Ethio Legal Work

Ethio Legal Work ���

ቡታጅራ ከተማ-እሁድ!ጥር 28 ማለትም እሁድ ከጠዋቱ 2 ጀምሮ በቡታጅራ ከተማ በኢትዮጲያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተቃጣውን መንግስታዊ ጥቃት በሰላማዊ ሰልፍ በቃ ትላለች። መረጃውን ለ10 ...
04/02/2023

ቡታጅራ ከተማ-እሁድ!

ጥር 28 ማለትም እሁድ ከጠዋቱ 2 ጀምሮ በቡታጅራ ከተማ በኢትዮጲያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተቃጣውን መንግስታዊ ጥቃት በሰላማዊ ሰልፍ በቃ ትላለች።

መረጃውን ለ10 ሰው ሼር በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታችንን እንወጣ!

የውብ ተፈጥሮ ባለቤት❗❗በአማራ ክልል የሚገኙ 34 ተራሮች❗❗❗የተራራው ስም --ከፍታው በሜትር-- የሚገኝበት ዞንና ወረዳ✔ራስ ደሽን --- 4620 ------ ሰሜን ጎንደር ----- በየዳ✔አ...
18/01/2023

የውብ ተፈጥሮ ባለቤት❗❗
በአማራ ክልል የሚገኙ 34 ተራሮች❗❗❗
የተራራው ስም --ከፍታው በሜትር-- የሚገኝበት ዞንና ወረዳ

✔ራስ ደሽን --- 4620 ------ ሰሜን ጎንደር ----- በየዳ
✔አናሎ ------- 4473 ---------ሰሜን ጎንደር ------ ደባርቅ
✔ወይኖበር--- 4465 ------- ሰሜን ጎንደር----- በየዳ
✔ቅዱስ ያሬድ-- 4453---------ሰሜን ጎንደር ----- በየዳ
✔ አባት ደጀን----4445-------------ሰሜንጎንደር ----- በየዳ
✔ ጠፋው ለዘር---4449----------ሰሜንጎንደር ----- በየዳ
✔ ቧሂት----------4430---------ሰሜንጎንደር ----- ጃናሞራ
✔ ሲሊኪ---------4420---------ሰሜንጎንደር------ ደባርቅ
✔ አባ ያሬድ------ 4409 -------ሰሜን ጎንደር----- በየዳ
✔ መሳረሪያ-----4355----------ሰሜንጎንደር----- ጃናሞራ
✔ደግረዋ--------4316--------ሰሜንጎንደር--------ደባርቅ
✔ቦርጭ ውሃ----4272-------ሰሜንጎንደር------ደባርቅ
✔ ዋልያቀንድ---4249-------ሰሜንጎንደር-------ጃናሞራ
✔ሸዋና------4113---------ሰሜንጎንደር---------ጃናሞራ
✔እናትየ-------4070-------ሰሜንጎንደር----------ደባርቅ
✔ጓዘመቀርቀቢያ---4063-----ሰሜንጎንደር------ጃናሞራ
✔ትልቅ አምባ----4044-------ሰሜንጎንደር--------ደባርቅ
✔ጨነቅ---------4000---------ሰሜንጎንደር-------ጃናሞራ
✔ጉና ----4231---ደቡብጎንደር---እስቴ፣ፉርጣ፣ላይ ጋይንት
✔አደባባይ--- 4261 ----- ደቡብ ወሎ ----ሳይንትና ተንታ
✔ጠና --------4208----------ደቡብ ወሎ------- መቅደላ
✔አንጦት -------4108------ደቡብ ወሎ------- ለጋንቦ
✔የወል ------- 3832-------ደቡብ ወሎ------- ደሴ ዙሪያ
✔ልመስክ -----3710---ደቡብ ወሎ---መሃል ሳይንትና ቦረና
✔ወፋጮ ---- 3651------ደቡብ ወሎ------ አባሰል
✔ ወረባያሱ -----3598------ደቡብ ወሎ------ ወረኢሉ
✔ መሆነኛ -------3463 ----ደቡብ ወሎ------ኩታ በር
✔ ጦሳ----------ከ2500 በላይ---- ደሴ ---------ደሴ ዙሪያ
✔አዳማ -------3533--------------------- ምዕራብ ጎጃም
✔ መገዘዝ------3596------ሰሜን ሸዋ------- አሳግርት
✔ጓሳ--------3400-------- ሰሜን ሸዋ
✔ጮቄ-----4100-------ምስራቅ ጎጃም-----ቢቡኝ
✔አባሚኒዎስ--3664---ምስራቅ ጎጃም---እነብሴ ሳርምድር
✔ አራት መከራከር---3537-----ምስራቅ ጎጃም-----ቢቡኝ

