Ida'ama dhaloota

Ida'ama dhaloota Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ida'ama dhaloota, Grocers, Dubai.

19/09/2024

ኢትዮጵያ የአፍሪካዊያን ሁለንተናዊ ተምሳሌት- በጠንካራ ቀጠናዊ ትስስር ወደ ጋራ ከፍታ!

ኢትዮጵያ የረጅም ዓመታት የሀገረ መንግስት ስርዓት ያላት፣ ቀደምት የስልጣኔ ባለቤት፣ የሰው ዘር መገኛ እንዲሁም ለአህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ምስረታ የጎላ አስተዋፅኦ ያደረገች፣ ለዓለም ሰላም እና ለፍትሀዊነት አብዝታ የምትታትር ሀገር ናት፡፡

በህብር ደምቀው፣ በአብሮነት ፀንተው በመስዋዕትነታቸው ሀገራዊ ሉዓላዊነትን አስከበረው የዘለቁት ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ ከእራሷ አልፋ ለአፍሪካዊያን የነፃነት ቀንድሊ ሆና ለመላው የዓለም ጥቁር ህዝብም ኩራትና ተምሳሌት እንድትሆን አስችለዋል።

ኢትዮጵያዊያን በታሪካቸው ሉዓላዊነታቸውን ያላሰደፈሩ የማንንም ያልነኩ ጨዋ፣ ታታሪና አብሮ የመኖርና ማደግ ዕሴትን ያካበቱ ጀግኖች ናቸው። የአባቶቹን ፈለግ የተከተለው ይህ ትውልድ ሀገራዊ ክብርን ያስቀደመ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ያማከለ አብሮ የማደግ የመደመር መርህን ይከተላል። በጀግኖች አርበኞች ደም የከበረችዋን ሀገር በላቡ በማጽናት አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌትነትን ለማረጋገጥ ይተጋል።

ዘመንን በመዋጀት ቀደምት የሆነችዋ ሀገራችን አፍሪካዊያንን በሀሳብም ሆነ በተግባር ከቅኝ ተገዥነት ይላቀቁ ዘንድ ከፓን አፍሪካኒዝም ዕሳቤ እስከ አፍሪካ ህብረት ድርጅት ምሰራታ በአንድ ተሰባስበው ለነፃነትና ሉዓላዊነታቸው እንዲታገሉ በማድረግ ከፍተኛውን ሚና ተወጥታለች፡፡

ኢትዮጵያ በወንድማማችነትና እህትማማችነት ዕሳቤ የአፍሪካዊያንንና አህጉራዊ ትስስርን በማላቅ የወል ከፍታን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻን ተወጥታለች። ለዚህ ደሞ በየዘመናቱ የነበሩ መሪዎቿ እና በሁሉም የሀገሪቷ ጫፍ የሚገኙ ብሄር ብሔረሰቦች ሀሳብ በማመንጨትና እስከ ህይወት መስዋዓትነት በሚያስከፍል አህጉራዊ ትብብር ምስረታ ላይ እልህ አስጨራሽ ዋጋን ከፍለዋል፤ ዛሬም የኢትዮጵያ ተምሳሌትነት ዘመንን በዋጀ የትብብር መንፈስ እንደቀጠለ ይገኛል።

ይህ ትውልድ ዘመንን ይዋጃል፤ ትናንትን ከዛሬ አስተሳስሮ የነገን ይሰራል። በዚህም በመደመር መርህ ኢትዮጵያ የነበራትን ተምሳሌትነት በማላቅ ከፍ ወደአለ ሽግግር ለማድረስ በመትጋት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስብራቶችን በመጠገን ብልጽግናዊ የትብብር ተምሳሌትነትን ለማጽናት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በመከወን ላይ ነው።
የመደመር ትውልድ የአፍሪካ መዲና የሆነችዋን አዲስ አበባንም ስምና ታሪኳን በሚመጥን መልኩ ላቅ ወደ አለ ከፍታ በማሸጋገር አፍሪካዊ ተምሳሌትነቷን እያረጋገጠ ይገኛል።

ፓርቲያችን ነባር የኢትዮጵያን ሚና በማላቅ በአፍሪካ ትብብርና ፉክክር መሳለመሳ የሚጓዙበትን ጠንካራ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትስስርን በመገንባት የህዝቦችን የቆየ ትስስር በማስቀጠል አህጉራዊ አንድነትንና ልማትን ለማዳበር እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እየተጋ ይገኛል፡፡ ሁለንተናዊ ተምሳሌትነትን በማሳለጥም በአጭር ጊዜ ከተስፋ ብርሃን ወደ የሚጨበጥ ብርሃን በመሻገር ብልጽግናዊ ተምሳሌትነትን ያፀናል።

