Mo 'J'a MO

Mo 'J'a MO Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mo 'J'a MO, Grocers, Addis Ababa.

Nageenyi Ka'umsa Waan Hundaati. Gatiin nageenyaa haala kamiinuu tilmaamuun waan hin danda’amneef, dhimma filannoo biraa ...
29/07/2025

Nageenyi Ka'umsa Waan Hundaati.

Gatiin nageenyaa haala kamiinuu tilmaamuun waan hin danda’amneef, dhimma filannoo biraa hin qabne waan ta’eef, namni hundi onneerraa waa’ee nageenyaa yaadun; nageenyaaf Itti gaafatamummaa ofii bahachuun, ambaasaaddara nageenya dhugaa ta'uu qaba.

Nagaa fi daandii nagaa filachuun mallattoo ummata onneerraa jaalachuu, dhugaaf dhabbachuufi obsuun mallattoo biyyaaf dhimmamuuti.

🕊 Nageenyi Hundaaf Hundi Nageenyaaf 🕊

🕊ሠላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው🕊።

የሰላም ዋጋ በምንም ዓይነት ሁኔታ ሊተመን የማይችል እና ለድርድር ሊቀርብ የማይገባው ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ስለሰላም ከልብ በማሰብ ፤ ለሰላም ኃላፊነትን በመወጣት እውነተኛ የሰላም አምባሳደር ሊሆን ይገባል ፡፡

ሰላምን እና የሰላም መንገድን መምረጥ ሕዝብን ከልብ የመውደድ ፣ ወገንን ስለእውነት የማክበር እንዲሁም ስለሀገር በጽናት የመቆርቆር ማሳያ ነው፡፡

🕊ሰላም ለሁሉም ፤ ሁሉም ለሰላም 🕊

 #በባቲ ወረዳ  #ሐምሌ-24 የሚካሄደው የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር በቂ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቋል።‎አቶ መሀመድ ይማምየባቲ ወረዳ ም/አስተዳደርና ግብርና ፅ...
29/07/2025

#በባቲ ወረዳ #ሐምሌ-24 የሚካሄደው የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር በቂ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቋል።

‎አቶ መሀመድ ይማም
የባቲ ወረዳ ም/አስተዳደርና ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ

‎7ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ሐምሌ 24 እንደ ሀገር 700 ሚሊየን ችግኝ ተከላ ይካሄዳል።

‎በወረዳችን በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በአንድ ጀንበር 2መቶ ሺ በላይ ችግኝ ለመትከል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

‎ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በችግኝ ተከላ የሚሳተፉበት እንደሆነና ተከላዉ ልክ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ቀኑን ሙሉ የሚደረግ እንደሆነ ተገልጿል።

‎ለተከላዉ የሚሆን ጉድጓድና የችግኝ ማጓጓዝ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን ህብረተሰቡም በችግኝ ተከላ በነቂስ እንዲሳተፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በማህበራዊ ሚዲያ የመንግስትን ስም የሚያጠለሹ እና ራሱን የአማራ ፋኖ ብሎ የሚጠራውን ጽንፈኛ ቡድን የሚደግፉ ጽሑፎች እና መልዕክቶች በማሰራጨት የሽብር ተልዕኮ ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ በሰባት...
18/06/2025

በማህበራዊ ሚዲያ የመንግስትን ስም የሚያጠለሹ እና ራሱን የአማራ ፋኖ ብሎ የሚጠራውን ጽንፈኛ ቡድን የሚደግፉ ጽሑፎች እና መልዕክቶች በማሰራጨት የሽብር ተልዕኮ ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ በሰባት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

13/06/2025

መንግስት ሰላም እንዲመጣ ከሚፈልግ ማንኛውም አካል ጋር በትብብር ለመስራት እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

 #ለተከታታይ አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ8ኛና የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የባቲ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ መሀመድ አብዱ ገለፁ! በባቲ ወረዳ አስተዳደር ከሰኔ 3 እ...
13/06/2025

#ለተከታታይ አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ8ኛና የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የባቲ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ መሀመድ አብዱ ገለፁ!

በባቲ ወረዳ አስተዳደር ከሰኔ 3 እስከ 6/2017 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የ8ኛና 6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የባቲ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል።

በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የተመደቡ የወረዳ አመራሮች የፀጥታ አካላት ፣ ፈታኞች ፣የቀበሌ አመራሮች፤ ሱፐርቫይዘሮችና የፈተና አስፈፃሚዎች የተጣለባቸውን ሀላፊነት በአግባቡና በትጋት በመወጣታቸው ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

“ሕዝብ በአንድነት ሲነሳ የማያሸንፈው ጠላት የለም”አቶ ይርጋ ሲሳይየአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ
12/06/2025

“ሕዝብ በአንድነት ሲነሳ የማያሸንፈው ጠላት የለም”

አቶ ይርጋ ሲሳይ
የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ

በደቡብ ጎንደር ዞን በእብናት ወረዳ ባላርብ ቀበሌ በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በሰላማዊ መንገ...
31/05/2025

በደቡብ ጎንደር ዞን በእብናት ወረዳ ባላርብ ቀበሌ በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ሃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በሰላማዊ መንገድ ገብተዋል።

Amhara Prosperity Party /APP/

Ida'amuu, Furmaata Rakkoolee Keenyaa!******************************************Paartiin Badhaadhinaa yaadama Ida'amuutii...
30/05/2025

Ida'amuu, Furmaata Rakkoolee Keenyaa!
******************************************
Paartiin Badhaadhinaa yaadama Ida'amuutiin faayamee tokkummaa sabdaneessummaa sadarkaa hundatti dhugoomsuuf hojjachuu irratti argama.

