Badrii bahar

Badrii bahar Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Badrii bahar, Grocers, Dire, Addis Ababa.

16/05/2026
16/05/2026
16/05/2026
16/05/2026
16/05/2026
15/05/2026

በክልሉ ባለፉት አምስት ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት አስገኝቷል

በሐረሪ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማስገኘታቸውን የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ አስታወቀ።

የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ኢማን መሀመድ ባለፉት አምስት ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶች በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አምራች ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ሀይል እንዲያፈሩ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍን የኮሌጆችን ደረጃ ማሻሻል፣ የግብዓት አቅርቦትን ማሟላትና የመምህራን አቅም የማሳደግ ስራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ስለመሰራቱ ገልጸዋል።

በክልሉ በተለይም በሀረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማስፋፍያ ግንባታ እንዲሁም በኤረር ወረዳ መለስተኛ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከል መገንባት መቻሉን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደረጃቸውን የጠበቁ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መጽሀፍት፣ ቤተ ሙከራዎች እና የአስተዳድር ህንጻ የተሟላላቸው መደረጉን ነው የገለፁት።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የኢንዱስትሪ ልማቱን ከመደገፍ ባሻገር ለዜጎች ኑሮ መሻሻልና ምቹ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።

የስራ ገበያውን ፍላጎትን መነሻ በማድረግ በመደበኛ መርሀ ግብር 32 ሺህ 518 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን መቻሉን አክለው ገልጸዋል።

በገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠና ከ14 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን መቻሉን ገልጸዋል።

የስልጠናዎቹም በዋናነት በሆቴል፣ሀገር በቀል ሙያዎች:- ባህላዊ የሰፌት ሙያ፣በኮንስትራክሽን ጂብሰም፣በፀጉር ስራ፣ በከተማ ግብርና ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በቧንቧ ዘርፎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በቀጣይም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተመዘገቡ ዉጤቶችን ተጠናክረው ይቀጥላል ብለዋል።

Address

Dire
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Badrii bahar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category