I doubt that love itself resembles me

I doubt that love itself resembles me Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from I doubt that love itself resembles me, Grocers, Addis Ababa.

29/04/2026
20/04/2026

2 ቀናት ብቻ ቀሩት!

ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠው የምርጫ ካርድ መውሰጃ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ዛሬውኑ የምርጫ ካርድዎን በመውሰድ መብትዎን ይጠቀሙ!

የሚመራዎን መንግስት በድምፅዎ መምረጥ ይችላሉ! የምርጫ ካርድ መያዝዎን ብቻ እርግጠኛ ይሁኑ!

11/04/2026

ብዝኃነትን ጌጣችን፤ኢትዮጵያዊ አንድነትን ደግሞ የጋራ ማንነታችን በማድረግ ዘላቂ አውንታዊ ሰላም እንጠዲረጋገጥ ብልፅግና ፓርቲ ጠንክሮ ይሰራል ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃነት ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት የየራሳቸው ማንነት ያላቸው ነገር ግን እጅግ የተጋመደ የጋራ ማንነት ታሪክ እና እሴት ያላቸው ህዝቦች በጋራ የሚኖሩባት የኢትዮጵያውያን ሁሉ የጋራ ቤት ናት። ባለፉት ዘመናት ብዝሃነታችንን በአግባቡ የሚያስተናግድ ስርዓት ባለመገንባቱ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ፈተና ተጋርጦበት ቆይቷል። ብልፅግና ፓርቲ በሃገራችን ያለው ሰፊ ብዝሃነት ለኢትዮጵያ አንድነት መሰረት እንዲሆን አድርጎ መጠቀም ይቻላል ብዝሃነትም ፀጋ እንጂ ስጋት አይደለም ብሎ ያምናል በሃገራችን ያለው የብሄር የቋንቋ የባህል እና ሌሎች ማንነቶች ብዝሃነት ለኢትዮጵያ አንድነት እንደ ጸጋ ለመጠቀም የመንግስት አወቃቀሩ ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርአት መሆን አለበት ብለን እናምናለን።
ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርአት ብዛነትን የሚያስተናግድ በህዝቦች ማንነትና በሀገራዊ አንድነት መካከል ሚዛን የሚጠብቅ አካታችና አቃፊ ፌደራሊዝም እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት የብሔር ፌደራሊዝም አይደለም። አወቃቀሩም መልካም ምድራዊ አሰፋፈርን የጋራ ማንነትን እና የጋራ ፈቃደኝነትን መሰረት አድርጎ የሚተገበር ነው። በሃገራችን ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም ባለፈው ስርዓት የአተገባበር ችግር ነበረበት። ነገር ግን ከሃገራዊ ለውጡ ወዲህ የፌደሬሽኑ አባል ክልሎች በህገ መንግስቱ ተለይቶ በተሰጣቸው ግልጽ ስልጣን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ራሳቸውን ያስተዳድራሉ። በፌደራል መንግስቱ ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያን በጋራ ይመራሉ። ህብረ ብሄራዊ ብሄራዊ ፌደራሊዝም በሀገራችን ያለውን ብዝሃነት በአግባቡ በማስተናገድ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ባይተዋር እንዳይሆኑ በየደረጃው እንዲወከሉ ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በፌደራላዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች እንዲሳተፉ እና ለኢትዮጵያ ብልፅግና የድርሻቸውን እንዲወጡ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለንእናምናለን። ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝምን በሀገራዊ አንድነትና በህዝቦች ማንነት መካከል ሚዛን ጠብቆ መተግበር ህዝቦች ቋንቋቸውን ባህላቸውን እና ሌሎች ማንነቶቻቸውን እያጎለበቱ በዘመናት መካከል በተጋመደ የጋራ ማንነታቸው ደግሞ ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን በማዳበር በጋራ ትርትት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነትን መገንባት ይቻላል ብለን እናምናለን። ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርአት ለኢትዮጵያ የግዛትና የህዝቦች አንድነት መጠንከር ሁነኛ አማራጭ እንጂ የስጋት ምንጭ ሊሆን አይችልም። በፍጹም ፈቃደኝነት እና የጋራ ህልም ላይ የተመሰረተ ህብረት እና ትብብር ማረጋገጥ የሚቻለው ሁሉን አካታች አቃፊ እና አሳታፊ የፌደራል ስርአት መገንባት ሲቻል ነው ብለን እናምናለን።የፌደራል ስርአቱ ህጋዊና ተቋማዊ መሰረት ይበልጥ እንዲዳብር የተጀመሩ የሀገራዊ ሪፎርም እርምጃዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ህገ መንግስታዊ መሰረት ያለው ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርዓቱ ህጋዊና ተቋማዊ መሰረቱ ይበልጥ እንዲጠናከር የመንግስታት ግንኙነት ስርአት መወሰኛ አዋጅ ወጥቶ ተግባራዊ ተደርጓል። በዚህም በክልሎች መካከል እንዲሁም በክልሎች እና በፌደራል መንግስት መካከል መተባበር መደጋገፍ መቀናጀት እና በምክክር እና በጋራ ችግርን እየፈቱ መሄድ እየዳበረ መጥቷል። ፓርቲያችን ብልፅግና ደግሞ በራሱ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ በመሆኑ በእሳቤው በአደረጃጀቱ እና በአሰራሩ ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርአቱን የሚያጸና የኢትዮጵያን አንድነትም የሚያጠናክርአካታችና አቃፊ ተቋም ሆኗል። ኢትዮጵያን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ቤት ለማድረግ እና
በጠንካራ አንድነት ላይ የተመሰረተ ጽኑ ሃገር መንግስት ለመገንባት ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም በሀገራዊ ምክክር ይበልጥ እንዲዳብር እና በውጤታማነት እንዲተገበር ጠንክረን እንሰራለን። ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርአቱ ለዘላቂ አዎንታዊ ሰላም እና ለአንድነታችን ዋስትና እንዲሆን አስተሳሳሪ የጋራ ትርክትም አብሮ መገንባት አለበት አለበት ብለን እናምናለን። ፌደራሊዝሙን በህዝቦች ታሪካዊ ትስስር እና በሁኔታዎች የማይቀያየር የጸና አብሮነት ትርክት ላይ ገንብተን ብዝሃነትን ጌጣችን ኢትዮጵያዊ አንድነትን ደግሞ የጋራ ማንነታችን በማድረግ ዘላቂ አውንታዊ ሰላም እንዲረጋገጥ ጠንክረን እንሰራለን። ብልፅግናን ይምረጡ ብልፅግናን መምረጥ ጠንካራ የፌደራል ስርአት ማረጋገጥ ነው። ብልፅግናን መምረጥ ከሁሉም ለሁሉም በሁሉም የሆነች ሀገር መገንባት ነው።



23/03/2026

የተከበራችሁ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ እጩዎችን እንድታውቋቸው፦




23/03/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when I doubt that love itself resembles me posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category