Bekele Bale

Bekele Bale Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bekele Bale, Grocers, Gambela.

25/12/2025

ሁሉም የጊደታውን ቢወጣ ዛሬ ሀገሪቱ የት በደረሰች

25/12/2025

ኢትዮጵያ ለሎች ባለሰለጠኑባት ግዜ ሰልጥናለች፣
ለሎች በቀኝ ገዥዎች ስገዙ አልተገዛችም፣
አሁን ታረኳ ተገልብጠው በባለስልጣን፣በባለገንዘብ እንገዛለን ፣እርስ በእርስ እንባላለን፣መቆሚያ የለለ ወደሆነው የበቀል ጥላቻ ውስጥ ገብተናል።

እኔ እንኳን ብዙ ነገር ለመናገር አይደለም ሰሞኑ በቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር  ሀይለማርያም ደሳለኝ ላይ እየተባለ ያለው የጥላቻ እና የውንጀላ ንግግር መልስም አልሰጥም ።የህ ግለሰብ መወዳደሩ አ...
16/12/2025

እኔ እንኳን ብዙ ነገር ለመናገር አይደለም ሰሞኑ በቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ላይ እየተባለ ያለው የጥላቻ እና የውንጀላ ንግግር መልስም አልሰጥም ።የህ ግለሰብ መወዳደሩ አይቀረም የሚወዳደረው በአለም መድረክ ነው።ትዝ ካላችሁ የአለም ጤና ድርጅት ዶ/ር ተዎድሮስ አዳኖም እንድህ አይነት ውንጀላ ነበር በወቅቱ ከትግራይ ጋር በነበረው የእርስበርስ ጦርነት ላይ ተሳትፎ አድርጓል በምል ከመንግስት ጭምር የተለያዩ ነገሮች ስደረግ ነበር ነገር ግን ያው ውጤቱን አይታችኋል ።አንድ ኢትዮጵያዊ እንድህ ባለ መድረክ አይደለም መወዳደር ማዬት ለራሱ ምን ያክል ከፊታ ነው።እስክ ንፉግ አንሁን።ከቻላችሁ መደገፍ አልያ ዝም በሉ አለም ምን ያክል እንደምትታዘብ እንደ ሰው እንኳን አድርጎ አይቆጠሩም ።ይመቸው ሊቀመንበርነቱን ተረክበው እንደማይ እርግጠኛ ነኝ።ይመቸው።

16/12/2025

በቀጣዩ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊነት ይጠብቁ !! እውቀት ያለው የትም ተጠርተው እየተፈለገ በክብር ይሰራል! በፅንፈኞቹ ዘመቻ የማይሰበረው የግዙፉ ስብዕና ባለቤት!

የአገር መሪ ሆነው ከስልጣን ከተነሱ በኃላ ቀጥሎ የመጣውን መንግስት መውጋት ባህል ባደረገበት አፍሪካ ላይ በተቃራኒው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው በሰላማዊ መንገድ ከለቀቁ በኋላ እስከ አለም አቀፍ ደረጃ ያከናወኗቸው ቁልፍ ተግባራት በጥቂቱ 👇

👉 ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ቦርድ አባል። እ.ኤ.አ ከ2022 ጀምረው፥

👉 የአፍሪካ ዋይልድላይፍ ፋውንዴሽን የትረስት ቦርድን አባል ሆነው ተመረጡ። እ.ኤ.አ ከ2021 ጀምረው፥

👉 የአፍሪካን ዋይልድላይፍ ፋውንዴሽን የግሎባል ትረስት ቦርድ አባል። እ.ኤ.አ ከ2022 ጀምረው፥

👉 በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ በአለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃን በማሳደግ እና #የአፍሪካ ድምጽን በመወከል መሳተፍ እ.ኤ.አ ከ2021፥

👉አሊያንስ ፎር ኤ ግሪን ሪቮሉሽን አፍሪካ (ኤጂአርኤ) የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት ሊቀመንበር፣

👉 የትሬድማርክ አፍሪካ ቦርድ ሰብሳቢ እ.ኤ.አ ከ2025 ጀምረው፥

👉 የታንዛንያ ፕሬዝደንታዊ ከፍተኛ ምክር ቤት አባል በመሆን በሀገሪቱ ፕረዚዳንት ተሹመው እ.ኤ.አ ከ2023 ጀምረው፥

👉 በመላው አፍሪካ ያሉ የአስተዳደር፣ የአመራር እና የፖሊሲ ጉድለቶችን መፍታትን አላማ ያደረገው የመጀመሪያው ተቋም ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር አቋቋመው ወደ ስራ ያስገቡ፥

👉 በጃፓንና በአፍሪካ ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር ላበረከቱት አስተዋፅኦ እስፕሪንግ ኢምፔሪያል የተባለውን ጃፓን ለውጪ ዜጎች የምትሰጠው ሽልማት የተቀበሉ፣

👉 በአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ በዓለ ስመታቸው የአፍሪካ ልዑካንን በመምራት እንዲገኙ ተጋብዘው በብቸኝነት በክብር የተጋበዙ፣

👉 የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክ ንግድ ቡድን (The A-eTrade Group) የበላይ ጠባቂ ሆነው መሾም። እ.ኤ.አ ከ2021 ጀምረው፥

👉 የወቅቱ የትሬድማርክ አፍሪካ የቦርድ ሰብሳቢ በተጨማሪ ከእ.ኤ.አ 2019 ጀምሮ የግዙፉ በአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ጥምረት (AGRA) የቦርድ ሊቀመንበር፥

👉 መቀመጫውን ብራሰልስ ቤልጂዬም ያደረገ አንድ ታዋቂ በሰላምና የሰላማዊ ስልጣን ሽግግር ላይ የሚሰራው ድርጅት ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ በራስ ፍቃድ ሥልጣን ያሸጋገረ የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ" በማለት ዕውቅና የተቀበሉ፣

👉 እ.ኤ.አ 2018 ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ ከለቀቁ በኃላ ከባለቤታቸው ከቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር በመሰረቱት ትልቅ ፋውንዴሽን አማካይነት የተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ ተጨባጭ ስራ እየሰሩ የሚገኙ፣

👉 የአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ለውጥ ተነሳሽነት (ACCI) መሪነት አማካይነት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰቱትን ችግሮች ለመቋቋም፣ ለምሳሌ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የምግብ ዋስትና እጦት፣ የሚያስችሉ የፖሊሲ ማዕቀፎችን እንዲያዘጋጁና እንዲተገብሩ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ የሚገኙ፣

👉 የተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋሮችን በማስተባበር የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የአቅም ግንባታ እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት ያደረጉ፣

👉 በአፍሪካ ቀጠና በተለይም በአጎራባች ሀገራት የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ፣

👉 ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ ካስረከቡ በኃላ ባቋቋሙት ፋውንዴሽን አማካይነት በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ለኢትዮጵያ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት በሚረዱ ጉዳዮች ላይ እውቀታቸውን በማካፈል ተጨባጭ ተግባር ላይ ይገኛሉ።

👉 በተለይም የአፍርካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፍትሔ ማግኘት አለበት፣ የአፍሪካውያን ዕድገት ዕድል በእውቀት ላይ በተመሠረተ በአፍሪካውያን አንድነትና መተባበር ውስጥ ይገኛል የሚለውን የፀና አቋማቸው በተለያዩ መድረኮች እያንፀባረቁ የሚገኙ፣

👉 በየጊዜው ዋጋው እየጨመረ የሚገኘው እውነተኛ ማንነት ባለቤት፣ በርካታ መሪዎች በስልጣን ሙጭጭ ብለው ለማድረግ ያልደፈሩትን በተግባር ያሳየ፣ ተግባሩንም በመኖር እያሳየ የሚገኝ፣ የወጣበት ማህበረሰብ እሴትን እንዲሁም ፈጣሪንም ስልጣን ላይ ተጨማልቀውና ከህዝብ ሰርቀው ያላስነቀፉ የህያው ታሪክ ባለቤት የሆኑት እንደሆነ በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉ።

