Aysha ahmed

Aysha ahmed Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aysha ahmed, Grocers, Dire Dawa.

12/11/2026

በመደመር እሴቶች በመጽናት ፈተናዎችን በድል ተሻግረናል፤ አሁን ደግሞ ክልላችንንና ህዝባችንን ወደ ታላቅ የብልፅግና ከፍታ የምናደርስበትን ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን።"

አቶ ኦርዲን በድሪ
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

12/11/2026
12/11/2026
12/11/2026
12/11/2026

"በክልሉ ከህዳር 3 እስከ ህዳር 27 ድረስ አለም አቀፍ ፀረሙስና ቀን በተለያኑ የንቅናቄ ስራዎች ይከበራል"- የሀረሪ ክልል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን

ሀረር፣ ህዳር 3/ 2019 (ሀክመኮ) በሀረሪ ክልል ከህዳር 3 እስከ 27 / 2019 ድረስ አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በተለያዩ የንቅናቄ ስራዎች እንደሚከበር የክልሉ ስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ገለፀ።

አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የሀረሪ ክልል ስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወሒብ በድሪ የፀረ ሙስና ቀን መከበር በመልካም ስነምግባር ግንባታና ሙስናን በማጋለጥ ሂደት ሰፊ ንቅናቄ የመፍጠር አላማ ያለው ነው ብለዋል።

የፀረሙስና ቀን በአለም ለ23ኛ ጊዜ በሀገራችን እና በሀረሪ ክልል ደግሞ ለ22ኛ ጊዜ "ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፣ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር አስታውቀዋል።

መሪ ቃሉ የተመረጠበት ምክንያትም ሙስና ሁሌም በትስስር የሚፈፀም፣ የማስፈፀም አቅም ባላቸውና በተለያየ ደረጃ በሚገኙ አካላት ትስስር የሚካሔድ ሀገር ገዳይ አስከፊ ተግባር በመሆኑ ነው ብለዋል።

ለዚህም ስውር ትስስሮችን በማጋለጥና በመበጠስ ሙስናን ለመከላከልና የሙስና ወንጀል ፈፃሚዎችን በህግ ለመጠየቅ የሚያግዝ ህዝባዊ ተሳትፎን የሚያጠናክር ንቅናቄ ማካሔድ፣ ግልፅነት፣ ተጠያቃነትና ህጋዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል።

የተተኪ ትውልድ ስነምግባርና ግንዛቤ ላይ በመስራት ግብረገብነትን የተረዳ ዜጋን ማፍራት ግብረገብነት በጎደላቸው ሀላፊዎች የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ሁነኛ መሳሪያ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

ህዝቡን፣ የመንግስት ተቋማትን፣ የፀጥታ አካላትን እና የመገናኛ ብዙሐንን በጋራ በማቀናጀት ሰፊ የንቅናቄ ስራ ማካሔድ ይገባልም ብለዋል።

በክልሉም ይህን ንቅናቄ ለመፍጠር በሚካሔዱ ስራዎች በሁሉም ተቋማትና ወረዳዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንደሚካሔዱ፣ የስነምግባርና ፀረሙስና ፅንሰ ሐሳብን በተተኪ ትውልድም ላይ ለመቅረፅ በትምህርት ቤቶች የጥያቄና መልስ ውድድሮች እንደሚካሔዱ ጠቁመዋል።

እንዲሁም ግልፅነትና ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያም የሀብትና ንብረት ምዝገባ ያላካሔዱና ያላደሱ አካላትን እንዲያስመዘግቡና እንዲያድሱ የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም 5274 የመንግስት አመራሮችና ሰራተኞች የምዝገባ ዕድሳት እንዲያደርጉ የሚጠበቅ መሆኑንና 200 አዲስ ሰራተኞች ደግሞ ምዝገባ ለማካሔድ መታቀዱን ተናግረዋል።

በአጠቃላይም በንቅናቄው 60 ሺህ የሚደርሱ የክልሉ ነዋሪዎችን ተደራሽ ያደረገ የፀረሙስና ንቅናቄ ለማካሔድ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውቀዋል።

ህዝባዊ ንቅናቄን ፈጥሮ ሙስናን ማጋለጥ፣ መልካም ስነምግባርን ማላቅ፣ እና የሙስና ተግባር የፈፀሙ አካላትን ለህግ ማቅረብ የፀረ ሙስና ቀን አከባበሩ መሰረታዊ አላማ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የአለም የፀረ ሙስና ቀን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ1995 በተደረገውን ስምምነት መሰረት በየአመቱ ህዳር ወር የሚከበር ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም ሰነዱን በቀዳሚነት ከፈረሙ ሀገራት አንዷ ናት።

11/11/2026

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aysha ahmed posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category