04/07/2024
በቤቶች ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ ተቋሙን የማይወክሉ መረጃዎችን እያሰራጨ መሆኑን በተደጋጋሚ ማሳወቃችን ይታወሳል
ከዚህ በታች ያለውም የተሳሳተ መረጃ ተቋማችንን የማይወክል እና ሀሰተኛ መሆኑን ቢሮው እየገለፀ ተቋሙ በዚህ ገፅም ሆነ ይህንን ገፅ ተጠቅመው ሀሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እስኪያስወስድ ድረስ ህ/ሰቡ በሀሰተኛ ገፅ እና መረጃ እንዳይታለል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያሳውቃል።