Abebe shumea

Abebe shumea Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abebe shumea, Grocers, Addis Ababa.

።።  ።።።።። በህዝብ ነው።።።።።።። እስከ ቀን 20/06/2015 ዓ.ም ድረስ የሚከተሉት ሁኔታዎች እንዲሟሉ እና ከነገ ቀን 14/06/2015 ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ እናሳውቃለን!።።።።።...
20/02/2023

።። ።።።።። በህዝብ ነው።።።።።።።

እስከ ቀን 20/06/2015 ዓ.ም ድረስ የሚከተሉት ሁኔታዎች እንዲሟሉ እና ከነገ ቀን 14/06/2015 ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ እናሳውቃለን!
።።።።።።።።።።
በወልቂጤ ከተማ ውሃ ብሎ ለወጣ ህዝብ 7 ሰዎች በፈረሰው ደቡብ ክልል ልዩ ሃይል በከባድ መሳሪያ በጠራራ ፀሃይ በጭካኔ ሲገደሉ 32 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወቃል። ይሄንን ተከትሎ ለ6 ተከታታይ ቀናት ወልቂጤ ከተማ ዛሬ ጉብሬ ምንም ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንደቆመ ይታወቃል። ሆኖም የጉራጌ ክልል እና የፌደራሉ መንግስት እስከ ቀን 20/06/2015 ዓ.ም ድረስ የሚከተሉት ሁኔታዎች እንዲሟሉ እና ከነገ ቀን 14/06/2015 ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ እናሳውቃለን=-

1ኛ . የሞቱት 7 ንፁሃን ወንድሞቻችን ገዳዮች እና እንዲገደሉ ያዘዙት ለህግ እንዲቀርቡ በግልፅ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ! 32 የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በህግ አግባብ እንዲታይ!
2ኛ . የፈረሰው ደቡብ ልዩ ሃይል ወጥቶ አስፈላጊ ከሆነ መከላከያ ሰራዊት እንዲገባ
3ኛ . የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳና ህዝቡ በመደበኛ ህግ እንዲዳኝ
4ኛ . የወልቂጤ ጭፍጨፋ እና አካል ማጉደል በገለልተኛ አካል እንዲታይ
5ኛ . ህዝቡ የሚያነሳቸው የውሃ እና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈታ ፈጣን የመፍትሄ ተግባራት ማሳየት!
6ኛ . ንፁሃን የጉራጌ ልጆች ማሳደድ እንዲቆም እና የታሰሩ ንፁሃን የጉራጌ ልጆች እንዲፈቱ!

ማሳሰቢያ:-
1. ከነገ ጀምሮ ከተለያየ አካባቢ ህዝቡ ጥቁር ለብሶ የሟችና አካል ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተሰብ እንዲጠይቅ እያሳሰብን፡ ለቅሶ መድረስ ያልቻለ ባለበት ቦታ ሆኖ ጥቁር በመልበስ በሚድያ ለሞቱት ንፁሃንና ለተገፋው ጉራጌ አጋርነቱ እንዲገልፅ እንጠይቃለን!
2 . ከላይ ከ1-6 የተቀመጡ ነጥቦች እስከ የካቲት 20/2015 ተሟልቶ ምላሽ እንዲሰጥ ለፌደራሉ መንግስት እና ለጉራጌ ክልል አስተዳደር እያስጠነቀቅን ለሞቱት ነፍስ ይማር ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው ህዝባችን መፅናናትን እየተመኘን የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ፈጣሪ ምህረት እንዲያወርድላቸው እየተማፀንን ከነገ ማክሰኞ ቀን 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ እየጠየቅን ጠቅላላ የጉራጌ ክልል አካባቢዎች ከየካቲት 20/2015 ጀምሮ ጥያቄያችን ምላሽ ካላገኘ የትግል ጥሪ እንዲጠባበቅ እያሳሰብን እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ በማንኛውም ሰዓት ጥሪ እንደምናደርግ እናሳውቃለን። ለጉራጌ ህዝብ መሰረታዊ የልማት ጥያቄና የህልውና ጉዳይ እስራት; ሞት; ስደት፡; የአካል ጉዳት ይሁን የትኛውም መሰዋትነት ለመክፈል የተዘጋጀን ሲሆን የህዝባችን ክብር በቁርጥ ቀን ልጆቹ እውን እንደሚሆን አቋማችን የፀና ነው!
የካቲት 13/2015 ዓ.ም
ወልቂጤ

20/02/2023

ሼር

ወንድሙ ሲገደል ወንድሙን ካልከፋው፥
ደጁ ላይ ቅበረው ደሙ እንዲከረፋው!

