለቤትነት የበኩሉን እንዲወጣ የብሔር ብሔረሰቦች ተሳትፎ አስፈላጊ በመሆኑ ውይይቱ መዘጋጀቱን ገልፀው መንግሰት ሰራተኛውም ይህንን በመገንዘብ ነፃና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት የመንግስት ሃብት መጠበቅ እንዳለበት ጠቁመዋል።

የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት እና መሰባሰብ ለሀገር እድገት ወሳኝ በመሆኑ አንድነታችንን በሚያፀናና በሚያሳይ መልኩ በዓሉ በከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ ቀበለያት በተለያዩ ዝግጅቶች ስለመከበሩን ተናግሯል።

የከተማው የብልጽግና ፓርቲ ረ/የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ገብሬ እንዳሉት፤ ማህበረሱቡም በብዝሀነት ውስጥ አንድነትን በማጠናከር በህዝቦች መካከል ለአመታት የዘለቀውን አብሮነትና ወንድማማችነትን ማጠናከር በዓሉ ፋዳ የጎላ ነው ብለዋል።

"ኢትዮጵያን ደምቃ የምናገኛት በብዝኃነት ውስጥ መሆኗን አውስተው ለዚህ ደግሞ በመንግስት ሰራተኛው ውስጥ ያለው የአብሮነት እና የህብረ-ብሄራዊ አንድነት መንፈስ ጥሩ ማሳያ እንደሆነ ተናግሯል።

በመድረኩ የህገመንግስት አስተምህሮ ዙሪያ የተዘጋጀውን ስነድ የአመያ ከተማ አስተዳደር ፍትህና ፀጥታ ጽ/ቤት የህግ ባለሙያ ወ/ሪት ብርቱካን ቡልቶ እንደገለፁት፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በየአመቱ መከበሩ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጎልበት የኢትዮጵያውያንን አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑንም አብራርተዋል።

አክለውም፤ ማናችንም ብንሆን ከህግ በታች መሆናችን አውቀን ለህገ- መንግስቱ ተገዢ ሆነን በተሰማራንበት ውጤታማ መሆን ያስፈልጋል ሲሉ አብራርተዋል።

ተሳታፊ አካላትም "ሀገራዊ አንድነትን በማስጠበቅና ሰላምን በማጽናቱ ረገድ እንደመንግስት ሰራተኛ የሚጠበቅብንን ግዴታ ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ ነን" ብለዋል::

#ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በአመያ ከተማ አስተዳደር ዱካ ዛሌ ቀበሌ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በልማት ፣በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የህዝብ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ታምራት ጫን...
11/11/2026

በአመያ ከተማ አስተዳደር ዱካ ዛሌ ቀበሌ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በልማት ፣በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የህዝብ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ታምራት ጫንያለው፣ የብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ረ/ተጠሪና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኮንን፣ ረ/የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንደሙ ገብሬ የዱካ ዛሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር የልማትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ የህዘብ ውይይት መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ የከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ታምራት ጫንያለው እንደተናገሩት፤ መንግሥት ህብረተሰቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስና ሁለንተናዊ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሲሰራ ቆይቷል እየሰራ ተናግሯል።

አክለውም፤ መንግሥትን የሚመራው ፓርቲያችን ብልፅግና የተጀመሩ የልማት ተግባራትን በማጠናከር የህዝቡን ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በመስራትና በአፈፃፀም ሂደት የሚታዩ ጉድለቶችን በውይይት ለመፍታት ከህዝቡ ጋር ውይይት በማድረግ ህዝቡን ማዳመጥ ተገቢ እንደሆነም ተመላክተዋል ።

በውይይት መድረኩ መንግሥት የህዝቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስና የተለያዩ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአጭርና ረዥም ጊዜ ዕቅድን በማዘጋጀት እንደሚሰራና እየሠራ እንደሚገኝ ተናግሯል።

