Gezahegn

Gezahegn Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gezahegn, Grocers, Addis Ababa.

10/07/2025

The Equaliser የሚሰኘው ተከታታይ ፊልምና ሌሎች ፊልሞቹ የሆሊውድ ፈርጥ የጥቁር አሜሪካዊያን ኩራት ሲያሰኙት የትዳር ህይወቱ ደግሞ
በአንድ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ሲሰሩ ነበር የተዋወቁት ፡ ተቀራረቡና ፡ አንድ ቀን እራት ልጋብዝሽ አላት ።

ጥሩ ቦታ ወሰዳት ፡ አሪፍ እራት በሉ ፡ እና ወደቤት ሊሄዱ ተነሱ ፡ ዴንዝል ዋሽንግተን የተጠቀሙበትን ሂሳብ ከፈለና ፡ ኪሱ ውስጥ የቀረውን ገንዘብ ሲያይ ደነገጠ ። በወቅቱ ሁለቱም መኪና የላቸውም ። ኪሱ ውስጥ የቀረው ገንዘብ ለታክሲ ላይበቃ ይችላል ። እና በባቡር እንሂድ ልበላት ? ወይስ ፡ ለምን ወክ አናደርግም ብዬ እስከቤት ልሸኛት ? የሚለውን እያሰበ እያለ ፡ ከሆቴሉ ወጥተው በሩ ላይ የተደረደሩት የሜትር ታክሲዎች ጋር ደረሱ ።

ፓውሌታ የአንዱን ታክሲ በር ከፍታ ገባች ። ዴንዝል ተከተላትና ፡ ወደቤቷ አቅጣጫ መጓዝ ጀመሩ ፡ እና እያወራት ፡ በመሀል ስንት እንደቆጠረ የታክሲውን ሜትር ያያል ።
ኬሎሜትሩ በጨመረ ቁጥር ፡ ብሩም እያደገ ሄደ ። ዴንዝል ዋሽንግተን ፡ ሀሳብ ገባው ፡ በመጀመሪያ ቀን ዴቲንግ ፡ የታክሲ መክፈል ያልቻለ ሰው ሆኗል ።
በመጨረሻም ቤቷ ደረሰች ። ዴንዝል ነገራት ።
ብር ጨርሻለሁ
ታዲያ ምን ችግር አለ ብላ የመጣችበትን እና እሱን ቤቱ ሊያደርሰው የሚችለውን ጨምራ ከፍላ ወረደች ።.....
ግንኙነታቸው እያደገ ሄዶ ፡ አንድ ቀን ቀለበት ገዝቶ ተንበረከከ
ፓውሌታ ፡ አብረን እንድንኖር እፈልጋለሁ ። ታገቢኛለሽ ? ሲል ጠየቃት
አላገባህም አለችው
ቀለበቱን ኪሱ ከቶ ተለያዩ ።....
ትንሽ ቆይቶ አንድ ቀን ይህንኑ ጥያቄ ደገመው ።
እኔና አንቺ ባልና ሚስት መሆን ያለብን ሰወች ነን ፡ አብረን እንድንኖር እፈልጋለሁ ፡ አለና ያንኑ ቀለበት አውጥቶ ለጋብቻ ጠየቃት ።
አዝናለሁ ዴንዝል አላገባህም ብላው ሄደች ።
እሱም ሄደ ።...

ከወራት በኋላ አንድ ቀን ያችኑ የፈረደባት ቀለበት አውጥቶ ፡ ለሶስተኛ ጊዜ አግቢኝ ሲል ጠየቃት ።
ፓውሌታ ይህን ተስፋ የማይቆርጥ ሰው ፡ አትኩራ አየችው እና የቀለበት ጣቷን ዘረጋችለት ።
እሽ አገባሀለሁ ።.........
ቆየት ብለው ሰርግ ደገሱ ፡ ትንሽ ሰርግ ነበር ። እና የሚበላ ነገር በተጠሩት ሰወች ልክ ተዘጋጀ ።

እንግዶች እየተመገቡ እያለም ፡ ሙሽሮቹ ዴንዝል ዋሽንግተንና ፡ ፓውሌታ ፒርሰን ፡ በሰርጋቸው ላይ የተገኙትን እንግዶች ፡ እየዞሩ ሰላም ሲሉና አብረው ፎቶ ሲነሱ ቆይተው. . ምግብ ሊያነሱ ወደ ጠረጴዛው ሲሄዱ ፡ ባዶ ነው ።
ምግቡ አልቋል ።.....
እንግዶቻቸውን ሸኝተው በሰርጋቸው ቀን ሬስቶራንት ሄደው ተመገቡ ።

ይህ ከሆነ አሁን አርባ አመታት አለፈ ። በዚህ መልኩ የተገናኙት ጥንዶች አራት ልጆች ወልደው ፡ ሶስት መቶ ሚሊየን ዶላር በባንክ አጭቀው ፡ ሆሊውድን የሚያምሰው የመፋታት አባዜ ሳያገኛቸው ፡ እስካሁን አሉ ።

©️Meseret Hon Kib

ድሮ በፈረስ እየጋለብን ነበረ ሌቦችን የምንይዘው ።
10/07/2025

ድሮ በፈረስ እየጋለብን ነበረ ሌቦችን የምንይዘው ።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gezahegn posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category