👉 በአፍሪካ ቀጠና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት፣ በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በመሳተፍ በአፍሪካ ቀጠና የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ የሚገኙ፣

👉 ከፖለቲካ ተሳትፈው በተጨማሪ ትውልድ በመልካም ስብዕና እንዲገነባ እንዲሁም እውነተኛ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲከተል የወንጌል አገልግሎት እንዲሰጡ ከኢትዮጵያ ከሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ህጋዊ የቅስና ማዕረግ ተሰጥትዋቸው የተለያዩ አለማት በመዞር እያገለገሉ የሚገኙ፣

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት በኋላ፣ በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የአስተዳደር፣ የሰላም፣ እና የልማት መሪ ሆነው እንዲቀጥሉ የቻሉት፣ በሰላማዊ ሽግግር ወቅት ያሳዩት ምሳሌያዊ አመራር እና ለህብረተሰቡ ያላቸው ቁርጠኝነት ሲሆን፣ ይህም በተለያዩ የአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ያላቸው እንቅስቃሴ በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን በሰላማዊነት፣ በሀገራዊ አንድነት፣ እና በአፍሪካዊ ወኪልነት ላይ ያተኮረው ርብርብ፣ ለወደፊት ትውልድ የሚተርፍ ታሪካዊና በምሳሌያዊነት የዘለቀ ይሆናል።

እናም ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ|ን በቀጣዩ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊነት ይጠብቁ !! እውቀት ያለው የትም ተጠርተው እየተፈለገ በክብር ይሰራል! በፅንፈኞቹ ዘመቻ የማይሰበረው የግዙፉ አለምአቀፍ ስብዕና ባለቤት ነውና !

02/12/2025



የዚህ ማኅበረሰባዊ ዕይታ የዳሰሳ ጥናት መሠረታዊ ዓላማ

አሁን በሀገራችን እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር፤

👉 በሀገሪቱ በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ፣ መረጋጋትንና ሀገራዊ እድገትን ለማምጣት የሚያስችል ስለመሆኑ

👉 አሁን ያለውን የፖለቲካ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ ችግሮችን መፍቻ ቁልፍ ስለመሆኑ፤

👉 ሀገራዊ ምክክሩ አካታች (የሁሉም ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎችን፣ ማኅበረሰባዊ ተቋማትን እና ሌሎችም የተወከሉበት ስለመሆኑ እና

👉 በሀገራዊ ምክክሩ ሒደት ውስጥ ማኅበረሰቡ በንቃት መሳተፍ አለመሳተፉን ለመመልከት

በሀገር አቀፍ ደረጃ ማኅበረሰባችን ያለውን አመለካከት ለመዳሰስና ከውጤቱ በመነሳት የኢዜማ ሀገራዊ ምክክር አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚወስዳቸው ግብረመልሶች ግብዓት የሚሆን መረጃ ማቅረብ ነው፡፡

ከዚህ በመነሳት እርስዎም የዚህ የዳሰሳ ጥናት አካል በመሆን ግዴታዎትን እንዲወጡ ተጋብዘዋል፡፡ መጠየቁን ሞልተዉ ሲጨርሱ “SUBMIT” የምትለዉን ቁልፍ ሲጫኑ መረጃዉ ወደ መረጃ ቋታችን የሚገባ ይሆናል።

ማስፈንጠሪያውን በመጫን መጠይቁን ይሙሉ፤ ለትብብርዎ እናመሰግናለን!!