ልጄ ሆይ ፈልጊኝ! ውድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ እኔ መኮንን ይግዛው ካሳ እባላለሁ።  ልጄም  ፀሀይነሽ መኮንን ይግዛው ትባላለች የትውልድ  ሀገሯ  ጎጃም ቡሬ ዳሞት ሲሆን። ልጄም  እኔ ለስራ ...
10/01/2023

ልጄ ሆይ ፈልጊኝ!

ውድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ እኔ መኮንን ይግዛው ካሳ እባላለሁ። ልጄም ፀሀይነሽ መኮንን ይግዛው ትባላለች የትውልድ ሀገሯ ጎጃም ቡሬ ዳሞት ሲሆን። ልጄም እኔ ለስራ አዲስ አበባ ስመጣ አብራኝ መኖር ጀምራ እርሷም በ1984 ዓ.ም ከቦሌ ኦሎምፒያ ለስራ ብላ እንደወጣች አልተመለሰችም ከቤት ስትወጣ የሁለት ዓመት ህፃን ሴት ልጅ አስቀምጣ ነው የወጣችሁ።የልጄ ልጅም አድጋ አሁን ለቁም ነገር በቅታለች ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ሳትመለስ እስከ አሁን ድረስ በምችለው ነገር ሁሉ ሳፈላልግ ቆይቻለሁ::እንደ አጋጣሚ ሆኖ የልጄ ፎቶ የለኝምና እባክሽ ልጄ ሆይ ፈልጊኝ ልጅሽም እየፈለገችሽ ነውና እናንተ ደጋግ ውድ ኢትዮጵያዊን የእኔን ፎቶ አይታ ልጄን እንዳገኛት እንድትተባበሩኝ በፈጣሪ ስም እጠይቃችኋለሁ።
ሲ. ቁ 0911709755, 0921544700 ወይም 0921605004 , 0912850715 ደውልልኝ

03/01/2023

የነ አጅሬ አይበገር
አትንኩኝ ባይ የፋኖ ዘር

#ሸር

አየር መንገዱ ወደ ሽረ እንዳስላሴ ዳግም በረራ ጀመረአዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ወደ ሽረ እንዳስላሴ የሚያደርገውን በረ...
02/01/2023

አየር መንገዱ ወደ ሽረ እንዳስላሴ ዳግም በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ወደ ሽረ እንዳስላሴ የሚያደርገውን በረራ በዛሬው ዕለት ጀምሯል፡፡

ባለፈው ሳምንት አርብ አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ መቀሌ ዳግም መደበኛ በረራ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ቴዲ ዮን ለእስር እና አፈና የዳረገው ይህ ነው👇 እውነት እውነቱን እስኪ ልናገርሁሉም ይበል ባንቺ ጥንቅር  ተወልደናል እኛ ሸገር     እንደሌለን ሆነን ሀገርዝም ያለ ሁሉ የሸገር ሰው ወዴት...
01/01/2023

ቴዲ ዮን ለእስር እና አፈና የዳረገው ይህ ነው👇

እውነት እውነቱን እስኪ ልናገር
ሁሉም ይበል ባንቺ ጥንቅር
ተወልደናል እኛ ሸገር
እንደሌለን ሆነን ሀገር
ዝም ያለ ሁሉ የሸገር ሰው
ወዴት ይሆን ሄዶ እሚያርፈው
ያአራዳ ልጅ እድለኛ
የፀዳ ነው ከዘረኛ
ፍቅር እኛ ጋር ኪስ ግን ባዶ
በዚህ ከቀና አይስቅ ወዶ

አረንጎዴ ቢጫ ቀይ አርማችን የኛ መመኪያችን
ፍቅር መስጠት ያስተማረችን ሸገር እናታችን

ጥቁር ንስር መልካም ልደት!በቃ የክርስቲያን ታደለ አድናቂዎች ገፅ ከፍቻለሁ  ገብታችሁ ላይክ እና ኮሜንት አሳዩኝ እስኪ
01/01/2023

