19/02/2025
የኢትዮጵያ በምግብ ራስን የመቻል ጥረቶች
ብዙ ጊዜ አፍሪካን በዘላቂነት በዕርዳታ ላይ ጥገኛ አድርጎ በሚገልጽ ዓለም፣ ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ለመቻል ቆራጥ እርምጃዎችን በመውሰድ ይህንን ትርክት ለማስተካከል እየሰራች ነው።
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ስድስት አመታት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን በድፍረት በመተግበሩ የምግብ ዋስትናን ብቻ ሳይሆን የረዥም ጊዜ ራስን መቻልን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
እነዚህ ጥረቶች ኢትዮጵያ ከጥገኝነት ለመላቀቅ እና ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቁ ናቸው።
እንዲህ ያለው እምርታዊ ለውጥ በውጫዊ ድጋፍ ላይ ከመተማመን ያላቀቀ በመሆኑ ትኩረትን ስቧል። ስለሆነም በአምራችነታችን እና በመረጃዎቻችን ላይ ጥርጣሬዎችን እና ትችቶችን ሊፈጥር እንደሚችል እንገነዘባለን።
አገራዊ እድገትን ለማዳከምና የልማት ጥረታችንን በተለይም በግብርናው ዘርፍ ለማጣጣል የውጭ ጥረቶች እንዳሉ እናውቃለን። ነገር ግን፣ ቁርጠኝነታችን፣ ለክብር ከሚደክሙት በርካታ ገበሬዎች ጋር ተደምሮ የምግብ ዋስትና የፖሊሲ ግብ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን እና ለህዝባችን ህልውና አስፈላጊ ስለሆነ የማይናወጥ ነው።
የስንዴ ምርት ለማሳደግ የምናደርገው ጥረት፡ ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ወደ መቻል በምታደርገው ጉዞ የስንዴ ምርትን ዋነኛ ምሰሶ አድርጋለች። በመስኖ የሚለማ መሬት በማስፋፋት፣ የተሻሻሉ የዘር ዓይነቶችን በመጠቀምና ዘመናዊ የአስተራረስ ቴክኒኮችን ተግባራዊ በማድረግ ሀገሪቱ የስንዴ ምርቷንና ለገበያ የሚቀርበውን ምርት መጠን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጋለች።
ይህ ስትራቴጂያዊ ትኩረት ኢትዮጵያን ከስንዴ አስመጪነት ራሷን ወደ መቻል ደረጃ በማሸጋገር የግብርና ፖሊሲዋን፣ ፕሮግራሟን እና ተያያዥ ውጥኖቿን ስኬታማነት አሳይቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት የግብርና ምርትን ለማሳደግ የተለያዩ ውጥኖችን በመተግበር ላይ ይገኛል።
ከነዚህም መካከል፡-
• በመስኖ ላይ የተመሰረተ እርሻን ማስፋፋት - በዝናብ ላይ የነበረውን ጥገኝነትን ለመቀነስ የመስኖ ስርዓቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት።
• ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ግብርና መከተል - የአየር ንብረት ለውጥን ተፅእኖ ለመከላከል ዘላቂ የግብርና ልምዶችን ማበረታታት።
• የግብርና ማሽነሪዎችን ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት - ከ400 በላይ የተለያየ አይነት የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች ከውጭ ከሚገቡት ቀረጥ ነፃ ናቸው፣ ለገበሬዎች ወጪን ይቀንሳል እና ምርታማነትንም አሳድጓል።
• የፖሊሲና የህግ ማሻሻያ - አዲስ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲን ማስተዋወቅ፣ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅን ማሻሻል እና የኮንትራት ግብርና የህግ ማዕቀፎችን በማዘመን የወቅቱን የግብርና አሰራሮችን ማስደገፍ ተችሏል።
• የተሻሻለው የዘር ብዜት ፖሊሲ - የግሉ ሴክተር ተሳትፎን ለማሳደግ የዘር አቅርቦትና ስርጭት የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማሻሻል፣ በዘር ብዜት እና ስርጭት ላይ ሁለገብ ተሳትፎን ጨምሮ፣ የበለጠ ተወዳዳሪ ገበያን መፍጠር።
• ተምሳሌታዊ ኢኒሼቲቮች- ሰፊ ተቀባይነት ያለው የመስኖ ስንዴ ኢኒሼቲቭ፣ የሌማት ትሩፋት እና አረንጓዴ አሻራ ሌጋሲ ኢኒሼቲቭ፣ በምግብ ራስን መቻል እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ዋና ዋና ፕሮግራሞችን መተግበር።
• ግብርናን በክላስተር የማዘመን ስራዎችና የኤክስቴንሽን አገልግሎቶች - የክላስተር ግብርና ልምዶችን ማስፋፋት እና በዓለም ትልቁን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ፕሮግራም ማጠናከር፣ ከ60,000 በላይ የመንግስት ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የተደገፈ የቴክኖሎጂ ማላመድና እና አተገባበርን ማሳደግ።
በስንዴ ምርት ዙሪያ መረጃ እንዴት ይሰበሰባል?
ኢትዮጵያ የግብርናውን እድገት ለመገምገም እና ስልቷን ለማጣራት ጥብቅ የመረጃ አሰባሰብ ሂደት ትከተላለች።
ይህ የሚያጠቃልለው፡-
• የመሬት ዳሰሳ ጥናቶች - በግብርና ባለሙያዎች የሚካሄደው ቅጽበታዊ መረጃን ለመሰብሰብ ነው::
• የግብርና ቆጠራ በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት - ESS ከዳሰሳ ጥናቶች በተጨማሪ በመሬት ሽፋን፣ በሰብል አይነቶች እና በምርታማነት ላይ ለውጦችን ለመከታተል የግብርና ቆጠራ ያደርጋል።
• የአስተዳደር መረጃ አጠቃቀም - አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከሌሎች ሪፖርት አድራጊ ኤጀንሲዎች የተገኙ አስተዳደራዊ መረጃዎች እንደ የመረጃ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ። ነገር ግን፣ እነዚህ አሃዞች እንደ ይፋዊ የመንግስት ስታቲስቲክስ እውቅና ከመስጠታቸው በፊት በሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጥብቅ ቁጥጥር እና ማረጋገጫ ይደረግባቸዋል።
• የርቀት ዳሳሽ እና ምስል ማቀናበር - እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በሩቅ ወይም ተደራሽ ባልሆኑ አካባቢዎች የሰብል ሽፋንን ለመከታተል ጥቅም ላይ ይውላሉ፣ ይህም የግብርና መረጃን ትክክለኛነት እና አጠቃላይነት ያሳድጋል።
ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች ላይ አስተማማኝ ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን የማውጣት የረጅም ጊዜ ባህል ያላት ሉዓላዊ ሀገር ነች።
የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት (የቀድሞው የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ) በአፍሪካ ውስጥ ካሉ አንጋፋ እና ታዋቂ የስታቲስቲክስ ቢሮዎች አንዱ ነው። የውጭ ድርጅቶች የተለያዩ አሃዞችን ሊያቀርቡ ቢችሉም፣ የኢትዮጵያ መንግስት እንደ ሉዓላዊ ባለስልጣን ብቻ የሚመረኮዘው በአገራዊ ስርአቱ በሚመረተው ይፋዊ መረጃ ላይ እንጂ የውጭ አሃዞችን እንደ ይፋዊ ስታስቲክስ አይወስድም።
በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የእቅድ እና ልማት ሚኒስቴር የሰብል ምርት ስታቲስቲክስን ጨምሮ በተጨባጭ ሴክተር አሃዞች ላይ መረጃን የማጣራት የመጨረሻውን ስልጣን ይይዛል።
ኦፊሴላዊ የስንዴ ምርት አሃዞች
• እ.ኤ.አ. በ2022/23 ወቅት - ኢትዮጵያ 151 ሚሊዮን ኩንታል (15.1 ሚሊዮን ቶን) ስንዴ አመረተች።
o 104 ሚሊዮን ኩንታል (10.4 ሚሊዮን ቶን) በመኸር ወቅት
o 47 ሚሊዮን ኩንታል (4.7 ሚሊዮን ቶን) በበጋ መስኖ።
• እ.ኤ.አ. በ2023/24 ወቅት - ኢትዮጵያ 23 ሚሊዮን ቶን ስንዴ አመረተች።
o 12.3 ሚሊዮን ቶን በዋናው የምርት ዘመን ተሰብስቧል።
o 10.7 ሚሊዮን ቶን በበጋ መስኖ በስንዴ ውጥኖች ምርት ተሰብስቧል።
እነዚህ አሃዞች ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ላይ እያስመዘገበች ያለችውን ከፍተኛ እድገት በማሳየት በምግብ እራሷን ለመቻል ያላትን ቁርጠኝነት ያጠናክራል።
ለምንድነው የምግብ ራስን የመቻል አጀንዳ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ አስፈላጊ የሆነው?
የኢትዮጵያ የምግብ እራስን መቻል ሀገራዊ ቀዳሚ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ማጎልበት ወሳኝ እርምጃ ነው። በምግብ ምርት ውስጥ በራስ መተማመኛን ማሳካት ጥንካሬን ያጠናክራል፣ ጥገኝነትን ይቀንሳል እና በአህጉሪቱ ዘላቂ እድገት ለማምጣት መንገድ ይከፍታል። የምግብ እራስን መቻልን ማረጋገጥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ስትራቴጂ መሰረታዊ ምሰሶ ሲሆን ከዳርቻው ባሻገር ሰፊ እንድምታ አለው።
ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የምግብ ምርትን በማረጋገጥ ራሷን ከአለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት መቆራረጥ በመጠበቅ ላይ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ሀገራት የግብርና ነፃነትን ለማግኘት ያላቸውን አቅም እያሳየች ነው።
Henok Abera, [2/19/2025 11:50 AM]
ጉዞው አድካሚና ፈታኝ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ የግብርና ለውጥ ራስን ለመቻል ለሚጥሩ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች አርአያ ሆኖ ያገለግላል። ዘላቂ የግብርና እና አዳዲስ መፍትሄዎችን በማስቀደም ኢትዮጵያ አፍሪካ ራሷን የመመገብ አቅም እንዳላት እና ለመጪው ትውልድ የበለፀገ፣ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ አቅም እንዳላት እያሳየች ነው።
ይህ ኢትዮጵያ የምትኮራበት የብልፅግና ጉዞ ነው!