👉 ህመማችን ሞታችን አለም በደንብ መስማት አለበት።👉 በካድሬ ሽማግሌ የሚድበሰበስ አደለም ተጠያቂ እንፈልጋለን!!
17/02/2023

👉 ህመማችን ሞታችን አለም በደንብ መስማት አለበት።
👉 በካድሬ ሽማግሌ የሚድበሰበስ አደለም ተጠያቂ እንፈልጋለን!!

17/02/2023

ወይ ጉራጌ የጠየቅነው ውሃ ያጠጡን ጥይት አንላቀቃትም ተጠያቂው ማን ነው?

06/09/2022

👉'' እያመመው መጣ'' አለ የከተማው ልጅ ቀስ በቀስ አንጠባጥበህ ጥለህ እንዴት እንደምትመሩት እናያለን አይናችን አሁንም ከኳሷ ላይ አንነቅልም !!

♦♦♦የተከዳው ብልፅግና ወይስ ጉራጌ?♦♦♦®®®® ፍርዱን ለእናንተ የተካደው ብልፅግና ፖርቲ ወይስ የጉራጌ ህዝብ ? ሰሞኑን ደኢህዴን የወለዳቸው ብልፅግና ፖርቲ አመራር ነን ተብዬዎች ፖርቲው ...
31/08/2022

♦♦♦የተከዳው ብልፅግና ወይስ ጉራጌ?♦♦♦

®®®® ፍርዱን ለእናንተ

የተካደው ብልፅግና ፖርቲ ወይስ የጉራጌ ህዝብ ? ሰሞኑን ደኢህዴን የወለዳቸው ብልፅግና ፖርቲ አመራር ነን ተብዬዎች ፖርቲው ተክዷል እያሉ ዲስኩራቸውን እየደሰኮሩ መሆኑን እየሰማን ነው ። መላው የጉራጌ ህዝብ ሆይ የተካደው የጉራጌ ህዝብ እንጂ ፖርቲው እንዳልሆነ ለአብነት እንመልከት።

1ኛ የጉራጌ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቀው የነበረው የክልልነት ጥያቄ
በለውጡ መንግስት ምላሽ አገኛለሁ ብሎ ለለውጡ በከፍተኛ ገንዘብ ሊተመን የማይቻል ዋጋ የከፈለ በመሆኑ መንግስት ጉዳዩን በትኩረት አይቶ ምላሽ ለመስጠት ቃል የገባ በመሆኑ

2ኛ የጉራጌ ህዝብ ምክር ቤት በተወካዮች አማካኝነት የክልልነት ጥያቄ የጠየቁ ሲሆን በምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳረፉት ሁሉም ተወካዮች የፓርቲው አባል መሆናቸው ይታወቃል። ስለዚህ አፅዳቂው ጠያቂውም የፖርቲ አባል ሆነው ሲያበቁ ታድያ ማንን ነው የሚሸውዱት ፖርቲ ተክዷል ብለው?

3ኛ በ2013 በጉራጌ ዞን ወረዳዎች ሀገራዊ ምርጫ ሲካሄድ ዋና መቀስቀሻ የነበረው የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ እናስመልሳለን እና በግልፅ ጉራጌን ክልል እናደርጋለን ነበር የዚ ሃሳብ ዋና ባለቤት አቶ ዕርስቱ ይርዳው ወሎ ቶሎደረስ(እስከነ አያቶቹ) ነበር
ለዚህም ሲቀሰቅስ የነበረ መሆኑን የሚያሳይ audio and vidio መረጃዎች እንደ አስፈላጊነቱ ለህዝብ የምናቀርብ በመሆኑ መረጋገጥ ይቻላል።

ስለዚህ ማነው የተከዳው ብልፅግና ፖርቲ ወይስ የጉራጌ ህዝብ??

