Habtom Gidey

Habtom Gidey እግዚአብሔር ታላቅ ነው🙏🙏🙏
ጤና ትልቅ ሀብት ነው።

10/04/2024

✍️ ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቀው ዘውትር ቢጠጡ እነዚህን 10 የጤና ጥቅሞች ያገኛሉ🔬🔬🔬🔬🔬

1. ጉበቶን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳሉ፡፡ለብ ባለ ውሃ ውስጥ የሎሚውን ጭማቂ (ፈሳሽ) ብቻ ሳይሆን የሎሚው ልጣጭ ጭምር ከተን የምንጠጣ ከሆነ ደረጃ 2 የጉበት ፀረ- መርዝ ማስወገድ ተግባራን ያከናውናል፡፡

2. ጉበቶ ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባታማ ምግቦችን ሰውነቶ እንዲፈጭ ይረዳል፡፡

3. ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳታችን(cells) እንዳይወድሙ ይጠብቃቸዋል፡፡

4. በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- ኦክሲደንት እና ፌቶኬሚካልስ የጉበት ሕዋሳት እንዲታደሱ ይረዳል፡፡

5. በሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የምግብ ስርዓተ ልመትን ያፋጥናል እንዲሁም የኩላሊት ጠጠርን (kidney stone) ያሟሟል፡፡

6. ሎሚ ከሰውነት ውጭ አሲድ ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ አልካላይን ነው ስለሆነም በሰውነት ውሰጥ ያለውን የፒ ኤች ደረጃ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳል በተጨማሪም በሽታን ይከላከላል፡፡

7. በሎሚ ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ጠንካራ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከል አቅም እንዲኖረን ያስችላል፡፡

8. ሎሚ የደም ቅባትን በመሰባበር በዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሀሞት ድንጋይዎች(gall stones) በሰውነታችን ውስጥ እንዳይፈጥር ያግዛል፡፡

9. ሎሚ ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ስላላው የዩሪክ አሲድ መጠንን በመቀነስ ሰዎች በሪህ (Gout) እና የአጥንት አንጓ

10. ብግነት (Arthritis) እንዳይጠቁ ይጠብቃቸዋል፡፡

11. ሎሚ ከአንደንድ የካንስር በሽታዎችም ይከላከላል፡፡
መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ!!!!
👉ምንጭ:- Hakim-bet.com

02/03/2024

ከቁጥጥር ቀጠናችሁ ውጪ የሆኑት ነገሮች ጉዳይ!

ለማድረግም ሆነ ለመለወጥ ስለማትችሏቸውና ከእናንተ የቁጥጥር ቀጠና ውጪ ስለሆኑት ነገሮች መጨነቅ ቀናቸሁን በመፍዘዝ፣ ማታቸሁን ደግሞ እንቅልፍ በማጣት እንድታሳልፉ ያደርጋችኋል፡፡

ከእናንተ የቁጥጥር ቀጠና ውጪ ስለሆኑት ነገሮች መጨነቅ አቁሙና ማድረግና መለወጥ በምትችሉት ነገር ላይ በማተኮር ያንን በሚገባ መወጣታችሁን እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ከእናንተ አቅምና የቁጥጥር ቀጠና ውጪ የሆኑት ነገሮች በመጨነቅ አይስተካከሉም፡፡ እነሱን ልክ የሚያስገባቸው በቁጥጥራችሁ ስር የሆኑትን ነገሮች በትኩረት፣ በብርታትና በደስተኛነት ከግባቸው ለማድረስ ወደፊት የመገስገሳችሁ ጉዳይ ነው፡፡

መልካም እንቅልፍ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

23/02/2024

✍️ አስም በሽታ ምንድን ነው???
አስም በዘላቂነት የመተንፈሻ ቱቦዎችንና የሳንባን መተላለፊያ በማጥበብ እንዲሁም ብዛት ያለውን አክታ በመፍጠር የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ህመም ነው፡፡

👉 የአስም በሽታ በ አለም ላይ ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች አንዱ ነው ። እንደ አለም ጤና ድርጅት መረጃ በ 2016 ከ 339 ሚልየን በላይ ሰዎች የአስም በሽታ እንዳለባቸው ያሳያል። በአመት ውስጥ እስከ 417,918 የሚደርሱ ሰዎች በአስም ምክንያት እንደሚሞቱ የ አለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።
👉 አስም ሙሉ ለሙሉ የሚድን በሽታ አይደለም፤ ነገር ግን የሚያመጣቸውን ምልክቶች ተገቢውን የህክምና ክትትል በማድረግ መቆጣጠር ይቻላል፡፡

