melkshoow ads agent

melkshoow ads agent this page is advertising and marketing page if you want do it please kindly contact me

ኤርትራው ብልጽግናን ከሰሰች‼️የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የብልጽግና ባለሥልጣናትን  ወነጀሉየኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር፣ የብልጽግና ባለሥልጣናት በኤርትራ ላይ የሚያካሄዱትን  ግድየለሽ...
04/09/2025

ኤርትራው ብልጽግናን ከሰሰች‼️

የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የብልጽግና ባለሥልጣናትን ወነጀሉ
የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር፣ የብልጽግና ባለሥልጣናት በኤርትራ ላይ የሚያካሄዱትን ግድየለሽነት የተሞላበት ወታደራዊ ዛቻ ቀጥለውበታል ሲሉ ከሰሱ።

የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል፣ ረቡዕ ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋዊ የኤክስ ገጻቸው ላይ፣ የብልጽግና ፓርቲ ባለሥልጣናትና ''ተሳዳቢዎቻቸው'' በኤርትራ ላይ "በዘፈቀደ" የሚያካሂዱትን "ወታደራዊ ዛቻ" ዳግም ቀጥለውበታል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው ውይይታቸው ላይ የቀይ ባሕርን ጉዳይ አንስተው "የተፈጸመው ስህተት በቅርቡ ይታረማል" ካሉ በኋላ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪያቸው ጋር በነበራቸው በዚህ ውይይት ላይ የታላቁ ሕዳሴ ግድብን መጠናቀቅ አስመልክቶ ሲናገሩ የሺህ ዓመት የአባይ ታሪክ እንደተቀየረው ሁሉ ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት ሁኔታም "ነገ ይታረማል፤ ብዙ ከባድ አይደለም" ብለዋል።

የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር በኤክስ ልጥፋቸው ላይ፣ የብልጽግና ፓርቲ ባለሥልጣናት የኤርትራን ጥንታዊ፣ የመካከለኛው ዘመንና ዘመናዊ ታሪክ ያዛባሉ በማለት ወቅሰዋል።

የአሁኑ የብልጽግና ፓርቲ ባለሥልጣናት ንግግር ከኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ጋር እንደሚያያዝ የጠቆሙት የማነ፣ ሕዝበ ውሳኔው ኤርትራን በወረራ የያዘችው አገር በቅድሚያ ፍላጎቷ ሊጠየቅ ወይም ሕዝበ ውሳኔውን እንድትቀበል በቅድመ ሁኔታነት ሊቀርብ የሚችልበት ሁኔታ እንዳልነበረና ሊኖርም እንደማይችል ገልጸዋል።

የማነ ይህን ያሉት፣ በቅርቡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ፣ ''ኢትጵያ የባሕር በር የምትጠይቅበት አራት አሳማኝ ምክንያቶች አላት'' በማለት ከዘረዘሯቸው ነጥቦች መካከል አንዱ አሰብ በወቅቱ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ተላልፎ መሰጠቱን ነው።

ኤርትራ ነጻነቷን ስታገኝ የአሰብ ወደብ ወደ ኤርትራ የሄደበትን መንገድ በማንሳት ያብራሩት ጄነራሉ፣ በወቅቱ የነበረው የሽግግር መንግሥት በመሆኑ "የባሕር በርን ያክል ለመስጠት ሕጋዊ ውክልና" አልነበረውም ብለው መናገራቸውን ተከትሎ ነው።

===========================
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ads agent follow

🌟 እንኳን ወደ Darash Media በደህና መጡ - ይህ ፈጣንና ወቅቱን የጠበቁ ዓለም አቀፍ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መረጃዎች መገኛ መድረክ ነዉ ethio news # World news # news # Israel news # Ethiopia news # Tigray ne...

ታግተናል በማለት ወላጆቻቸውን 500ሺህ ብር የጠየቁ ታዳጊዎቸ በቁጥጥር ስር ዋሉ  ምርመራ እያደረገም  መሆኑን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልፇል።የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአዲ...
01/08/2025

ታግተናል በማለት ወላጆቻቸውን 500ሺህ ብር የጠየቁ ታዳጊዎቸ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ምርመራ እያደረገም መሆኑን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልፇል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

አጋችና ታጋች በመምሰል የማታለል ወንጀሉን የፈፀሙት አራቱ ተጠርጣሪዎች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ሲሆኑ ለሁለት ቀናት ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ሲዝናኑ ቆይተው ገንዘብ ሲያጥራቸው በመመካከር ለቤተሰብ ስልክ ደውለዋል፡፡

ወንዶቹ አጋች ሴቶቹ ደግሞ ታጋቾች በመሆን ለሴቶቹ ቤተሰቦች በደወሉት ስልክ 5 መቶ ሺ ብር የጠየቁ ሲሆን የሴት ወላጆች አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ጥቆማ ሠጥተዋል። ፖሊስም ለቀረበው ጥቆማ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት መረጃዎችን በማሰባሰብ አራቱንም ተጠርጣሪዎች ካሉበት ቦታ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው ችሏል፡፡

የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በወቅቱ ሴት ልጆቻቸው መታገታቸውን ሲሰሙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተው እንደነበር ተናግረው ፖሊስ ላከናወነው ተግባርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በልጆች አስተዳደግ ዙርያ የቤተሰብ ኃላፊነት ከፍተኛ ሲሆን በአንዳንድ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚስተዋለው ባህሪ የነገ ተስፋቸውን ሊያጨልም የሚችል በመሆኑ ሊታረምና በወላጆች ዘንድም ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪ አቅርቧል ።

በዜሮ አመት[የሲዳማ ክልል] -  የጉምሩክ ኮሚሽን ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
01/07/2025

በዜሮ አመት[የሲዳማ ክልል] - የጉምሩክ ኮሚሽን ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

Address

Hawasa
Awassa
520

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when melkshoow ads agent posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category