19/10/2025
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለፀ፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኼራ ሄደዋል ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ምክርቤቱ በመግለጫው፤ "የሀገራችን ዋርካ እና የሁሉም አባት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈታቸው የመላው ሀገራችን ህዝብ ሀዘን ነው" ብሏል፡፡
"ሀገራችን ታላቅ አባት አጥታለች" ያለው ምክርቤቱ፤ "እኚህን ታላቅ አባት ላበርክቷቸው ሀገራዊና ሃይማኖታዊ አስተዋፆ በሚመጥን መልኩ ስርዓተ ቀብራቸው በመንግስት ደረጃ ኢስላማዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኃላፊነቱን በመውሰድ የሚፈፅም መሆኑን" ጠቁሟል፡፡
ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን ይስጣችሁ።