https://ee.kobotoolbox.org/x/Rhg9bpF0

21/11/2025

ምኑ ግራ የገባን ማህበረሰብ ነን ግን ባለፉት 30 እና ከዛ በላይ አመታትን ሀገራችን የትምህርት ስረዓት የገደለውን ትውልድ ያሁኑ እንደ ህዳር አህያ ማንም ስጋልብ እያየን ችግሩ የት ጋር እንዳለ እንኳን ያየ የለም።ሁሉም መንግስት ፣መንግስት እያለን ስንጮህ ነበር መንግስ ደግሞ ብዙ ችግሮች በኖረበትም ቀዳሚ የሚሆነው በትምህርት እንደሆነ አምኖ በትውልድ ላይ መሰራት እንዳለበት ይህን ከታች የምንመለከተውን አቅጣጫ በመያዝ ወደ ስራ ገብቷል።ምኑን እንደምንቃወም እንኳን ማወቅ አቃተን ።እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን ።
በተማሪዎች አለባበስ፣
በሞባይል አጠቃቀም፣
በትምህርት ቤት ውስጥ በሚደረጉ ጭፈራዎች
እና በትምህርት ቤቶች ዙሪያ ባሉ ንግዶች ላይ አዲስና ጥብቅ መመሪያ አወጣ::

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶችን ሥነ-ምግባር እና የመማር ማስተማር ሂደትን ለማሻሻል አዲስ የረቂቅ መመሪያ ያዘጋጀ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት የሚከተሉት ክልከላዎች ተቀምጠዋል፡፡
1. የተማሪዎች አለባበስ እና ራስ አጠባበቅ ላይ የተጣሉ ክልከላዎች (በተለይ ለሴቶች)፡-

ማንኛውም ዓይነት የመኳኳያ (ሜካፕ)፣ የጥፍርና የከንፈር ቀለም፣ እንዲሁም ቅንድብ መቀንደብ ተከልክሏል፡፡

አርቴፊሻል ፀጉር (ዊግ) መቀጠል አይቻልም፤ ተፈጥሮአዊ ፀጉር ብቻ ይፈቀዳል፡፡

የሴቶች የደንብ ልብስ (ቀሚስ) ርዝመት ከጉልበት በታች መሆን አለበት፡፡

በሰውነት ላይ ንቅሳትን ማድረግ ወይም አሳይቶ መገኘት ያስቀጣል፡፡
2. በትምህርት ቤት ውስጥ የተከለከሉ ነገሮች፡-

ማንኛውም ተማሪ ሞባይል ስልክ እና የሙዚቃ ማዳመጫ ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ማስገባት አይችልም፡፡

እንደ "ክሬዚ ዴይ"፣ "ቫላንታይን"፣ "ከለር ዴይ" እና የመሳሰሉ የውጭ ባህል ያላቸውን በዓላት ትምህርት ቤት ውስጥ ማክበር በጥብቅ ተከልክሏል፡፡

ማንኛውም የፖለቲካ እና የኃይማኖት እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም ምልክቶችን ይዞ መገኘት አይፈቀድም፡፡
3. በትምህርት ቤቶች ዙሪያ (በ500 ሜትር ራዲየስ)
የተከለከሉ ንግዶች፡-
የትምህርት ቤት አካባቢን ከረብሻ ነፃ ለማድረግ የሚከተሉት ተቋማት ከትምህርት ቤቶች ቢያንስ 500 ሜትር መራቅ እንዳለባቸው ረቂቁ አዘዞል፡-

የጫት፣ የሺሻ እና የአልኮል መሸጫዎች

ፑል፣ ጆተኒ፣ ፕሌይ ስቴሽን፣ እና ፊልም ቤቶች (DSTV)

የእንግዳ ማረፊያዎች እና ማሳጅ ቤቶች
ቅጣቱ ምንድን ነው?
ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በተደጋጋሚ የዲሲፕሊን ጥፋት ካጠፉ እንደ ጥፋቱ ክብደት እስከ 1 ዓመት ከትምህርት ሊታገዱ እንደሚችሉ መመሪያው አስቀምጧል፡፡
>>ይህ አሁን ምን ተቃውሞ ያስነሳል?

02/11/2025

በዚህች በትንሹ ያስደሰተን ጌታ ክብሩን ጠቅልሎ ይውሰድ

Address

Gambela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bekele Bale posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category