Ruhama Belete

Ruhama Belete Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ruhama Belete, Grocers, Bahirdar, Agaro.

08/05/2026
29/01/2026

‎የክልሉን ሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን ይበልጥ ለማስፋፋት ያለመ የንቅናቄ መድረክ ይካሄዳል፦ወይዘሮ ኤልሳቤት ሽመልስ


‎ሆሳዕና፦ጥር 20/2018ዓ.ም
‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት የክልሉን ሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችልና ለተጀመረው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አቅም የሚፈጥር የንቅናቄ መድረክ ከክልል እስከ ቀበሌ ማዕከላት ለማካሄድ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

‎"በሴቶች ተሳትፎ የጸናችና የበለጸገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በሁሉም መዋቅሮች የሚካሄደው የንቅናቄ መድረክ መላው የክልሉ ሴቶች በሁሉም የልማት ዘርፎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ግንዛቤ የሚፈጥር እንደሆነም ተገልጿል።

‎የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ወይዘሮ ኤልሳቤት ሽመልስ የመድረኩን ዝግጅትና ፋይዳ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ፣ የንቅናቄ መድረኩ "በሴቶች ተሳትፎ የጸናችና የበለጸገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ መሆኑን ገልፀው፣ በሀገራችን ለሚካሄደው 7ኛ ዙር ምርጫ ህደቱ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ነጻና ፍትሀዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንዲሁም በልማቱ መስክ የተጀመሩ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ይበልጥ እየጎለበቱ እንዲመጡ መነቃቃትን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነም አመልክተው ለተግባራቶቹ ስኬት የሴቶች ሚና ከፍ ያለ ነው ብሏል።

‎ለንቅናቄ መድረኩ ክልላዊ የማስፈጸሚያ ዕቅድ መዘጋጀቱንም የገለጹት ሃላፊዋ ፤በዞን ፣በልዩ ወረዳ፣በወረዳ፣በትላልቅ ከተሞችና በቀበሌያት በሚደረገው የንቅናቄ መድረክ ከ900 ሺህ በላይ የክልሉ ሴቶች እንደሚሳተፉም ገልጸዋል።

‎የንቅናቄ መድረኩ በየደረጃው በሴቶች ክንፍ ግንባር ቀደም መሪነት እንደሚካሄድም ያስታወቁት ወይዘሮ ኤልሳቤት፣መድረኮቹ የክልሉ ሴቶች በየአካባቢያቸው ሰላምን በማረጋገጥ በቀጣይ የሰላም ዘብ ሆነው እንዲቆሙ ግንዛቤ የሚፈጥር ነው ብለዋል።

‎በመድረኮቹ አካባቢያዊ፣ክልላዊና አገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች የሚተነተኑ ይሆናሉ ሲሉ የገለጹት ሃላፊዋ፣ለንቅናቄ መድረኮቹ ስኬት የክልሉ ሴቶች ክንፍ አስተባባሪዎች ከዕቅድ ዝግጅት እስከ ማጠቃለያ መድረኮች በሁሉም መዋቅሮች የተጠናከር የድጋፍና ክትትል ስራዎች እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

‎የንቅናቄ መድረኮቹ የአገራችንን የለውጥ ጉዞ ከየት ተነስቶ የት ደረሰ በሚሉና በሂደቱም የሴቶች ሚና ምን እንደነበር እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ማትኮሩን ወይዘሮ ኤልሳቤት አስረድተዋል።

‎መድረኩ አገራዊ የለውጥ ጉዞ ያለበትን ደረጃ የክልሉ ሴቶች እንዲገነዘቡ የሚያደርግ፣በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ ሴቶች ንቁ ተሳታፊና ዋና ተዋናይ እንዲሆኑ የሚያስችል ምክክርና ውይይት የሚደረግበት የንቅናቄ መድረክ ስለመሆኑም የጽህፈት ቤት ሃላፊዋ አብራርተዋል።

‎የንቅናቄ መድረኩን አላማዎች ለማሳካት በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውንም ያስታወቁት ወይዘሮ ኤልሳቤት፣በክልሉ በየደረጃው የሚካሄዱ የማጠቃለያ መድረኮች በከፍተኛ አመራሮች የሚመሩ ስለመሆናቸውም ገለጻ አድርገዋል።