ጥቁር ንስር መልካም ልደት!
በቃ የክርስቲያን ታደለ አድናቂዎች ገፅ ከፍቻለሁ ገብታችሁ
ላይክ እና ኮሜንት አሳዩኝ እስኪ

   #አድርጉልኝ https://www.facebook.com/114837008134605/posts/122331397385166/?mibextid=Nif5oz #እጮሃለሁ! ...  #አሞኛል!  ...  😭(በ...
31/12/2022

#አድርጉልኝ https://www.facebook.com/114837008134605/posts/122331397385166/?mibextid=Nif5oz
#እጮሃለሁ! ... #አሞኛል! ... 😭

(በአርቲስት ሜሮን ጌትነት)
==========
አባቴ ተሰቅሎ፣
ወንድሜ ተቃጥሎ።
እህቴ ታግታ፣
እናቴ ተቀልታ።
አያቴ ተሰ'ዶ
ህፃን ልጄ ታርዶ... አሞኛል!
ወገን ሞቶብኛል!
ሰው ተገ'ሎብኛል
በማያውቀው ጉዳይ ባልገባው ጨዋታ፣
በሌለበት ግንባር ባልዋለበት ሜዳ ቀድሞ እየተመታ፣
ተጨምቆ ተጨምቆ ጠብ ላይልለት የድላቸው ፋይዳ፣
መከራ የሚገፋው እየወደቀበት የማያውቀው እዳ...።
ሞት እያንዣበበ... ደክሞት ካረፈበት ከደሳሳ ቤቱ፣
ለማይሞላ ኑሮው ለማይነጋው ሌቱ።
ዛች ጥርስ እያፋጨ፣
ጥይት እያፏጨ።
ካራ እየተሳለ፣
ቀስት እየተሾለ...
አለ!
ከተፈጥሮ ታግላ፣
ጎታች ባህል ጥላ፣
ልትማር የተጋች ቀን ይወጣል ብላ።
መድረሻ ተነፍጋ መንገድ ላይ የቀረች
እህቴ.... የታለች?
አሞኛል!
ሰው ተገድሎብኛል!
ሰው ተሳዶብኛል! ተፈናቅሎብኛል! ከኖርበት ቀዬ፣
የአቅሜን እጮሃለሁ ...
"የሰላም፣ ፍትህ፣ የህግ ያለህ!" ... ብዬ።
"የኔ አቅም ለቅሶ ነው ድምፅ ልሁናቸው ልጩህላቸው" ስል
ይመጣል ሳይፈራ አሳ'ቆ ሊያፍነኝ ቃላቱን የሚስል
"ምንድነሽ?" ይለኛል "ለእገሌ ለእንትና" ጉዳቴ ሳይገደው
"የሟች ወገኑ ነኝ!" ንፁህ ሆኖ ሳለ ለሞት 'ሚማገደው።
"የት ነበርሽ?" ይለኛል
"ለምን ዛሬ?" ይለኛል... ይሳለቅብኛል ድምፄን እየለካ
ስጮህም ዝምም ስል ለ'ሱ ፖለቲካ
"መርጠሽ ነው" ይለኛል...
መርጦ ገዳይ ካለ በየአደባባዩ፣
መርጬስ ባለቅስ ማን ይሆን ከልካዩ?
መርጬ አለቅሳለሁ ለተገፋው ህዝቤ ለሞተው ወገኔ
ቡድኑን አንተ አብጀው ንፁህ መሆኑ ነው የሚያገባኝ እኔ።
በፈለግኩት ጊዜ በፈለግኩት ቦታ
ስችል አለቅሳለሁ ሳልችል በዝምታ
ፈቃጅ አልፈልግም ለራሴ ስብራት ሀዘን አስተማሪ
አስታዋሽ አልሻም ላጣሁት ወገኔ የ'ጩሂለት' ጥሪ
በፈለግኩት ጊዜ በፈለግኩት ቦታ
ስችል አለቅሳለሁ ሳልችል በዝምታ
"የማን ነሽ? ምንድነሽ? ከየት ነሽ?" ይለኛል ከየትስ ብመጣ?
ገድዬ አልፎከርኩኝ ሞቶብኝ ነው እንጂ አቅሌን የማጣ
ገዳይ ንፁህ ፈጅቶ በኮራበት ሀገር
ለተገፋ ማልቀስ ለምነው 'ሚያስወግር?
ገድሎም አይበቃውም "እሰይ" ብሎ አይረካ
እንባዬን አድርቆ ሀዘኔን መቀማት አዲስ ፖለቲካ
እጮህለታለሁ...
ንፁሁ ሲጎዳ ባልመረጠው ደሙ ባልመረጠው መልኩ
ክርስቲያንም ሙስሊም ጥፋት ከሆነበት በምርጫ ማምለኩ
ለአማራ እጮሃለሁ በጅምላ ለሚያልቀው ለሚፈሰው ደሙ
ለትግራይ እጮሃለሁ ጦርነት ሲጎሰም በልቶት ሰቀቀኑ፣
ስደት ለመረጠው ከገዛ ሀገሩ፣ ከገዛ ወገኑ።
ለተደፈረችው፣ ለተሰበረችው እንግልት እህቴ፣
ላዘነች እናቴ
ለኦሮሞ ወንድሜ፣ ለደቡብ አባቴ፣ ለሀረሪ፣ ሱማሌ፣
ቤኑሻንጉል፣ አፋር፣ ድሬደዋ ላለው ወይ አዲስ አበቤ።
ለተበዳይ ህዝቤ፣ ለሞተ ወገኔ...
እጮህለታለሁ!
ቡድኑን አንተ አብጀው ንፁህ መሆኑ ነው የሚያገባኝ እኔ።
ትናንት ጮኼያለሁ፣ እጮሃለሁ ዛሬ፣ እጮሃለሁ ነገ
ሁሉም ወገኔ ነው ድምፅ የተነፈገ።
እጮህለታለሁ! ... እጮሃለሁ!

