27/03/2024
የተከበራችሁ የዶቼ ቬለ ተከታታዮች፤ የስርጭት ሰዓታችን እየደረሰ ነው። ለዛሬ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓም የዜና መጽሔት፤ በኢትዮጵያ ድርቅ፣ ረሃብ እና የምግብ ዋስትና እጦት ስጋት እያንዣበበ መሆኑን፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን የዶዶላ የንጹሐንን ግድያ እንዲሁም የኢትዮጵያውያንን የኑሮ ሁኔታ ያመላከተውን ጥናት የሚያስቃኙ ዘገባዎች በዝርዝር ይቀርባሉ።
ለዛሬ ከኤኮኖሚው ዓለም፤ «የኢትዮጵያ እና የአይኤምኤፍ ባለሞያዎችን የውይይት ውጤት የሚጠባበቀውን የዕዳ ክፍያ» ላይ አተኩሯል፤ ሳይንስና ቴክኒዎሎጂ ደግሞ ይፋ ስለተደረገው «ኢትዮጵያ በመካከለኛው ዘመን የሰው ልጅ አመጣጥ ላይ ጉልህ ድራሻ እንዳላት የሚያሳይ አዲስ ጥናት»ን ይዳስሳል። የቀጥታ ስርጭታችንን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።