Yasmin Gohan Beast

Yasmin Gohan Beast Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yasmin Gohan Beast, Grocers, ADDIS ABABA, Addis Ababa.

12/05/2026
05/05/2026

“የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልጽግና!”


የሚሰሩ እጆች፤ የሚፈጥሩ አዕምሮዎች ለሀገር ግንባታ ትልቅ መሰረትን ይጥላሉ። ሀገራችን በዚህ ወቅት በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ መቅዳት እና መልሶ በመጠቀም የዓለምን ፈጣን እድገት መቀላቀል ችላለች።
ትላንትና ተኪ ምርቶችን ባለማምረታችንና በውጭ ምንዛሪ እጥረት የምንፈልገውን ፈጣን እድገት ማስመዝገብ ላይ የነበረውን ውስንነት በመቅረፍ ትላልቅ ለውጦችን እያስመዘገብን እንገኛለን።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

27/04/2026

በመደመር ፍልስፍና የተቃኙት የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎች አካታችነትን በተግባር ማረጋገጥ አስችለዋል!

ኢትዮጵያውያን የጋራ ሀገር፣ የጋራ ታሪክ እንዲሁም የጋራ እጣፈንታ አለን፤ በመስዋዕትነት ጭምር የሀገርአችንን ዳር ድንበር በማስጠበቅም ይሁን ለሀገረ መንግስት ግንባታው አሻራን በማሳረፍ በየዘመኑ ሁሉም የድርሻውን ተወጥቷል፡፡

አንዱን ከአንዱ የሚያበላልጡ፣ አንዱን አቅርበው አንዱን የሚገፉ ህጎች እና አሰራሮች በአንድ ሀገር ህዝቦች ላይ ሊኖሩ ስለማይገባ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በተከናወኑ ተከታታይ የሪፎርም ስራዎች ሁሉም ዜጋ እኩል ተሳታፊ እና ተጠቃሚ የሚሆንበት አውድ ተፈጥሯል፡፡

ፖርቲያችን በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በማኅበራዊ እንቅስቃሴው ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ሕጻናትን እና ሌሎች ተጋላጭ እና የሀገር ባለውለታ ዜጎችን ታሳቢ አድርጎ በመሥራት ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡

ፓርቲያችን ሴቶችን ወደ አመራርነት በማምጣት በፖለቲካ ውሳኔ ሰጪነት በተገቢው መልኩ እንዲሳተፉ እያደረገ ሲሆን፣ በኢኮኖሚው እና በማኅበራዊ ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ እና የመከወን ዐቅም ለመጨመርም ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ሠርቷል።

ለማሳያም በከተማችን አዲስ አበባ አስታዋሽ አጥተው በአስከፊና በአሳሳቢ የኑሮ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች “የነገዋ የሴቶች የማገገሚያ እና የክህሎት ማዕከል”ን በመገንባት አዲስ የህይወት ምዕራፍ መክፈት ተችሏል፡፡

ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ወጣቶችን ወደ አመራርነት በማምጣትም ፓርቲያችን ዘርፈ ብዙ ስኬታማ ተግባራትን አከናውኗል።

ወጣቶች በእውቀት እና በክህሎት የሚገነቡባቸውን ምቹ ሁኔታዎች በመፍጠር ፣ የሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን የውጭ ሀገር የስራ ዕድል አማራጮችን በመፍጠር ዘላቂ ተጠቃሚነታቸውን ለማጎልበት አበረታች ተግባራት ተሰርተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን በመገንባት በክህሎት፣ በጤና እና በሥነ ምግባር የበቁ ወጣቶችን ለማፍራት ፅኑ መሰረት መጣሉን በመዲናችን የተገነቡ አንፀባራቂ የትውልድ አሻራዎችን ለአብነትም መጥቀስ ይቻላል።

ወጣቶች ጊዜአቸውን ፣ ጉልበታቸውን እንዲሁም እውቀታቸውን የነገ ሀገራቸውን በሚገነቡ፣ ለወገኖቻቸው አለኝታ መሆን በሚያስችሉ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ እንዲያሳርፉ የተከናወኑ ስራዎችም ተስፋ ሰጪ ናቸው፡፡

በፓርቲያችን የሚሠሩ የልማት ሥራዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ከተማችን አንዷ ማሳያ ናት፡፡