   #አድርጉልኝ https://www.facebook.com/114837008134605/posts/122331397385166/?mibextid=Nif5oz #እጮሃለሁ! ...  #አሞኛል!  ...  😭(በ...
31/12/2022

#አድርጉልኝ https://www.facebook.com/114837008134605/posts/122331397385166/?mibextid=Nif5oz
#እጮሃለሁ! ... #አሞኛል! ... 😭

(በአርቲስት ሜሮን ጌትነት)
==========
አባቴ ተሰቅሎ፣
ወንድሜ ተቃጥሎ።
እህቴ ታግታ፣
እናቴ ተቀልታ።
አያቴ ተሰ'ዶ
ህፃን ልጄ ታርዶ... አሞኛል!
ወገን ሞቶብኛል!
ሰው ተገ'ሎብኛል
በማያውቀው ጉዳይ ባልገባው ጨዋታ፣
በሌለበት ግንባር ባልዋለበት ሜዳ ቀድሞ እየተመታ፣
ተጨምቆ ተጨምቆ ጠብ ላይልለት የድላቸው ፋይዳ፣
መከራ የሚገፋው እየወደቀበት የማያውቀው እዳ...።
ሞት እያንዣበበ... ደክሞት ካረፈበት ከደሳሳ ቤቱ፣
ለማይሞላ ኑሮው ለማይነጋው ሌቱ።
ዛች ጥርስ እያፋጨ፣
ጥይት እያፏጨ።
ካራ እየተሳለ፣
ቀስት እየተሾለ...
አለ!
ከተፈጥሮ ታግላ፣
ጎታች ባህል ጥላ፣
ልትማር የተጋች ቀን ይወጣል ብላ።
መድረሻ ተነፍጋ መንገድ ላይ የቀረች
እህቴ.... የታለች?
አሞኛል!
ሰው ተገድሎብኛል!
ሰው ተሳዶብኛል! ተፈናቅሎብኛል! ከኖርበት ቀዬ፣
የአቅሜን እጮሃለሁ ...
"የሰላም፣ ፍትህ፣ የህግ ያለህ!" ... ብዬ።
"የኔ አቅም ለቅሶ ነው ድምፅ ልሁናቸው ልጩህላቸው" ስል
ይመጣል ሳይፈራ አሳ'ቆ ሊያፍነኝ ቃላቱን የሚስል
"ምንድነሽ?" ይለኛል "ለእገሌ ለእንትና" ጉዳቴ ሳይገደው
"የሟች ወገኑ ነኝ!" ንፁህ ሆኖ ሳለ ለሞት 'ሚማገደው።
"የት ነበርሽ?" ይለኛል
"ለምን ዛሬ?" ይለኛል... ይሳለቅብኛል ድምፄን እየለካ
ስጮህም ዝምም ስል ለ'ሱ ፖለቲካ
"መርጠሽ ነው" ይለኛል...
መርጦ ገዳይ ካለ በየአደባባዩ፣
መርጬስ ባለቅስ ማን ይሆን ከልካዩ?
መርጬ አለቅሳለሁ ለተገፋው ህዝቤ ለሞተው ወገኔ
ቡድኑን አንተ አብጀው ንፁህ መሆኑ ነው የሚያገባኝ እኔ።
በፈለግኩት ጊዜ በፈለግኩት ቦታ
ስችል አለቅሳለሁ ሳልችል በዝምታ
ፈቃጅ አልፈልግም ለራሴ ስብራት ሀዘን አስተማሪ
አስታዋሽ አልሻም ላጣሁት ወገኔ የ'ጩሂለት' ጥሪ
በፈለግኩት ጊዜ በፈለግኩት ቦታ
ስችል አለቅሳለሁ ሳልችል በዝምታ
"የማን ነሽ? ምንድነሽ? ከየት ነሽ?" ይለኛል ከየትስ ብመጣ?
