Maalta’inna laataa ?

Maalta’inna laataa ? Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Maalta’inna laataa ?, Grocers, Awash.

23/10/2026
22/10/2026

የጋራ እሴቶች የሚባሉት ማኅበረሰቡ በአንድነት የሚጋራቸው እና የሚያከብራቸው መልካም አመለካከቶች እና ባህሪያት ናቸው።

የጋራ እሴቶች፦
🔹 መተማመንን ያጠናክራሉ
🔹 የአብሮነት ስሜትን እና የልማት ትብብርን ያጎለብታሉ
🔹 ግጭቶች በውይይት እና በመግባባት እንዲፈቱ ያግዛሉ
🔹 ፍትሕን፣ እኩልነትን እና የጋራ ተጠቃሚነትን ያበረታታሉ
🔹 መከባበርን እና ልዩነትን በክብር የመቀበል ባህልን ያዳብራሉ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ የጋራ እሴቶቻችንን በማጠናከር መተማመንን፣ አንድነትን እና ዘላቂ ሰላምን እናጎለብታለን።

💬 በአካባቢዎ ትብብርን እና አንድነትን የሚያጠናክሩ የጋራ እሴቶች የትኞቹ ናቸው?

ሰላም ለኢትዮጵያ!🕊

የኤርትራው ሻዕቢያ አለም አቀፍ ጫና እየደረሰባቸው ሲሆን ብሪታንያ የባለስልጣናት ቪዛ አገደችበተለያዩ ዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ጉዳዮች ምክንያት ለዜጎቿ ምቹና አስተማማኝ ከባቢ መፍጠር ያቀታት ኤ...
15/10/2026

የኤርትራው ሻዕቢያ አለም አቀፍ ጫና እየደረሰባቸው ሲሆን ብሪታንያ የባለስልጣናት ቪዛ አገደች

በተለያዩ ዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ጉዳዮች ምክንያት ለዜጎቿ ምቹና አስተማማኝ ከባቢ መፍጠር ያቀታት ኤርትራ አለም አቀፍ ማዕቀቦች እየደረሱባት ነው። ሙሉ እድሜውን ለግብፅና ለሌሎች ውጫዊ ፍላጎቶች ብቻ እየኖረች ነው። አለም አቀፍ ወቀሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መጥቷል። ለገዛ ሕዝቧ ሰላምና የኢኮኖሚ ተስፋ መስጠት ባለመቻሏ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶቿ በየባህሩና በየበረሃው እየተንከራተቱ ለከፍተኛ እንግልት ሲዳረጉ፣ መንግሥቷ ግን ሀገራዊ አቅሙንና ትኩረቱን የሌሎች ሀገራትን የፖለቲካ ፍላጎት ለማስፈጸም በማዋል ላይ ይገኛል። ይህ የዜጎችን ሰብአዊ መብትና ጥቅም ችላ የማለት አካሄድ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን እያስከተለ ሲሆን፣ መንግሥት ለገዛ ዜጎቹ ግዴታውን ባለመወጣቱ ሀገሪቱ ለከፋ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ባዶነት እየተዳረገች ትገኛለች።

በዚህም ምክንያት ብሪታንያ ምክንያታዊ በሆነ አሠራርና በግልጽ መነሻ የኤርትራ ባለሥልጣናትና ዲፕሎማቶች ላይ የቪዛና የእንቅስቃሴ ማዕቀቦችን መጣሏ፣ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊገጥማት የሚችለውን አዲስ የማዕቀብ ማዕበል መጀመሪያ ተደርጎ እየታየ ነው። እንግሊዝ የጀመረችው ይህ ጠንካራ የዲፕሎማሲያዊ ማዕቀብ እርምጃ ሌሎች አውሮፓውያንና የምዕራብ ሀገራትም በተመሳሳይ መልኩ እንዲከተሉት መንገድ የሚከፍት ሲሆን፣ ኤርትራ ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን የማታከብርና የዜጎቿን መብት የማታስከብር ከሆነ ከቀጣናዊና ከዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ይበልጥ ተገለልተኛ እንድትሆን ያደርጋታል። ይህ ሁኔታ የሀገሪቱን ዲፕሎማሲያዊ ጫና ከመጨመሩም በላይ፣ በውጭ ሀገራት የሚኖሩና የሚንከራተቱ ኤርትራውያንም ከራሳቸው መንግሥት ጥበቃና ትብብር በማጣታቸው ምክንያት የበለጠ ለከፋ እንግልት እንዲዳረጉ በር የሚከፍት ነው።

12/10/2026
11/10/2026
10/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የተቋማት አመራሮች ሾመዋል፦



ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Address

Awash

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Maalta’inna laataa ? posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category