Jone sufyan

Jone sufyan Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jone sufyan, Grocers, Harari, Harar.

17/10/2026
17/10/2026
17/10/2026

በሀረሪ ክልል ባለፉት ሣስት ወራት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

በሀረሪ ክልል ባለፉት ሦስት ወራት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱለሂ በክልሉ በበጀት ዓመቱ ሦስት ወራት 1 ቢሊየን 13 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ1 ቢሊየን 202 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

ገቢው የተሰበሰበው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች እና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ መሆኑን አብራርተዋል።

ባለፉት ሦስት ወራት የተሰበሰበው ገቢም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ375 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ጠቁመው ይህም ከ45 በመቶ በላይ እድገት ያለው ገቢ መሰብሰብን ገልጸዋል።

የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር መሻሻል; ፍትሃዊ የታክስ ተደራሽነት እና አሰተዳደርና አመራር ትግበራ መሻሻል; የግብርና ገቢ አሰባሰብ አገልግሎት አሰጣጥና ቴክኖጂ አጠቃቀም መሻሻልና የግብር ከፋዪ ህብረተሰብ ግብርን በታማኝነት አሳውቆ እና የመክፈል ባህል በየጊዜው እየተሻሻለ መምጣቱ በገቢ አሰባሰቡ ሂደት እና ውጤት ላይ የላቀ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው ኃላፊው አስገንዝበዋል። በውጤቱ እያደገ ያለውን የህብረተሰብ የልማት እና መልካም አስተዳደር ፍላጎት በተሻለ ደረጃና አቅም ለመፈፀም እንደሚያስችልም አንስተዋል።

በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚሰበሰበው ገቢ እያደገ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ገቢን አሟጦ ከመሰብሰብ አንፃር እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላል ብለዋል።

ክልሉ በ2019 የበጀት ዓመት 6 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

Address

Harari
Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jone sufyan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category