06/01/2026
የገና በዓል ፍቅርን፣ አንድነትን፣ መተሳሰብን፣ የአብሮነት እሴቶችን በተግባር የምናሳይበት ነው በማለት እንኳ ለብርሃነ ልደት በሠላም አደረሳችሁ በማለት የዳውሮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ተረፈ ገልጸዋል
የዳውሮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መላኩ ተረፈ ለመላው ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በልዩ መንፈሳዊ ሥነ ስርዓት የሚከበር ክብረ በዓል ነው ብለዉ የገለጹት አቶ መላኩ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች የማያልቅና ፍጹም የሆነ ፍቅርን፣ አንድነትን መረዳዳትን እና መደጋገፍን እንዳስተማረን ሁሉ ህዝበ ምዕመናን በዓሉን ሲያከብሩ አቅመ ደካማ ወገኖቻችንን በማሰብ፣ ያለንን በማጋራትና የአብሮነት እሴቶቻችን በተግባር በማሳየት ሊሆን ይገባል ሲሉ አቶ መላኩ ገልጸዋል።
በዓል የፍቅር እና የአንድነት በመሆኑ ምዕመኑ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ኢየሱስ ክርሰቶስ ያሳየውን ተምሳሌትነት ሊተገብር ይገባል በማለት በዓሉ የብልጽግና፣ የደስታ፣ የፍቅር ፣ የሠላምና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
መልካም የገና በዓል!