የአፍሪካዊያን ኩራትና የነፃነት መነሻ የሆነችሁ ኢትዮጵያ ዘመንን በዋጀ የመደመር ዕሳቤ የነበራትን በማላቅ ተምሳሌትነቷን ታፀናለች። ይህ የመደመር ትውልድ የአባቶቹን አደራ የተረከበ በደም የከበረችዋን በላቡ የሚያፀና፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ሰላምን፣ ብልጽግናንና የጋራ ተጠቃሚነትን መርሁ አድርጎ የሚተጋ ነው። የወል የሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትበብርን የተከተለ ቀጠናዊና አህጉራዊ ትስስርን በማጎልበትም ለጋራ ብልጽግና ይሰራል።

ሰላምንና ልማትን መነሻው ብልጽግናን መዳረሻው ያደረገው የመደመር ትውልድ ዘመኑን በሚመጥን አርበኝነት ሀገራዊ ልዕልናን ይገነባል። የመደመር ትውልድ በሉዓላዊነቱና በሀገራዊ ክብር አይደራደርም፤ የሌላን አይፈልገም፤ ለጋራ ሀገራዊና አህጉራዊ ብልጽግና በተምሳሌትነት ይተጋል፤ ቀጠናዊ ትስስርን ለጋራ ተጠቃሚነት ይገነባል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

13/06/2024

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ባለፉት ወራት ውሰጥ የወረዳችንን ብሎም የከተማችንን ፅዳት እና ውበት ለማስጠበቅ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ድሪባ በባለፉት 10 ወራት የከተማችንን ውበት እና ፅዳት ለማስጠበቅ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ለመረጃ ክፍላችን በነበረን ቆይታ እንደሚከተለው ገልፀውልናል ።

የህዝብ ተሳትፎና ግንዛቤ ከማሳደግ ጋር በተያያዘ በወረዳችን ውሰጥ 5825 አባ ወራዎችና እማወራዎች ቤት ለቤት ግንዛቤ በስታንዳርዱ መሰረት መስጠት መቻሉን ገልፀዋል ።ከዚህ በተጨማሪም
በየሳምንቱ ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ በ8ቱም ቀጠናና በ40ዎች ብሎክ ላይ የፅዳት ንቅናቄ መካሄዱንም አብራርተዋል

ሳምንታዊ የተቋማት ጽዳት ንቅናቄ በተመለከተ አርብ አርብ በ16 ተቋማት በተለይ የወረዳ አስተዳደር 1 ፣ የትምህርት ተቋማት12 ፣ የሀይማኖት ተቋማት 4 በድምሩ በ16 ተቋማት ላይ ከፍተኛ ንቅናቄ ማድረግ ተችሏል
ሞዴል ብሎክ እና መንደር ከመፍጠር ጋር በተያያዘ በወረዳችን ከአሉን
40 ብሎኮች ውሰጥ 18 ነባር ሞዴል ብሎክ ማሰቀጠል 6 ደግሞ አዲስ ሞዴል ብሎክ መፍጠር እንደተቻለ አክለው አብራርተዋል

ከሀብት አሰባሰብ ጋር በተያያዘ 346000 ብር የሚገመት ለፅዳት ስራችን አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በተለይ አካፋ፣ማዳበሪያ ፣ ጓንት፣ መጥረጊያ ፣ ዲስትቢን ከባላሃብቶች እና ተቋማት መሰብሰብ ተችሏል

ከደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ እና አገልግሎት ከመስጠት አንጻር
በወረዳችን በ40ዎች ብሎክ ያሉ እማወራ እና እባወራ በሳምንት ውሰጥ ከ2 እስከ 3 ጊዜ የቤት ለቤት አገልግሎት እንዲያገኙ ጠንካራ ስራ ተሰርቷል

በ10 ወራት ውስጥ 4600 ቶን ደረቅ ቆሻሻ በመሰብስብ 69,840,560 ብር ገቢ ማግኘት እንደተቻለ ገልፀዋል።

ከመንገድ ፅዳት ጋር በተያያዘ 14 ኪሎ ሜትር ስታንደርድ የወጣላቸው የአስፋልት መንገድ በቀን ሁለት(2) ጊዜ መጽዳት ተችሏል

የመልሶ መጠቀምና ዑዳት ማድረግ በተመለከተ በህብረት ሽርክና የተደራጁት ማህበር በተለይ ማዳበሪያ ፣ብረታ ብረት፣ ሀይላንድ፣ማይካ፣ጠርሙሶች እና የወረቀትና ካርቶን ዑደት በማድረግ 10,000,000 ብር በላይ ማግኘት እንደተቻለ ገልፀዋል።

ህግ ወጥ ቆሻሻ በሚጥሉ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ በአዋጅ 150/2015 የእርምት እርምጃ በመውሰድ ብር 65,000 ብር ገቢ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል ።

05/10/2016 ዓ.ም

13/06/2024
ከለውጡ ወዲህ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ከተሰሩ ዘመን ተሻጋሪ ታላላቅ ስራዎች መካከል በታላቅነቱ ትውልድ የሚቀባበለው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ትልቁን ስፍራ ይይዛል! ከብልጽግና በፊት የነበሩት መንግ...
30/01/2024

ከለውጡ ወዲህ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ከተሰሩ ዘመን ተሻጋሪ ታላላቅ ስራዎች መካከል በታላቅነቱ ትውልድ የሚቀባበለው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ትልቁን ስፍራ ይይዛል!

