Addis ketema subcity trade office

Addis ketema subcity trade office office

17/05/2026
06/04/2026
06/04/2026

"ለበዓል ግብይት ምንም አይነት እጥረት እንዳይኖር በቂ ምርት ወደ መዲናዋ ገብቷል"

- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ
++++++++++++++++++++++++

| የበዓል ግብይት ላይ ምንም አይነት የአቅርቦት እጥረት እንዳይኖር በቂ ምርት ወደ መዲናዋ መግባቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ሃቢባ ሲራጅ በሰጡት መግለጫ በበዓል ግብይት ምንም አይነት የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር ዝግጅት ተደርጓል።

በተሰራው ስራም ከክልሎች ጋር ትስስር በመፍጠር በቂ ምርት ወደ መዲናዋ ገብቷል ብለዋል።

በመዲናዋ በሚገኙ የሰንበት ገበያዎች፣ ባዛሮች እንዲሁም የሸማች ማህበሮች በቂ ምርት እየገባ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ዓለም ላይ ያለው የነዳጅ ዋጋ የንግድ ዘርፉ ላይ ተጽዕኖ እያደረገ ነው ያሉት ኃላፊዋ፤ ሆኖም ከተማ አስተዳደሩ ቀደም ብሎ በተለይም ከተማ ግብርና ላይ በትኩረት በመስራቱ ችግሮችን መቋቋም መቻሉን ተናግረዋል።

ወደ መዲናዋ የገቡ ምርቶች ላይ መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ይሆናል ብለው፤ በተጋነነ ዋጋ ውጪ የሸጡ አካላት ላይ እርምጃ የሚወደስ ይሆናል ብለዋል።

ሸማቹም ያለ አግባብ ዋጋ የሚጨምሩ አካላት ላይ በ8588 ነፃ ስልክ መስመር ጥቆማ ማድረግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ቁጥጥሩ ከዋጋ ባለፈ መለኪያዎች እና ባዕድ ነገር የሚጨምሩ አካላት ላይ እንደሚደረግም አመላክተዋል።

በዳግማዊት አበበ
++++++++++++++++++++++++

02/03/2026

Address

Addis Ketema Subcity
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis ketema subcity trade office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category