Itoophiyaan biyya sabdaneettii, heddumminni aadaa, afaan, amantaa fi eenyummaan lammiilee miidhagina ta'anii itti mul'atan ta'uu isheetiin yaadamni Ida'amuu tokkummaa Itoophiyaanotaa jabeessuudhaan galma badhaadhina waloo dhugoomsuudhaaf daandii murteessaa fi filatamaadha.

Ida'amuun ilaalama "nuti hundi ni barbaachifna, nu keessaa kan hin barbaachifne hin jiru" jedhu kan tarkaanfachiisu akkasumas gufuuwwan tokkummaa fi obbolummaa maqsuudhaan jaalala fi dhiifama kan diriirsu yaadama mo'ataa, furmaata rakkoolee hundaa ta'edha.

Mul'atni Paartii Badhaadhinaa fi yaadamni inni hordofu Itoophiyaanota mara daandii bu'a qabeessa irra imalchiisuun badhaadhinatti kan qajeelchuu fi tokkummaa cimaa obbolummaa dhugaa bu'uureffate lammiilee gidduutti kan diriirsuudha.

Yaadama ida'amuutiin dabaalamnee galma badhaadhina waloo dhugoomsuudhaaf tokkummaan haa sochoonuu.

የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በዛሬ ምሽት በከሚሴ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ጉብኝት አካሄዱ።በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በ...
23/05/2025

የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በዛሬ ምሽት በከሚሴ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ጉብኝት አካሄዱ።

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በዛሬ ምሽት በከሚሴ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ጉብኝት አካሂዷል።

በጉብኝት መርሀ ግብሩ የአማራ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ እብሬ ከበደ፣ የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አላምር ተሻለ፣የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ አባ-አፍሮ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ሁሴን ሙሐመድን ጨምሮ ሌሎች የዞንና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ባለሙያወች ተገኝተዋል።

የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር ትስስር ያለው እና ሰው ተኮር ልማት መሆኑ እና ጠንካራ የህብረተሰብ ተሳትፎና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትም የታየበት መሆኑ ተገልጿል እንድሁም የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት በቀንና ምሽት መስራት መጀመሩ ተገልጿል።

ከተሞቻችን ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም የዋጁ እንዲሆኑ፣ ለቀጣይ ትውልድ እንዲሸጋገሩ መሰራት እንዳለበት በጉብኝት መርሀ ግብሩ ተገልጿል።

"‎ሚዲያን አመራሮቻችን አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን በጤናማ መንገድ መጠቀም ከቻሉ የፓርቲያችን የለውጥና የብልፅግና እሳቤዎች በአግባቡ ሰርፀው የህዝባችንን ኑሮ በሚያሻሽል ወሳኝ ተግባራት ላይ የ...
23/05/2025

"‎ሚዲያን አመራሮቻችን አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን በጤናማ መንገድ መጠቀም ከቻሉ የፓርቲያችን የለውጥና የብልፅግና እሳቤዎች በአግባቡ ሰርፀው የህዝባችንን ኑሮ በሚያሻሽል ወሳኝ ተግባራት ላይ የልምድ መቅሰሚያ ሆኖ ልያገለግል ይገባል"።

ክቡር አቶ አህመድ ሁሴን ሙሀመድ
‎በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኀላፊ

የጫካ ቆይታቸው ለወገናቸው ያተረፈለት የማይረሳ ጠባሳ እንደኾነ ለሰላም ጥሪው ምላሽ የሰጡ ኀይሎች ገለጹ። በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ሬማ ከተማ መንግሥት ላቀረበው የሰላም ጥሪ ምላሽ ...
22/05/2025

የጫካ ቆይታቸው ለወገናቸው ያተረፈለት የማይረሳ ጠባሳ እንደኾነ ለሰላም ጥሪው ምላሽ የሰጡ ኀይሎች ገለጹ።

በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ሬማ ከተማ መንግሥት ላቀረበው የሰላም ጥሪ ምላሽ የሰጡ ኀይሎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበሉ ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ የክልሉ እና የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ101ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማቲያስ ማዴቦ ተገኝተዋል።

ለሰላም ጥሪው ምላሽ የሰጡ ታጣቂ ኀይሎች አሳዝነነው ይቅር ያለንን ወገናችንን ሰላሙን በመስዋዕትነት እንጠብቃለን ብለዋል።

የጫካ ቆይታቸውም ለወገናቸው ያተረፈለት የማይረሳ ጠባሳ ነው ብለዋል።

ወንድም ወንድሙን ከሚገድልበት የትግል መንገድ በመውጣት ወደ ሰላማዊ ትግል መመለሱ የተሻለ እንደኾነም ተናግረዋል።

ዛሬም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኀይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ቀያቸው ተመልሰው በሰላም ወላጆቻቸውን እና ልጆቻቸውን እንዲቀላቀሉም ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ መንግሥት ባቀረበው የሰላም ጥሪ በርካታ ኀይሎች በሰላም ወደ ቀያቸው መግባታቸውን ነው የገለጹት።

የመንግሥት የሰላም ጥሪ ዛሬም እንደቀጠለ እንደኾነ የተናገሩት የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኀይሎች ለሰላም ጥሪ ምላሽ የሰጡትን ወንድሞች አርዓያነት በመከተል ለሕዝቡ ሰላም እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

ዞኑ ከክልሉ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ወደ ሰላም የተመለሱ ኀይሎችን ወደ ቀድሞ ሰላማዊ ሕይዎታቸው ለመመለስ የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የሃይማኖች አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ዛሬም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኀይሎች ወደ ቀያቸው እንዲመጡ የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም አደራ ብለዋል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"

22/05/2025

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mo 'J'a MO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category