ገድዬ አልፎከርኩኝ ሞቶብኝ ነው እንጂ አቅሌን የማጣ
ገዳይ ንፁህ ፈጅቶ በኮራበት ሀገር
ለተገፋ ማልቀስ ለምነው 'ሚያስወግር?
ገድሎም አይበቃውም "እሰይ" ብሎ አይረካ
እንባዬን አድርቆ ሀዘኔን መቀማት አዲስ ፖለቲካ
እጮህለታለሁ...
ንፁሁ ሲጎዳ ባልመረጠው ደሙ ባልመረጠው መልኩ
ክርስቲያንም ሙስሊም ጥፋት ከሆነበት በምርጫ ማምለኩ
ለአማራ እጮሃለሁ በጅምላ ለሚያልቀው ለሚፈሰው ደሙ
ለትግራይ እጮሃለሁ ጦርነት ሲጎሰም በልቶት ሰቀቀኑ፣
ስደት ለመረጠው ከገዛ ሀገሩ፣ ከገዛ ወገኑ።
ለተደፈረችው፣ ለተሰበረችው እንግልት እህቴ፣
ላዘነች እናቴ
ለኦሮሞ ወንድሜ፣ ለደቡብ አባቴ፣ ለሀረሪ፣ ሱማሌ፣
ቤኑሻንጉል፣ አፋር፣ ድሬደዋ ላለው ወይ አዲስ አበቤ።
ለተበዳይ ህዝቤ፣ ለሞተ ወገኔ...
እጮህለታለሁ!
ቡድኑን አንተ አብጀው ንፁህ መሆኑ ነው የሚያገባኝ እኔ።
ትናንት ጮኼያለሁ፣ እጮሃለሁ ዛሬ፣ እጮሃለሁ ነገ
ሁሉም ወገኔ ነው ድምፅ የተነፈገ።
እጮህለታለሁ! ... እጮሃለሁ!

28/12/2022

 #ሸር #አድርጉት #ለጠላቶቻችንበጎንደር ከተማ አስተደተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ለፋኖ ባሻ እሱ ባለው የመኖሪያት ቤት ሰጠ!የፋኖ ባሻ ስጦታው ዳኛው የመኖሪያ ቤት የመኖሪያ ቤት ርክክብ ስነ...
20/12/2022

#ሸር #አድርጉት #ለጠላቶቻችን
በጎንደር ከተማ አስተደተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ለፋኖ ባሻ እሱ ባለው የመኖሪያት ቤት ሰጠ!

የፋኖ ባሻ ስጦታው ዳኛው የመኖሪያ ቤት የመኖሪያ ቤት ርክክብ ስነ-ስርዓት ዛሬ ተከናውኗል። በዕለቱ የአራዳክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባንታየሁ ሞላ ባስተላለፉት መልክት የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ፋኖ ባሻ ስጦታው አገርን ሰላም ለመጠበቅ ላደረገው አሰተዋፅዎ የመኖሪያ ቤቱን መሰጠቱን ገልፀው ቀጣይም ክፍለ ከተማው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ የፋኖ አባላት ሀገር እንዳትፈራርስ በጀግንነት የታገለ ጀግኖችን ነው። ፋኖ በጦርነቱ ስንቄን ማቄን ሳይል ለሀገር ሰላም የሚታገል በሰላም ጊዜ ደግሞ በልማት ግንባር ቀደም ሁኖ የሚሰራ ሃይል ነው ብለዋል።

