Kedo fiker

Kedo fiker Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kedo fiker, Grocers, Addis Ababa.

05/10/2026
30/09/2026

ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሆነው የተሰየሙት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

30/09/2026

ወ/ሪት ፈይዛ መሐመድ ዑመር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እጩ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሪት ፈይዛ መሐመድ ዑመር የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

30/09/2026

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

30/09/2026

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ

ላለፉት አመታት አዲስ አበባን በከንቲባነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድጋሜ ከንቲባ ሆነው በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ተሰይመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታና 4ኛው ዙር የከተማው ምክር ቤት የመክፈቻ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመሩበት ሁሉ ውጤት የሚያስመዘግቡ ጠንካራ የህዝብ ልጅ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ያስመሰከሩ ናቸው።

በከተማው የስራ ባህል እንዲለወጥ የህዝብ ችግር የሚፈቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በማሰራት ከተማዋን በለውጥ ጎዳና መርተዋል።

ከተማዋ አዲስ አበባ በሰው ተኮር የልማት ስራዎች ተጠቃሽ እንዲትሆን አስችለዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፅናትን ብርታትን ለዓላማ ታምኖ መስራትን በከተማዋ የለውጥ ስራዎች ላይ አስመስክረዋል ሲሉ የምክር ቤት አባላትም ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኦሮሚያ ክልል ከመምህርነት ጀምሮ በበርካታ የሃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።

እንዲሁም በፌዴራል ደረጃም በበርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊነት አገልግለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሰየሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

30/09/2026

"ያለፉትን አምስት አመት የከተማችንን መልክ እንቀይራለን ፣ የህዝባችንን ክብር እናስጠብቃለን፣ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አዲስ እናደርጋለን ብለን ቃል ገብተን ነበር ይህም ከጠበቅነውና ካቀድንው በላይ ተሳክቶልናል፡፡

ሆኖም የትላንቱ ስኬት የነገ ኃላፊነትን አይተካም፡፡ ትላንት የከተማችንን ገፅታ ለመቀየር ሰርተናል በርካታ ስራዎችንን አከናውነናል ያቀድንውም ተሳክቶልናል በቀጣይ የነዋሪዎቻችንን ኑሮ በተጨባጭ ማሻሻል የሚችሉ ስራዎችን ማከናወን ይጠበቅብናል፡፡

ሪፖርታችን ብዛት ወይም ቁጥር አይሆንም በዜጋው ህይወት ላይ በመጣው ተጨባጭ ለውጥ ብቻ መሆን ይገባዋል"፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

30/09/2026

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሾሙ

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

30/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበዋል።

በዚሁም፡-
አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ በመሆን በከንቲባዋ የቀረቡ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቀረቡትን ሹመቶች አጽድቋል።

30/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን የካቢኔ አባላት ሹመት አፅደቀ
በዚህም መሰረት፦

• ዶ/ር አህመዲን መሃመድ - የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ

• ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ - የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ

• ኢንጂነር አያልነሽ ኃብተማሪያም - የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ

• ወ/ሪት ጽዮን ደረጀ (የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል)- የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ

• ኢንጂነር ህይወት ፀጋዬ - የግንባታ ቁጥጥርና ፈቃድ ቢሮ ኃላፊ

• ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ - የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ

• ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል - የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ

• አቶ ግርማ ሰይፉ -የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

• አቶ ቢኒያም ምክሩ -ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

• አቶ ሙሉቀን ታሪኩ - የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

• ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ

• ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ - የጤና ቢሮ ኃላፊ

• ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

• አቶ አወሌ መሃመድ ኡመር - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ

• ዶ/ር ተፈራ ሞላ - የትራንስፖርት ቢሮ

• ኢንጂነር አይሻ መሃመድ - የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር

• ኢንጂነር ሔለን ገመዳ - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ

• ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ - የህፃናት ማህበራዊ ጉዳይና ሴቶች ቢሮ

• አቶ ተስፋዬ ደጀኔ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ

• አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

• አቶ መላኩ ታምሩ - የመሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kedo fiker posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category