SL Sport

Directions

SL Sport Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SL Sport, Grocers, Addis Ababa.

አርሴናል ስነልቦናው በጣም ስስ ነው። ደጋፊዎችም ቢሆኑ እንደ ህፃን ልጅ በትንሽ የተስፋ ጭላንጭል የሚደሰት መንፈስ በትንሽ እንቅፋት በሀዘን ቀሽ ብሎ የሚሰበር ልብ ነው ያላቸው። ብዙ አድካሚ...
15/12/2024

አርሴናል ስነልቦናው በጣም ስስ ነው። ደጋፊዎችም ቢሆኑ እንደ ህፃን ልጅ በትንሽ የተስፋ ጭላንጭል የሚደሰት መንፈስ በትንሽ እንቅፋት በሀዘን ቀሽ ብሎ የሚሰበር ልብ ነው ያላቸው። ብዙ አድካሚ ስራ የሚጠብቀውን የሊግ ዋንጫ ገና ሲዝኑ ጅማሬ ላይ የኛ ነው ብለው አፋቸውን ሞልተው ይናገራሉ። ከዛ እንዲህ ክለባቸው የተወሰኑ ጭዋታዎች ላይ ውጤት ሲጠምበት ደግሞ ተስፋ ቆርጠው በሀዘን ኩርምትምት ብለው ይቀመጣሉ። ይህ ባህሪያቸው ሁሌም ይደንቀኛል።

ወደ ክለባቸው እና ውጤታቸው ስንመለስ ደግሞ ከውጤቱ ይልቅ አሰልጣኛቸው ከጭዋታ በኋላ የሚሰጠው አስተያየት የአርሴናልን ደጋፊዎች የበለጠ ሊያስጨንቃቸው ይገባል። "ጥሩ ነበርን ማሸነፍ ይገባን ነበር" እያለ ሲናገር ትንሽ አይደብረውም። ድክመታቸውን በግልፅ ተናግሮ ተጫዋቾቹን ገስፆ ለዋንጫ ተፎካካሪ ለማድረግ ጥረት ካላደረገ በቀር እንዲህ ሁሌ ጥሩ ሳይሆኑ ምርጥ ነበርን የሚል ሽፋን እየሰጣቸው በሚኬል አርቴታ የአርሴናልን እድገት እንዳትጠብቁ።

ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ በማንሲቲ ላይ፡ " ማን ሲቲን የማሸነፍ እድል ካጋጠመህ ሁሌም ከገና በፊት ነው። ምናልባት ገና ሲዝኑ እንደጀመረ በመጀመሪያዎቹ ሶስት፣ አራት ወራት ውስጥ እስከሚ...
14/12/2024

ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ በማንሲቲ ላይ፡ " ማን ሲቲን የማሸነፍ እድል ካጋጠመህ ሁሌም ከገና በፊት ነው። ምናልባት ገና ሲዝኑ እንደጀመረ በመጀመሪያዎቹ ሶስት፣ አራት ወራት ውስጥ እስከሚሟሟቁ ይቆያሉ፣ ከዚያም ከገና በኃላ እስከ አዲስ አመት ድረስ ይመጣላቸዋል። እውነቱን ለመናገር እነሱን ስለማሸነፍ መርሳት ይሻላል።

"አንዴ አዲስ አመት አካባቢ ሪትም ውስጥ ሲገቡ አምስት ወራት ሳይሸነፉ ይሄዳሉ፣ አንድ ወይም ሁለት አቻ ሊወጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዝም ብለው ማሸነፍ ይቀጥላሉ። ዘንድሮም እንደዛ ቢሆን አይገርመኝም።

"እስካሁን ካገኙት በላይ ምናልባት ብዙ ነጥቦችን ጥለዋል፣ ነገር ግን በተከታታይ አራት የሊግ ዋንጫ አሸንፈዋል፣ ትሬብል አሳክተዋል ፣ በሚያስደንቅ ሁኔታ world class የሆኑ ተጫዋቾች፣ ከሚገርም አሰልጣኝ ጋር አላቸው። ስለዚህ በፍጹም ችላ ልትላቸው አትችልም። የውድድር ዘመኑ መጨረሻ ላይ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክር ቢመለሱ አይገርመኝም …"
SL sport

መከረኛው ዛሬ ይጫወታል። ከፈለገ ያሸንፍ፣ ከፈለገ ይሸነፍ፣ ከፈለገ አቻ ይውጣ! እኔ ምናገባኝ! ያገባኛል?
14/12/2024

መከረኛው ዛሬ ይጫወታል። ከፈለገ ያሸንፍ፣ ከፈለገ ይሸነፍ፣ ከፈለገ አቻ ይውጣ! እኔ ምናገባኝ! ያገባኛል?

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SL Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category