Ezra Ab

Ezra Ab Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ezra Ab, Grocers, Boditi.

03/01/2026
04/07/2025
04/07/2025

ፅዱና ምቹ አካባቢን ለመፍጠር ማህበረሰቡ ፅዳትን ባህሉ እንዲያደርግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ።

ሰኔ 27/2017 ዓ.ም:-በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዋዩ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ፅዱና ምቹ አካባቢን ለመፍጠር ማህበረሰቡ ፅዳትን ባህሉ እንዲያደርግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ጥላሁን ገለፁ።

የወረዳ ዋዩ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ከማህበረሰቡ የሚቀርቡ ጥቆማና አስተያይቶችን ተቀብለን ተቋሙን ማነጋገር ተችሏል።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ጥላሁንም እንደገለፁት ቆሻሻ ያለአግባብና ያለቀን ከመጣል እንዲሁም ቋሚ ሳምንታዊ የፅዳት ዘመቻ ላይ ያለመሳተፍ ጋር በተያያዘ በሁሉም ብሎክ ተገቢዉን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን ገልፀዉ በዚህም ህብረተሰቡ አካባቢዉንና ሰፈሩን በየሳምንቱ የማፅዳት ስራ ባህል አድርጓል ብለዋል።

ኃላፊዉ አያይዘው ይህ ብቻዉን በቂ ስላልሆነ ህብረተሰቡ የራሱን አካባቢና ግቢ የማፅዳት ባህሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል እየሰራን ነዉ ሲሉ ገልፀዋል። ስለሆነም በወረዳዉ የተሻሉ ሞዴል ብሎክ መፍጠር መቻሉንም ገልፀዉ ይህን ወደ ሌሎች ብሎክ የማስፋት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዉ ።

ቀጥለውም በተለይ የፅዳት ሰራተኞች የሚያነሱትን ችግር ለመቅረፍ የአንድ ማዕከል የደረቅ ቆሻሻ የቅብብሎሽ ጣቢያ ለመገንባት የቦታ ልየታና ሌሎች ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።ስለሆነም ቆሻሻ ሀብት እንደመሆኑ መጠን መልሶ ለመጠቅም ስራ በተለይ በትምህርት ቤቶች አካባቢ በስፋት እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይሁን እንጅ ከፍተኛ የበጀት እጥረት መኖር ፣የግብዓትና የባለሙያ ችግር መኖር ስራዎችን በተያዘዉ እቅድ መሰረት ለመምራት ተግዳሮት መሆኑን ለወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቀዋል።

#ወረዳ ዋዩ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት

28/06/2025

Address

Boditi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ezra Ab posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category