Biftu umer haji

Biftu umer haji Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Biftu umer haji, Grocers, Addis Ababa.

23/09/2026

የሀረሪ ቋንቋን በዲጂታል አማራጮች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው-የሀረሪ ክልል ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ

ሀረር፣መስከረም 13/2019(ሀክመኮ):-የሀረሪ ቋንቋን በዲጂታል አማራጮች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

በሀረሪ ክልል ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የቋንቋ ዳይሬክተር ወ/ሮ ያስሚን ሳላሃዲን ቢሮው የሀረሪ ቋንቋ አጠቃቀምን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ቋንቋውን የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም ተደራሽ ለማድረግ ከሶፍትዌር ባለሙያዎችና ምሁራን ጋር እየተሰራ እንደሚገኝም አክለዋል።

በዚህም ከ25 ሺህ በላይ ቃላትና የንግግር ዘይቤዎችን ያካተተ በአራት ቋንቋዎች የተዘጋጀ የቋንቋ ሶፍትዌር ሥራ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

ሶፍትዌሩ በክልሉና በውጭ አገራት ለሚኖሩ የሀረሪ ተወላጆችና ዲያስፖራዎች ቋንቋውን ለመጻፍ፣ ለማንበብና ለመማር እንዲሁም በቀላሉ ለመተርጎም የሚያግዝ ዲጂታል መሠረት መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የመንግሥት ተቋማት የክልሉን የስራ ቋንቋ አጠቃቀምን ለማጎልበት ከመምህራን ኮሌጅ ጋር በመተባበር የአጭር ጊዜ ሥልጠና ለመጀመር ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የምልክት ቋንቋን በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

በዚህ ረገድ በክልሉ ከሚገኝ የምልክት ቋንቋ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚገኙ ሠራተኞችን በምልክት ቋንቋ ለማሰልጠን ስምምነት መደረሱን አስታውቀዋል።

ቢሮው በሀረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ አማካኝነት የክልሉን ቋንቋ የሚያጎለብቱ በራዲዮና በቴሌቪዥን አስተማሪ የሆኑ ፕሮግራሞችን ለመጀመር በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biftu umer haji posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category