📌 የአስም በሽታ ምልክቶች??👉 ክፍል 1

👉 ድምፅ ያለው አተነፋፈስ (ፉጨት መሰል)
ደረቅ ሳል ደረት ላይ የመጫን/የመውጋት ስሜት
ትንፋሽ ማጠር/ለመተንፈስ መቸገር የህመሙ ምልክቶች ወቅቶችን ጠብቀው የሚመጡና የሚጠፉ ናቸው፤ በተለይም ክረምቱ አልፎ መስከረምና ጥቅምት ሲመጣ ይበረታሉ፡፡ የአስከፊነት ደረጃቸውም ከመጠነኛ ሳል እስከ መተንፈስ አለመቻል የሚያደርስ ሲሆን አልፎ አልፎም እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡

📌 የአስም በሽታ እንዴት ይከሰታል??

👉 አስም ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች የሚመደብ ሲሆን ለምን አንዳንድ ሰዎችን አጥቅቶ ሌሎችን እንደማይይዝ እስካሁን መናገር አይቻልም፡፡ ነገር ግን አካባቢያዊ ሁኔታዎችና በዘር የሚተላለፉ ነገሮች በአንድ ላይ ለአስም ተጋላጭ እንደሚያደርጉ ይታመናል፡፡ አስም በየትኛውም የዕድሜ ክልል ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡

👉ለአንዳንድ ሰዎች አስም ከተወሰኑ ሁኔታዎች ጋር ብቻ ተያይዞ ሊከሰት ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡-

🔥ከአካል ብቃት እንቅስቀሴ ጋር ተያይዞ የሚነሳ አስም

🔥ከሥራ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚነሣ አስም
በአለርጂ ምክንያት የሚነሣ አስም የመሳሰሉት ።
ለብዙዎች እንዲደርስ እባክዎ ሼር ያድርጉ...ክፍል 2......

09/02/2024

✍️ የፊት ማፅጃ በቤት ውስጥ
*************************

🔥 ስኳር እና ማር 🍝🍝🍝

👉 #አዘገጃጀት ፡-
1 ማንኪያ ስኳር እና 2 ማንኪያ ማር
ለመቀባት አመቺ እስኪሆን ድረስ ማዋሃድ በንጹህ ፊት ላይ መቀባት እና ለ3 ደቂቃ ማሳጅ ማድረግ እና በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ፤ይህንን የፊት ማጽጃ በየሁለት ቀኑ በመጠቀም ፊታችን ላይ ልዩነቱን ማየት እንችላለን፡፡

🔥 ፓፓያ🍋🍋🍋

👉 #አዘገጃጀት ፡-
የበሰለ ፓፓያ በጁስ መልክ ማዘጋጀት ፊታችንን በመቀባት ከ10-15 ደቂቃ ማቆየት እና ለብ ባለ ውሃ መታጠብ፤ ይህንን በሳምንት 1 ጊዜ መጠቀም።

🔥የሙዝ ልጣጭ 🍌🍌🍌

👉 #አዘገጃጀት ፡-
1 የሙዝ ልጣጭ በማዘጋጀት የውስጠኛው ክፍሉን በማንኪያ በመፋቅ ማውጣት የፈቀፈቅነውን በንጹህ ፊት ላይ መቀባት እና ትንሽ አቆይቶ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ፤ ይህንን በሳምንት 3 ጊዜ መጠቀም።

🔥ቲማቲም🍎🍎🍎

👉 #አዘገጃጀት ፡-
1 የቲማቲም ጁስ ማዘጋጀት ወተት እና የሎሚ ጭማቂ ከተፈጨው ቲማቲም ጋር ማደባለቅ፤ ይህንን በሳምንት 2 ጊዜ መጠቀም።

📌 የፊቶት ቆዳ ደረቅ ከሆነ ለብ ባለ ውሃ አይታጠቡ።
# በቅንነት ሼር ያድርግሉን!!!

08/02/2024

✍️የምንወስዳቸው #ጁሶች #ከጤናችን #ሁኔታ #ጋር!!!