የከተማው ረ/የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኮንን በበኩላቸው፤ መንግሥትን የሚመራው ፓርቲያችን ብልፅግና የተጀመሩ ልማት ሥራዎችን በማጠናከር መጪውን በዕቅድ አስቀምጦ በመሥራት የህብረተሰባችን የመልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ በመመለስ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

ረ/የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ገብሬ እንዳሉት፤ የተጀመሩ ልማት ሥራዎችን በማጠናከር የዛሬውን በተግባር የነገውን ደግሞ በዕቅድ አስቀምጦ በመሥራት ለዘመናት የቆየውን ውስብሰብ ችግሮችንና የህብረተሰባችን የመልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ትኩረት ሰጥተው እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የመድረክ ተሳታፊዎች አጠቃላይ የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ሌሎች ችግሮችንና በየደረጃው የሚስተዋሉ የተለያዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችን አንስተው በመወያየት ተገቢ ምላሽ ከመድረኩ ተሰጥተው መግባባት በመፍጠር ውይይቱ ተጠናቅቋል።

ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

የ21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን የወረዳ ፐብሊክ ሰርቫንት በፓናል ውይይት አከበሩበኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ''በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን...
11/11/2026

የ21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን የወረዳ ፐብሊክ ሰርቫንት በፓናል ውይይት አከበሩ

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ''በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ'' በሚል መርህ ቃል ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓልን የወረዳው ፐብሊክ ሰርቫንት በፓናል ውይይት አክብረዋል።

በመድረኩ ተገኝቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳ ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ መሉነሽ አየለ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል በብዝኃነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር በማድረግ ህብረብሔራዊና አገራዊ አንድነት እንድጎለብት የሚያደርግ በዓል መሆኑን አብራርተዋል።

ብዝሃነትን በማስተናገድ ዲሞክራሲያዊና አገራዊ አንድነትን ከማረጋገጥ አንፃር የበዓሉ መከበር የሚኖረው ፋይዳ ከፍ ያለ መሆኑን አውስቶ የሕዝቦች ሕገ-መንግስታዊ መብቶችን ለማስከበር፣ አብሮነት፣ ወንድማማችነት ሥር እንዲሰድ እና ጤናማ የፌዴራል ሥርዓት እንዲጎለብት አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

የወይይት መድረኩን የመሩት የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና ሕዝብ ገንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ አደሮ
ሕዝቦች በብዝኃነት፣ በእኩልነት፣ በመከባበርና በምክክር ላይ የተመሰረተ ሕገ- መንግሥታዊ ግንዛቤን እንዲያዳብሩ ፣የጋራ ባህልና እሴቶችን እንድያጎለብቱ እንዲሁምአንድነትን እንዲያጠናክሩ የሚያደርግ በዓል መሆኑን ገልፀዋል።

የወረዳ ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ አቶ አደሮ አሰፋ የብዝሃነት አስተዳደር እና የመንግስታት ግንኙነት ለጠንካራ የፌደራል ስርዓት ግንባታ በሚል መርህ ቃል የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ አቅርበው በፐብሊክ ሰርቫንት የፓናል ውይይት ተደርጓል።

የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ማጠናከር የአካባቢውን ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ልማዳዊ እውቀት፣ ጥበብና የጋራ እሴቶች በእኩል ዕድል ማስተዋወቅ የሴቶች፣ ወጣቶች አረጋውያንና ሌሎች ተጋላጭ ቡድኖች ተሳትፎን የሚያረጋግጡ የጋራ የሆኑ እሴቶች የምጎለብትበት በዓል መሆኑን ጠቁመዋል።

በዓሉን በተለያዩ ኪዋኔዎች ያከበሩት መንግስት ሰራተኞች በበኩላቸው በቀረበው ሰነድ ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችንና ሀሳብ አስተያየቶችን ያነሱ ሲሆን ለተነሱ ሀሳቦች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ አንድነትንና የጋራ እሴቶችን በሚያጠናክር መልኩ ተከብሯል።

ዘገባዉ፦ በኮንታ ዞን የአመያ ዙሪያ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Address

Ameya
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ameya City Prosperity Party Branch Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category