በተለይም የኮሪደር ልማቱ ተደራሽ የሆነባቸው የከተማችን አካባቢዎች ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥረዋል፡፡

በዓይነቱ የተለየ ዘመናዊ የዓይነ ሥውራን ትምህርት ቤትም በከተማችን ተገንብቶ ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ለመጡ አይነ ስውራን አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ፤ ተጨማሪ አራት የዓይነ ሥውራን ትምህርት ቤቶች ደግሞ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተገነቡ ይገኛሉ።

ለሕጻናት እና ለመጪው ትውልድ ሰፊ ትኩረት የሰጠው ብልፅግና መጪውን ትውልድ ለመገንባት የሚያስችሉ ሥራዎችን ከመሥራት በተጨማሪ፣ የወላጆችን ጫና የሚያቀሉ አበረታች እንቅስቃሴዎችን አከናውኗል፡፡

ለአብነትም በየመሥሪያ ቤቶች የተገነቡት የሕጻናት ማቆያዎች ለትውልድም የተስተካከለ ዕድገት አስተዋፅዖ እያደረጉ ሲሆን ለወላጆችም ትልቅ እፎይታን ሰጥተዋል፡፡

በየአካባቢው የተገነቡ የሕጻናት መጫዋቻዎች እና ማዘውተሪያዎች ጤናማ እና በተለያዩ ክህሎቶች የበቃ ትውልድን ለመፍጠር አበርክቷቸው ከፍተኛ ነው፡፡

በሌላ በኩል የትምህርት ቤት ምገባ እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ ድህነትን ከማቃለል ባሻገር ለተሻለ ትውልድ ግንባታ መሠረት ጥሏል።

በተለይም በመዲናችን እየተተገበረ የሚገኘው የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምም ህፃናት ተገቢውን እንክብካቤ አግኝተው እንዲያድጉ በማስቻል የህፃናቱን ብቻም ሳይሆን የወላጆቻቸውን የነገ ተስፋ እያለመለመ ይገኛል፡፡

ብልፅግና በራስ ዐቅም ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የማኅበራዊ ዋስትና ሥርዓት ለመፍጠር እየሠራ ነው፡፡ በዚህ መርሕም ለዜጎች የዕለት ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ፣ የዜጎችን ሕይወት በመሠረታዊነት የሚቀይሩ ሥራዎች ተሠርተዋል። የማዕድ ማጋራት፣ የምገባ ማዕከላት፣ የተቸገሩ ዜጎችን ቤቶች ማደስ እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ማድረግ የዚህ መርህ ውጤቶች ናቸው፡፡

የብዝኃ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንጻር ፓርቲያችን ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ በየደረጃው ተግባራዊ አድርጓል። ከዚህ አንጻር በቀዳሚነት የሚነሣው በበጎ አድራጎት ሥራዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እና የዐቅመ ደካማ አረጋውያንን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለማሻሻል የተደረገው ውጤታማ ርብርብ ተጠቃሽ ነው።

“በራሳችን ዐቅም ለተቸገሩ እና ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ዋስትና መሆን” የሚለውን የማኅበራዊ ዋስትና መርሀችንን ይበልጥ ተቋማዊ እና ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይም ብርቱ ርብርብ እናደርጋለን፡፡

በሀገር ውስጥ ሀብት የማሰባሰብ ዐቅምን በማሳደግ እና የመረዳዳት ባህልን በማጠናከር፣ በራስ ዐቅም ላይ የተመሠረተ ዘላቂ የማኅበራዊ ዋስትና ሥርዓትን እንፈጥራለን።

በተለያዩ ምክንያት የተጋለጡ ዜጎችን በዘላቂነት በማቋቋም፣ ወደ አምራችነት በማሸጋገር፣ ተረጂነትን ለመቀነስ በቀጣይም በልዩ በትኩረት ይሠራል።

ብልፅግናን ይምረጡ! ፍትሀዊ እና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ያረጋግጡ!
የመደመር ፣ የአንድነት እና የትብብር መገለጫ የሆነው የስንዴ ነዶ ምልክታችን ነው !

መልካም የስራ ሳምንት!!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት


27/04/2026

የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጉዞና በውጭ ግንኙነት ስትራቴጂዎች ላይ የሚያደርጉት ተጠባቂ የክርክር መድረክ ሐሙስ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ ይጠብቁ!

Address

ADDIS ABABA
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yasmin Gohan Beast posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category