Ette Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ette, Grocers, addis aba ba, Addis Ababa.

17/04/2024

ቁልፍ የፖለቲካ ስብራታችንን ከመጠገን አንጻር የብሔራዊነት ትርክት ፋይዳ ምንድነው?

እኛ ኢትዮጵያዊያን የወል ብሔረ መንግስት (Nation) በመመስረት አሰባሳቢ ሀገረ መንግስት (State) መገንባት ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ዘላቂ ወረቶች በጋራ ያካበትን ህዝቦች ነን፡፡

በጋራ ያካበትናቸው ወረቶች እንደተጠበቁ ሆነው እስካሁንም ያልተሻገርናቸው የፅንፍ አስተሳሰቦች አሉ፡፡ እነዚህ የጽንፍ አስተሳሰቦች በአንድ አመራር ትውልድ የተፈጠሩ ሳይሆን ከብሔረ- መንግስታችን ምስረታ እና ከሀገረ - መንግስታችን ግንባታ ጀምሮ የነበሩና እስካሁንም ድረስ ከእኛ ጋር ያሉ ናቸው፡፡ ዳሩ ግን እነዚህ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦችና ከእነሱ የሚመነጩ ድርጊቶች የየራሳቸው ምንጮች ያላቸው ናቸው፡፡

ምንጮቻቸውም ፓርቲያችን በተለያዩ ጊዜያት በትላልቅ ሰነዶቹ ጭምር በግልፅ እንዳስቀመጣቸው ፍፁማዊ አንድነትና ፍፁማዊ ልዩነት የሚሰኙ የተቃርኖ ትርክቶች ናቸው፡፡ በብልፅግና እምነት ደግሞ ፍጹማዊ አንድነትም ሆነ ፍጹማዊ ልዩነት ሀገራችን ኢትዮጵያን የማይመስሉ ብቻ ሳይሆን የማይመጥኑም መሆናቸው ነው፡፡

እነዚህ የህዝቦች አንድነትና የሀገር ቀጣይነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የደቀኑ ትርክቶችና ፅንፈኛ አስተሳሰቦችን ተሻግረን ሁሉም ህዝቦችና ዜጎች እኩል የሆኑበት ከተማና ሀገር እውን ለማድረግ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነት አለበት።

የብሄራዊነት ትርክት በአንድ በኩል ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመጣችባቸው አባጣ ጎርባጣ የሀገር ምስረታና ሀገረ መንግስት ግንባታ የሚነሱ የተቃርኖ ትርክቶችን ከስር መሰረታቸው በመግራት ሀይል ለማሰባሰብ ያግዛል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በአርበኝነት መንፈስ የተቃኘ አንድነት፣ ወንድማማችነትና አብሮነት በመትከል የጠነከረችና ሰላማዊት የሆነች ሃገር እውን ለማድረግ ያስችለናል፡፡

ይሄን ማድረግ በመቻላችን በሃገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ እኩልነት እንዲረጋገጥ፣ ወንድማማችነት እንዲያብብ፣ የዴሞክራሲ ባህል እንዲዳብርና ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን እንዲሆን ያስችላል፡፡

17/04/2024
16/04/2024

ስለ ሰላም እንዘምራለን፤ ደግሞም እንሰራለን!

የዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት ሲንከባለሉ የመጡ እና በየጊዜው ቅርፃቸውን የሚቀያይሩ ሳንግባባ ያደርንባቸውን አገራዊ ጉዳዮች ጭምር ህዝባችንን በማሳተፍ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት በመስጠት አገራዊ አንደነታችንን በማይናወጥ መሰረት ላይ ለመገንባት ከለውጡ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።

በእሳት ተፈትኖ ነጥሮ እየወጣ ያለው የለውጡ መሪ መንግስታችን እና ፓርቲያችን "ኢትዮጵያ አበቃላት" ያስባለውን ከውጭም ከውስጥም የተደቀነባትን ምናልባትም በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ውስብስብ ፈተና ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ እንደ ጉም ከመግፈፉ በተጨማሪ የቆመለትን ኢትዮጵያን የማበልፀግ ዓላማ ለአፍታም ሳይገታ አጠናክሮ አስቀጥሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያን መለወጥ የማይመኙ፣ በልፅጋ ማየት የማይፈልጉ የውስጥና የውጭ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ፍላጎታቸው የሚሳካው እርስ በእርስ ስንጣላ እንጅ ስንፋቀር ባለመሆኑ 24 ሰዓት በታዛቢነት ከዳር ሆነው የሚመለከቱትን የጦርነት ፊሽካ መንፋታቸውንና ከእሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፋቸውን አላቆሙም።

ኢትዮጵያዊያን የጦርነትን እና የግጭትን አስከፊነት በየጊዜው የህይወት መስዋዕትነት እና የንብረት ውድመት ውድ ዋጋ እያስከፈለን እያለፍንበት ያለ የአስከፊ ታሪካችን ገፅታ ጭምር እንጂ ከርቀት የምንሰማው ጉዳይ አይደለም።

የግጭት አትራፊዎች ያልተቋረጠ የገቢ ምንጭ በሬ ወለደ የሚሉ የሀሰት ወሬዎች በመሆናቸው ሳያረጋግጡና ሳያመዛዝኑ የሚያዳምጡ ግለሰቦችን ወደ እኩይ መረባቸው ለማስገባት ጠዋት ማታ ያሰራጫሉ።

ከሀሰተኛ መረጃዎች ራስን መጠበቅ እንዲሁም በዘመኑ የሚዲያ አማራጮች ውሸታቸውን ማጋለጥም ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል።

የአገር ዋልታ የሆነው መከላከያ ሰራዊታችን እና ሌላውም የፀጥታ ሀይላችን አስተማማኝ ሰላማችንን ለማረጋገጥ ለሚወስዳቸው አጥፊዎችን ወደ ህግ የማቅረብና ህግን የማስከበር እርምጃዎች እንደተለመደው ደጀንነታችንና ድጋፋችንን ማጠናከርም ይገባል።

የግጭት አትራፊዎች ስለሰላም ማውራትን፣ ስለሰላም ነገሮችን በትዕግስት ማለፍን እንዲሁም የሀይማኖት አባቶችን የሰላም ምክር እንደ ሞኝነት ቢቆጥሩትም የኢትዮጵያን አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን እውን ለማድረግ ቆርጠን በመነሳታችን ዛሬም ሆነ ነገ ስለ ሰላም እንዘምራለን፤ ደግሞም እንሰራለን!

