Kelifa hasen

Kelifa hasen Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kelifa hasen, Grocers, Zerihun Yohans, Harar.

08/04/2024
08/04/2024
08/04/2024
08/04/2024

በሀረሪ ክልል የኢድ-አልፈጥር በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የኢድ-አልፈጥር በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ነው የገለጸው፡፡

የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስሪ ዘከርያ እንደገለጹት ይህ ታላቅ ክብረ በዓል በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከሚመለከታቸው አካላት የጸጥታ አካላት ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር በርካታ የፀጥታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል።

የበአሉ በሚከበርባቸው ቦታዎችም አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያካሂድ ጠቁመው ምእመናኑ ወደ መስገጃ ስፍራ እንደልብ እንዲንቀሳቀስ ለማስቻል የትራፊክ እንቅስቃሴን በመገደብ አማራጭ መንገዶች መዘጋጀታቸውንም ነው የገለጹት።

በአሉ የሰላምና የአንድነት በአል እንዲሆንም ኮሚሽነሩ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

06/04/2024

በሀረሪ ክልል ከለውጡ በኋላ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በሌሎችም መስኮች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል - አቶ ሔኖክ ሙሉነህ

በሀረሪ ክልል ከለውጡ በኋላ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በሌሎችም የልማት መስኮች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ገለጹ።

የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እንደገለጹትመጋቢት ወር የኢትዮጵያ የመለወጥ ፍላጎት እውን የሆነበትና የብልፅግና ጉዞ የተጀመረበት ወር ነው ብለዋል።

በፖለቲካ ረገድ ከለውጡ በኃላ በክልሉ ከሴራ ፖለቲካ ወደ መርህ ፖለቲካ፣ ከመገፋፋትና ከጥላቻ ወደ ሰላምና አብሮነት እንድንሸጋገር አድርጎናል ብለዋል።

በኢኮኖሚ ረገድም በግብርና እና በቱሪዝም ልማት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል።

በማህበራዊ ልማት ዘርፍም የትምህርት ጥራት ከማጎልበትና የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንጻር የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን ሃላፊው ገልጸዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የክልሉ ህዝብ በላቀ ተነሳሽነት ተሳትፎና ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል።

በመሆኑም በክልሉ በነገው እለት ከለውጡ ወዲህ የተገኙ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

''ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን'' በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ነገ ከጠዋቱ 1:00 ሰአት ጀምሮ በኢማም አህመድ ስታድየም መሆኑን ተናግረዋል።

Address

Zerihun Yohans
Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kelifa hasen posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category