ከብልጽግና በፊት የነበሩት መንግስታት እንደምን በዚህ ልክ ማሰብ ተሳናቸው ? ድሉን በየዘመኑ ለሚመጣው ትውልድ መማሪያነት አለመጠቀማቸው ቢያስቆጭም እነሆ ዘንድሮ ታላቁን ድል በታላቁ መታሰቢያ መዘከር የሚያስችል "ብሔራዊ ምልክት" በመቆሙ ኢትዮጵያውያንን የሚያስደስት የሚያኮራ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህ ታላቁ የዘመኑ አርበኝነት ነውና ሀሳቡን ከማመንጨት ጀምሮ መርተው አስተባብረው እስከ መጨረሻው ያስፈጸሙ የብልጽግና መሪዎችን ያለማመስገን ከንፉግነት በዘለለ ምንም ሌላ ትርጉም ሊሰጠዉ አይችልም፡፡

ከሁሉ በላይ ግን አንድ መሰረታዊ ጥያቄ በጋራ መመለስ ይገባናል፡፡ እሱም “ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ምን እንማራለን?” የሚል ነዉ፡፡

በተለይም የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ልጆች ከዚህ የሀገር ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ጀግንነትንና ጽናትን እንማራለን፡፡ ይህ ትዉልድ ይህንን የአባቶቻችንን ገድል እንደ አቅም በመጠቀም የበለጸገችና የጸናች ኢትዮጵያን መገንባትን እንማራለን፡፡

03/01/2024

ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሆኖ የተገነባ በሁሉም መመዘኛ ምልዑነትን የተላበሰ የኛ ትውልድ አሻራ!

ኢትዮጵያዊያን እንደ ድር ተጋምደን ያስመዘገብናቸው በዓለም አደባባይ ከፍ ያደረጉን አንፀባራቂ ታሪኮች አሉን።

ለአፍሪካውያን እንዲሁም ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት፣ የእኩልነትና የአትንኩኝ ባይነት አብነት የሆነው የአድዋ ድል የብሔር፣ የሀይማኖት እና መሰል ልዩነቶች ሳይገድቧቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አሻራቸውን ያሳረፉበት የወል ታሪካችን ነው።

አባት እናቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በጋራ ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ ታሪክ ሰርተዋል፤ የጋራ ታሪካችንን በአብሮነት ለመዘከር ግን በረባ ባልረባው ስንነታረክ ቆይተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቧራ ተነስንሶበት የነበረው የአድዋ ድል ታሪክ ተገልጦ ወርቅነቱ እንዲታይ ለማድረግና በዓመት አንድ ጊዜ ከመዘከር ባለፈ ዓመቱን ሙሉ እንዲወሳ የሚያደርገውን ግዙፉን የአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ላለፉት የለውጥ ዓመታት ሲገነባ ቆይቷል።

ሙዚየሙ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የአድዋን ድል ታሪክ በአብሮነት እንዲዘክር የሚያስችል ቦታ ላይ ያረፈ ከመሆኑም በላይ ታሪኩን በተሟላ መልኩ እንዲዘክር ተደርጎ የተሰራ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ አገራዊ ፕሮጀክት ነው።

የአድዋን የድል ታሪክ ከአርበኞችና ከመሪዎች ነጥሎ ማየት ስለማይቻል በአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም በተገቢው መልኩ የሚዘከሩበት ዕድል ተፈጥሯል።

የአድዋን ድል ስናነሳ የፈረሶቻችን ውለታ ባናወሳ የአድዋ ተራሮችም ጭምር ይታዘቡናል። በመሆኑም በሙዚየሙ የፈረሶቻችንን አሻራ የሚዘክሩ የጥበብ ስራዎችም ተካተዋል።

የአርበኞቻችንን ድል ከፍ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ዘመናዊ ጦር ታጥቆ የመጣውን ወራሪ ሀይል ጦር፣ ጋሻ፣ እና ጎራዴን በመሳሰሉ መሳሪያዎች በልበ ሙሉነት ገጥመው ድል ማድረጋቸው ነው።

በአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየምም የመሰባሰቢያ አዋጁ የተጎሰመበትን ታሪካዊ ነጋሪት ጨምሮ ጋሻ እና ጦራችን በሚገባ እንዲዘከሩ ሆኗል።

የአርበኞቻችንን መውጣትና መውረድ ለማሳየት በአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች አምሳል የተገነባው የአድዋ ሙዜም ባረፉበት የጥበብ አሻራዎች ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሆኖ የተገነባ በሁሉም መመዘኛ ምልዑነትን የተላበሰ የኛ ትውልድ አሻራ ነው!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

Address

Dubai

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ida'ama dhaloota posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category