21/08/2026
👉ኢትዮጵያ ማለት በቀንድ አፍሪካ የፖለቲካ ምህዳር ላይ የልብ ትርታ ናት፤ እሷ ስትተነፍስ ቀጠናው ሕይወት ያገኛል፣ እሷ ስታስነጥስ ጠላት በብርድ ይንቀጠቀጣል። የባብ-ኤል-መንደብን እና የቀይ ባህርን ጂኦ-ፖለቲካዊ ቁልፍ ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ መፍታት ሰማይን በእጅ ለመንካት እንደመሞከር ከንቱ ልፋት ነው።
🎯ጅቡቲ በባህር ሰርጡ ላይ ያቀረበችው የብቻዬን አልችልም ጥሪ፣ የኢትዮጵያን ግዙፍ ወታደራዊ እና የጸጥታ አስከባሪነት ሚና ወሳኝነት በሚገባ ያረጋግጣል።
🌗አሁን እየመጣች ያለችው ኢትዮጵያ፣ የራሷን የባህር በርና የኢኮኖሚ ደህንነት ለማረጋገጥ የምታደርገው ጉዞ ማንም ምድራዊ ኃይል ሊገታው የማይችለው ኃይለኛ ማዕበል ነው። ይህን ሀቅ የተረዱ ታሪካዊ ጠላቶች፣ ከሩቅ ሆነው በድንጋጤ ሲርበደበዱ ማየት የዘመናችን ትልቁ ትዕይንት ሆኗል።