16/04/2024

በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ተደርገዋል::

በኮሪደር ልማት ምክንያት ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ያለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ ተዘግቶ የነበረው መንገድ በከፊል ክፍት ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

•ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም የሚችሉ እና ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ምልክትና ማመላከቻዎች አክብረው እራሳቸውንና ሌሎችን ከትራፊክ አደጋ እየጠበቁ መንገዱን መጠቀም እንደሚችሉ እናስታውቃለን::

15/04/2024

ቃልን በተግባር የሚያፀና ብልጽግናዊ ጉዞ በመዲናችን አዲስ አበባ እንደቀጠለ ነው!

የብልጽግና ፓርቲ ዋና መገለጫ የገባውን ቃል በተግባር በመፈጸም ለህዝብ ጥቅምና አገልግሎት ማዋል ነው። ፓርቲያችን የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማሳለጥና ከሚገባት የከፍታ ማማ ለማድረስ መደመርን መንገዱ አድርጎ በህብረብሔራዊ አንድነት የፀናች ሀገርን ለትውልድ ለማውረስ በመትጋት ላይ ይገኛል።

የፓርቲያችን መሰረት ሰው ነውና ለህዝብ ቃል የገባውን የለውጥ ጉዞ በሚታይና በሚጨበጥ ብርሃናማ ተስፋ ላይ ማስቀመጥ ችሏል። በተለይም አዲስ አበባ ከተማን ስሟንና ክብሯን በሚመጥን መልኩ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ዘርፈብዙ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው።

በመዲናዋ እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ውብ፣ ፅዲና ማራኪ ከማድረግ ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስርን በማሳለጥ ረገድ ሚናው የጎላ ነው። ፕሮጀክቱ የከተማዋን አጠቃላይ ገፅታ በመቀየር ዓለማቀፋዊ የቱሪዝም ማዕከልና መዳረሻ ለማድረግም ከፍተኛ ድርሻ አለው።

ብልጽግና ፓርቲ ቃሉን የሚያከብርና የሚፈጽም፣ የጀመረውንም በታሰበለት ጊዜና ዓላማ የሚያጠናቅቅ የሀገርንና የህዝብን ክብር የሚገነባ ዛሬና ነገን በወል ዕውነት የሚያስተሳስር የትውልድ ፓርቲ ነው። ለዚህም ነው በተግባራቱ ሁሉ የየዕለትን ብቻ ሳይሆን የነገውንም ዓቅዶና ዓልሞ ሀገራዊ ስብራቶችን በማረም ለትውልድ የሚተርፍ ምንዳን እየገነባ የሚገኘው።

ከዚህ አንፃር የኮሪደር ልማቱ የአዲስ አበባን አጠቃላይ ገፅታ በመቀየር ደረጃዋን የጠበቀች ውብና ማራኪ ዓለማቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ ትሆን ዘንድ ከፍተኛ ሚናን ይወጣል። አድስ አበባ የቱሪስት መስብ፣ የኢኮኖሚ ማዕከል፣ የፖለቲካና ዲፕሎማሲ መናኸሪያ በመሆን ለነዋሪዎች ምቹና ተጨማሪ ገፀ-በረከት መሆን ትችላለች፤ እየሆነችም ነው።

በአጠቃላይ ፓርቲያችን በያዘው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት የህዝብን ጥቅም ባረጋገጠ ሁኔታ ከተማዋን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተተገበሩ ያሉ ሰፋፊ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል። በዚህም ''ቃል በተግባር'' እየተገለፀ ሀገራዊ ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚረጋገጥ ሲሆን ከተማችንም በሚመጥናት ስምና ክብር የምትቀመጥ ይሆናል።

15/04/2024

ኢትዮጵያውያን አንድም ብዙም ነን!!

በአንድነታችን ውስጥ ህብረ ብሔራዊነታችን፣ በህብረ ብሔራዊነታችን ውስጥ ደግሞ አንድነታችን አለ።

የኢትዮጵያ ድምቀትና ጥንካሬ ምንጩ ብዝሀነቷ ነው።

ፓርቲያችን ብልፅግና ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ እና ከእውነታው በመነሳት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በመከባበርና በመቻቻል ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለመገንባት ከምስረታው ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

አካታች የዴሞክራሲ ስርዓትን ለመትከልና እና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለሰለሰ ጥረት እያደረገ የሚገኘው ፓርቲያችን በቅርቡ በሀገራችን የተፈጠረውን አንፃራዊ የሰላም አየር ዘላቂ ለማድረግም ቁርጠኛ አቋም ሰንቋል።

የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምፅ የሚስተናገድበትና ያለፉ ቁርሾዎችን በይቅርታ በመዝጋት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እንደሚፈነጥቅ የሚጠበቀው ብሄራዊ ውይይታችንም ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላማችን የጎላ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

Address

Addis Aba Ba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ette posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category