02/06/2026
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ድምጹን በመስጠት ለዲሞክራሲዊ ግንባታ አስተዋጽዎ አድርጓል የሀረሪ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን
የሀረሪ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን በትላንትናው እለት የተካሄደውን 7ኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በሀረሪ ክልል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የክልሉ ፌዴሬሽን አመራሮች ጨምሮ 250 የሚጠጉ ወጣቶች በምርጫ ታዛቢነት ተሳትፈዋል።
የክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወጣት ረስተም ኡመር እንደገለጹት ፌዴሬሽኑ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የምልከታ ስራዎችን አከናውኗል።
በዚህም ምርጫው ፍፁም ሰላማዊና ነጻ ሆኖ መጠናቀቁን ተለያዩ አካላት የተሰበሰቡ መረጃዎች ያረጋገጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በተገኘው መረጃ መሰረትም ዜጎች የወደዱትንና የፈለጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ያለ ምንም ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ ሳይኖር በነጻነት መምረጥ መቻላቸውን አረጋግጠናል ብለዋል።
የክልሉ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ፣ ይበጀኛል ያለውን ፓርቲ በሰለጠነ መልኩ በድምጹ በመምረጥ ለዲሞክራሲ ግንባታ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ወጣት ረስተም ኡመር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የምርጫው ሂደት በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ፌዴሬሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።