Bole prime

Bole prime Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bole prime, Grocers, Addise Ababa, Addis Ababa.

08/08/2025
03/08/2025
31/07/2025
24/07/2025

የ2017 በጀት ዓመት በቦሌ ክፍለ ከተማ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት ነበር፡፡ በበጀት ዓመቱ በመደበኛ ሥራዎች፣ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ በሰላምና ጸጥታ፣ በሰው ተኮር ተግባራት፣በሕዝብ ተጠቃሚነት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎችም መስኮች ተጨባጭ ውጤቶች ከመመዝገባቸው ባሻገር የሕዝባችንን የተጠቃሚነት ጥያቄዎች በአግባቡ በመመለስ የኅብረተሰብ እርካታን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችለናል፡፡

እነዚህን ተግባራት ስናከናውን የአመራሩ፣ የፈጻሚዎቻችን፣ የአደረጃጀቶች፣የመላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች እና የአጋር አካላት የጋራ ርብርብና ቅንጅታዊ ሥራ ወሳኝ ሚና ነበረው፡፡ ይህንን ስኬት በ2018 በጀት ዓመትም አጠናክረን በመቀጠል በተለይም መልካም አስተዳደርን በተሟላ መንገድ ለማስፈን፣ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋና ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ፣ ብልሹ አሠራሮችን በማስወገድ ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እና የቦሌ መለያ የሆነውን አቅዶ የመፈጸም ብቃትና አርአያነት ያላቸው አዳዲስ አሠራሮችን የመተግበር ሥራችንን አጠናክረን ለማስቀጠል በበለጠ ትጋትና ቁርጠኝነት ልንረባረብ ይገባል፡፡ የክፍለ ከተማችንን ውጤታማ ጉዞ ቀጣይ ለማድረግ የጀመርነውን ጥረት አሁንም በላቀ ደረጃ ለማሳካት የሁላችንም የጋራ ርብርብ ወሳኝ በመሆኑ ለዚህ ግብ በጋራ እንድንተጋ አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡

ዶ/ር እሸቱ ለማ
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

በመደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት እንዲሁም ወቅታዊ ተግባራትን አጠቃላይ አመራሩ  በተገኙበት ተገመገሙ።የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ጠቅላላ አመራር በተገኙበተ መደበኛ የመንግ...
14/12/2024

በመደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት እንዲሁም ወቅታዊ ተግባራትን አጠቃላይ አመራሩ በተገኙበት ተገመገሙ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ጠቅላላ አመራር በተገኙበተ መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ተገምግሟል።

የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አሰተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፌል ባያብል እና የወረዳ 14 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኅላፊ አቶ አለማየሁ ጊዮን መድረኩን የመሩት ሲሆን ወቅታዊ ስራዎች ከሆኑት መካከል የስራ እድል ፈጠራ ፣ የከተማ ግብርና እና የልማት ትሩፋት ስራዎች፣ የጠና መድህን ደረጃ ፣የፀጥታ ስራዎች፣የፅዳት እና ውበት ስራዎች የበጎ ፊቀድ ተግባራቶች ፣ የዲጂታል መታወቂያ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ መደበኛ የውስጠ ፓርቲ ተግባራት ያለበት ደረጃ የተገመገመ ሲሆን ስራዎችን አስተሳስሮ በመስራትና ቅንጅታዊ አሰራርን በማስጠበቅ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንደሚገባ ተገልጿል።

Bole Woreda 14 communication

Address

Addise Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole prime posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category