በየቦታው ያለኸው የጉራጌ ህዝብ እና የጥያቄው ደጋፊ የሆናቹህ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቻችን በመሉ አሁን እየተሴረብህ ያለው ሴራ ትግሉ ረጅም እና ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን አውቀህ ትግልህን ልታቀጣጥል ይገባል።

በመጨረሻም በየቦታው ያለነው የጉራጌ ህዝብ በሀገራችን ያለውን የፀጥታ ችግር በመረዳት በኢትዮጲያዊነታችን ሳንደራደር ትግላችን በሰላማዊ መንገድ ብቻ በማድረግ ዋናው ግባችን የጉራጌ የክልል ምስረታ ላይ እንድናደርግ እናሳስባለን።

የተከዳው ብልፅግና ወይስ ጉራጌ?

ታምራት ውድማ ጉራጌ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ ሀላፊና ምክር ቤት አባል ነው ክላስተርን በድምፃቸው አሽቀንጥረው ከወረወሩት አንዱ ነው ይህም ብቻ አይደለም ከሰሞኑ አዋሳ ግምገማ መድረክ ክላስተ...
31/08/2022

ታምራት ውድማ ጉራጌ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ ሀላፊና ምክር ቤት አባል ነው ክላስተርን በድምፃቸው አሽቀንጥረው ከወረወሩት አንዱ ነው ይህም ብቻ አይደለም ከሰሞኑ አዋሳ ግምገማ መድረክ ክላስተሩን ውድቅ ማድረጉን ለጉራጌ ክልል መጠየቁን አምኜበት ያደረኩት ነው አፍንጫቹሁን ላሱ ብሏቸዋል ታምራት የወልቂጤ ነዋሪ ሁሉ ያውቀዋል መልከስከስ አያውቅም ጃኬት አይቀይርም ጉራጌን አይሸጥም እንዲህ ፀንቶ ይቆማል ሌሎቹም ፅናት ከሱ ይማሩ ይህ ልጅ ጉራጌ አባቶች ልጃቹህ ነው ይህ ልጅ የጉራጌ ወጣቶች ወንድማቹህ ሞዴላቹህ ነው ለሚደርስበት ሁሉም ነገር ከጎኑ ይቁም ።
ታምራት ክበርልን ሁሉም ይስማ

ሼር አድርጉ

ሼርርርርር ይደረግ👉 የወልቂጤ ከተማ ገቢዎች ባለሙያን የዞን ምክር ቤት ወሳኔ ይከበር ሪፈረንደም ባሉበት ጽንፈኛ ናቹ ብሎ የተሳደበው የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና የአደረጃጀት ሀላፊ አቶ ከድር ደ...
30/08/2022

ሼርርርርር ይደረግ

👉 የወልቂጤ ከተማ ገቢዎች ባለሙያን የዞን ምክር ቤት ወሳኔ ይከበር ሪፈረንደም ባሉበት ጽንፈኛ ናቹ ብሎ የተሳደበው የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና የአደረጃጀት ሀላፊ አቶ ከድር ደገፋ ይህ ነው !!!

በዛሬው እለት እሁድ በጉራጌ ትግል ለታሰሩ አመራሮቻችንና ወጣት ወንድሞቻችን ቤተሰብ በከተማው ወጣትና ሽማግሌ የስንቅ ድጋፍ ተደርጎአል!!!
28/08/2022

በዛሬው እለት እሁድ በጉራጌ ትግል ለታሰሩ አመራሮቻችንና ወጣት ወንድሞቻችን ቤተሰብ በከተማው ወጣትና ሽማግሌ የስንቅ ድጋፍ ተደርጎአል!!!

👉 መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልንቤተሰብ ይሁኑ
28/08/2022

👉 መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን

ቤተሰብ ይሁኑ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abebe shumea posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category