የፋኖ አባላት የአካባቢያችን ሰላም በመጠበቅ ረገድ የተጫወተው ሚና ከፍ ያለ ነው ።አሁን ከተማዋ ሰላም ማድረግ ተችሏል። ይህን አጠናክረን መቀጠል አለብን።ለለጎንደር ፋኖ የመከላከያ ሰራዊቱም መልካም ስም ያለው ነው።የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ የፋኖ አባላትን ለመደገፍ ዝግጁ ነው ብለዋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ለፋኖ ባሻ ስጦታው የመኖሪያ ቤት በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል።
የከተማ አስተዳደሩም የፋኖ አባላት በቋሚነት ወደ ልማት እንዲገቡ የሚያስችል የድጋፍ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክፍለ ከተማው የፋኖ አባላት ፣የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አ ቶ አወቀ አስፈሬ ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ፋኖ ባሻ እሱ ባለውም ለተሰጠው የመኖሪያ ቤት ስጦታ ክፍለ ለክፍለ ከተማው ምሶጋና አቅርቧል።

መረጃው የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽ ነው።

 በጫካ የነበሩ 300 በላይ የቅማንት ታጣቂ ቡድን አባላት በሰላም እጃቸውን ሰጡአዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከማህበረሰቡ አፈንግጠው በጫካ የነበሩ 300 በላይ የቅማንት ...
19/12/2022


በጫካ የነበሩ 300 በላይ የቅማንት ታጣቂ ቡድን አባላት በሰላም እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከማህበረሰቡ አፈንግጠው በጫካ የነበሩ 300 በላይ የቅማንት ታጣቂ ቡድን አባላት በሰላም እጃቸውን ለመንግስት ሰጡ፡፡

ታጣቂ ሃይሎች በሀገር ሽማግሌዎች ጥረትና በመንግስት የሰላም ጥሪ ትጥቆቻቸውን ለመንግስት በማስረከብ ለውይይት መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ÷ ታጣቂ ሃይሎች ለተጠቀሙት የሰላም አማራጭ ሒደት የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ጥረት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለተደረገው ጥረት ምስጋና ያቀረቡት ሃላፊው÷ከ300 በላይ የሚሆኑ ታጣቂ ሃይሎችም ወደ ቀያቸው ሰላምን መርጠው መመለሳቸው የህብረተሰቡ ስጋት የነበረውን ሞት፣ መፈናቀልና እገታ የሚቀርፍ ነው ብለዋል።

ቡድኖቹ አፈንግጠው በመውጣት በጠላት ሴራና በግል ፍላጎት ህብረተሰቡን በብሔር ስም እያጋጩ ለአላስፈላጊ ችግር ዳርገውት እንደቆዩ አንስተው÷ ሰርቶ መለወጥና ሀገርን መጥቀም የሚችል ወጣት ሃይልን ጫካ እንዲገባ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የህወሓትን አጀንዳ እየተቀበሉ ለክፋት ሲሮጡ የነበሩ ሃይሎች በመመካከርና በንግግር መፍትሄ እንደሚመጣ ሊገነዘቡ እንደሚገባና ህብረተሰቡም ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ ይደረጋልም ነው ያሉት።

የቅማንት የማንነትና ራስ አስተዳደር ኮሚቴ አበላት ችግሮች በመነጋገር እንጂ በሃይል ስለማይፈቱ የሰላም አማራጭን መቀበል ለሁሉም አካል ጠቃሚ መሆኑን በማመን መንግስት ጠርቶ እንዲያነጋግራቸው መምጣታቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይ መንግስት የሚያስቀምጣቸውን አቅጣጫዎች በመከተል ፊታቸውን ወደ ልማት እንደሚያዞሩም ነው የተናገሩት።

የሰላም አማራጩን ተቀብለው ከነትጥቃቸው የገቡ የቅማንት ታጣቂ ቡድን አባላት በመንግስት የአመለካከት ለውጥ ስልጠና እንደሚሰጣቸውም ተገልጿል።

በሙሉጌታ ደሴ

Address

Dessie

Telephone

+251919669035

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Legal Work posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share