18/04/2026
ተቀበል፤
"ጉድ እኮ ነው!
የሀገር ካባ ለብሶ፣ የመንደር ሰባኪ፣
መልአክ መስሎ መጣ፣ የሬሳ አምላኪ።
ይከፈት መዝገቡ፣ ታሪካችን ይታይ፣
ሀገር ማን ገነባ? ማነው ደግሞ ገዳይ?
ባንዳ ሀገር ሲሸጥ፣ ባልቻ በጎራዴ፣
ለይተን እንወቅ፣ ጀግናና ነጋዴ።
ለሀገሩ ብሎ፣ ህይወቱን የሰዋ፣
ይመስክር ታሪኩ፣ ይናገር አድዋ።
ምን ያደርጋል ወሬ፣ ቃላትን መደርደር?
ሞትን ሳንፈራ፣ ወድቀናል ለሀገር።
አፈር እየላስን፣ አበቃን ለበርገር፣
እኛ ያቀናናት፣ ገና ታብባለች፣
ጨፍላቂዋ ሀገር፣ እውነትም ሞታለች። (x2)"
Galaana Gaaromsaa ft Yosan Getahun