‎በክልሉ የሴቶች የንቅናቄ መድረኮች ላይ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የሌማት ቱሩፋትና ሌሎች ምርጥ ተሞክሮ አፈጻጸሞች የመስክ ምልከታዎችና የልምድ ልውውጥ መድረኮች እንደሚካሄዱም ሃላፊዋ በመግለጫቸው አንስተዋል።

‎በመድረኮቹ ማጠቃለያ ላይ የክንፉ የፌዴራል ስራ አስፈጻሚዎች እንደሚገኙም ያስታወሱት ወይዘሮ ኤልሳቤት ሽመልስ፣የንቅናቄ መድረኮቹ የተጀመረውን የዴሞክራሲና የልማት ግስጋሴ ይበልጥ አቅምና ጉልበት እንዲያገኝ የሴቶችን ተሳትፎና ርብርብ ይበልጥ የሚያጎለብት ስለመሆኑም አብራርተዋል።

‎ክልላዊ የሴቶች የንቅናቄ መድረኮቹ በክልሉ ሁሉም መዋቅሮች እስከ ቀበሌያት ድረስ ዛሬን ጨምሮ እስከ አንድ ወር ድረስ የሚካሄድ መሆኑም ተመላክቷል።

06/12/2025

የጋራ ትርክት ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ረገድ የጎላ ሚና አለው :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

(ሆሳዕና፣ህዳር 27/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በማስመልከት በጽ/ቤታቸው ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በማስመልከት ለመገናኛ ብዙሀን በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የጋራ ትርክት አእየጎለበተ ሲመጣ ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ረገድ የጎላ ሚና አለው ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው 20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ደማቅ በሆነ መንገድ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል።

በዓሉን አስመልክቶ ህዳር 28 እና 29 ሁለት አበይት ሁነቶች ይከናወናሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሲምፖዚየም እና የአደባባይ በዓላት ይከናወናሉ ብለዋል።

በሲምፖዚየሙ ክልላዊና ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ጉዳዮች እንደሚዳሰሱም ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

በሲምፖዚየሙ ውይይት መነሻነት የተገኙ ግብአቶች ለህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ እንዲደርስ ይደረጋል ብለዋል።

በሌላ በኩል ከ50ሺ በላይ የማህበረሰብ ክፍል የሚሳተፍበት እና ከፌደራል፣ከተለያዩ ክልሎች እና ከውጭ ሀገራት የተጋበዙ እንግዶች በተገኙበት የአደባባይ ዝግጅት እንደሚከናወንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

ክልሉ ከዛሬ 2 አመት ከ4 ወር በፊት መመስረቱን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ሀገራዊ እና ክልላዊ ህገ መንግስቱን በማጣጣም
የልማት፣የሰላም፣የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎችን ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱንም ጠቁመዋል።

በሁሉም ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ስለመቻሉም አመላክተዋል።

ከሁሉም በላይ የህዝብ ትስስር በማጠናከር የተጀመረውን የልማት ስራ ቀጣይነት ማረጋገጥ ተገቢ ስለመሆኑም አስረድተዋል።

ክልሉን 10 ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ መመስረታቸውን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ በሁሉም አካባቢዎች የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት ጥረት ስለመደረጉም ተናግረዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በነበሩት ሁለት አስርት ዓመታት የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና የነበረን ትርክት ያልተመጣጠነ እንደነበር ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያዊነት ጎልቶ ያልታየበት እና የብሔር ጉዳይ ገዝፎ የነበረበት ወቅት መሆኑን አብራርተዋል።

ከለውጡ በኋላ ሁለቱ ጉዳዮች ተመጣጣኝ እንዲሆኑ ስለመሰራቱም ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው ጠቁመዋል ።

ዓላማችን ታላቋን ኢትዮጵያን መገንባት እስከ ሆነ ድረስ ተቀራርበን እና ተደምረን ከነጠላ ትርክቶች በመውጣት የጋራ ትርክትን ማጠናከር ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በክልሉ በከተሞች የኮሊደር ልማትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ መቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ስናከብር ጠንካራ የህዝብ ትስስር መፍጠር መቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

የጋራ ትርክትን ከማጠናከር ባለፈ የልማት ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የላቀ እድል መፍጠር ስለመቻሉም አብራርተዋል።

Address

Bahirdar
Agaro

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ruhama Belete posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category