💥 ለጉንፋን ፡- የካሮት፣ የአናናስ፣ የዝንጅብል እንዲሁም የነጭ ሽንኩርት ጁስ

💥 ለራስ ምታት ፡- የአፕል፣ የኩከንበር ጁስ

💥 ለደም ግፊት፡- የቀይ ስር ጁስ፣ የአፕል፣ የኩከንበር ጁስ

💥 ኩላሊት #ለማጽዳት፡- የካሮት፣ የሃብሀሃብ፣ የኩከንበር ጁስ

💥ለአይን፡- የካሮት ከጁስ

💥 ለሆድ ድርቀት፡- የካሮት፣ የአፕል፣ የትኩስ (fresh) ጎመን

💥 ለስኳር ህመም፡- የካሮት፣ የስፒናች ፣ የሃብሃብ ጁስ

?? ለኩላሊት #ጠጠር፡- የብርቱኳን ፣ የአፕል፣ የሃብሃብ፣ የሎሚ ጁስ
💥ለጭንቀት፡- የሙዝ፣ የስተሮበሪ ጁስ
💥 ለምግብ አለመፈጨት፡-የአናናስ፣ የካሮት፣ የሎሚ እንዲሁም የሜንት።
♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

04/02/2024

👉የጭንቅላት ካንሰር(Brain Cancer)
ምንድነው???
✍️ በአመት በካንሰር ምክንያት ከሚሞተው ሰው በጭንቅላት ካንሰር ብቻ 3% የሚያህሉቱ ህይወታቸውን ያጣሉ። ብዙ አይነት የጭንቅላት እጢዎች አሉ የተወሰኑቱ በፍጥነት ሲያድጉ የተወሰኑቱ ደሞ በዝግታ ያድጋሉ::

✍️ የካንሰር ሴሎች ቁጥራቸው ሲጨምርና በመጠንም ሲያድጉ ወደ ጤነኛው ሴል ይዛመታሉ::በተጨማሪ ጭንቅላት ውስጥ እብጠት በመፍጠር ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል::

📌 የጭንቅላት ካንሰር ምልክቶቹ ምንድናቸው?

💥 ብዙ ጊዜ የመጀመሪያው ምልክት ሰውነት #ማንቀጥቀጥ(seizure) ነው::

💥 ከማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ጋር የሚከሰት ተደጋግሞ የሚመጣ #ራስ ምታት።

💥 የ ዕይታ ለውጥ ፦ የምስል መደብዘዝ እና ለእይታ መቸገር

👉 የማስታወስ ችሎታ መቀነስ

👉 የሰውነት መስነፍ(paralysis)

👉 የባህሪይ ለውጥ ማምጣት

📌 ለጭንቅላት ካንሰር የሚሆን ምርመራ አለ?

🔬 ኢሜጂንግ ከምንላቸው ውስጥ እንደ MRI እና CT SCAN በብዛት በሽታውን ለመለየት እንጠቀማለን::እንዲሁም ከ ኢሜጂንግ በኋላ እንደየ አስፈላጊነቱ የናሙና(Biopsy) ምርመራ ይደረጋል::

📌 የጭንቅላት ካንሰር ህክምና አለው?

👉 የተለያዩ የህክምና ዘዴዎች አሉት ከነዚህም ውስጥ ቀዶ ጥገና ፣ የጨረር ህክምና፣ ኬሞቴራፒ ይጠቀሳሉ።

ከ ህክምና በኋላ ምን መደረግ አለበት?

💥የካንሰር ሴሎቹ ድጋሚ እንዳይከሰቱ የህክምና ክትትል ያስፈልጋል::እንዲሁም በተጨማሪ ከሃኪሙ የሚሰጡትን የትኛውንም መልክት እና ትዕዛዝ መተግበር አስፈላጊ ነው::

✍️ እነዚህ ምልክቶች ከታዩ በቀላሉ በሽታው ስር ሳይሰድ የጤና ባለሙያዎችን ማማከር ብልህነት ነው::
ለብዙዎች እንዲደርስ እባክዎ ለወዳጅ ጓደኛዎን ሼር ያድርጉ!!!

04/02/2024

📃ስድሰት ​ነገሮች ሁሌም ማስታወስ ያለብህ....✍️

📌 ያለፈውን ነገር መለወጥ አይቻልም።

📌የምትወድቀው ካቆምክ ብቻ ነው።

📌 አንዳንድ ጊዜ "አይሆንም" ማለት "ለአሁን
አይሆንም" ማለት ነው።

📌 የነሱ አስተያየት የአንተን እውነታ አይገልጽም።

📌 ደስታ የሚገኘው ከውስጥህ ነው።

📌 ሁሉም ነገር ጊዜያዊ ነው።

መልካም ሰንበት🙏🙏🙏🙏

✍️Version of yourself
04/02/2024

✍️Version of yourself

03/02/2024

Address

Addis Ababa
Mekelle

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habtom Gidey posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category