05/08/2024
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወደ ሁለት የአውሮፓ ሀገራት ዜጎችን ለስራ ስምሪት ለመላክ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ገለፀ!.
ሐምሌ 29/2016).
የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም የሚያስጥብቅ እንዲሁም በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ብቻ ሳይወሰን የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪትን የሚያካትት እና የዘመነ አገለግሎት እንዲሆን ባስቀመጥነው የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት ወደ አውሮፓ (Sweden and Norway) ገበያ ለመግባት ቀደም ብሎ በተጀመረ ጥረት የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት የተጠየቁ የሞያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው።
1- ካርዲዬሎጂስት
2- የማርኬቲንግ ባለሙያ
4- ኬሚካል ኢንጅነር
5- ባስ ድራይቨር
6- አርክቴክት
7- አካውንታን
8- አውቶሞቲቭ ቴክኒሽያን ባለሙያ
9- የላብራቶሪ ቴክኒሺያን
10- የአይ ቲ ባለሙያ
11- የፋርማሲ ባለሙያ
12- የሽያጭ ባለሙያ
13- የሶፍትዌር ባለሙያ
14- ሜዲካል ዶክተር
15- የኮምፒተር ጥገና ባለሙያ
16- ነርስ
17- ግራፊክስ ዲዛይነር
18- የፀጉር ባለሙያ
19- የደንበኛ አገልግሎት ባለሞያ
በመሆኑም አስፈላጊውን ስልጠና እና ሌሎች መመዛኛዎችን በሟሟላት የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ዜጎች በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (https://lmis.gov.et) በመመዝገብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቀርቧል።