Frut Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Frut, Grocers, Addis ababa, Addis Ababa.

25/08/2025
21/07/2025

ትራምፕ የሕዳሴ ግድብ "የተገነባው በአብዛኛው በአሜሪካ ገንዘብ ነው" ሲሉ ለሦስተኛ ጊዜ ተናገሩ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ "የተገነባው በአብዛኛው አሜሪካ ገንዘብ ነው" ሲሉ ለሦስተኛ ጊዜ ተናገሩ።
ትራምፕ ይህንን አወዛጋቢ አስተያየት የሰጡት በዋይት ሐውስ ለሪፐብሊካን ሴናተሮች የእራት ፕሮግራም ባደረጉበት ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም. ምሽት ነው።
በዓለም ላይ ያሉ ጦርነቶችን ሰላማዊ እልባት ለመስጠት አገራቸው እያደረገችው ያለውን ጥረት በማጉላት የተናገሩት ትራምፕ ግብፅ እና ኢትዮጵያ "በሕዳሴ ግድብ እየተጣሉ መሆኑን ታውቃላችሁ" ብለዋል።
በመቀጠልም ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ አገራቸው ለሕዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ መስጠቷን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሁለት ጊዜ የተናገሩት ትራምፕ በሦስተኛው እና በአሁኑ ንግግራቸው ላይ ጠንከር ባለና አጽንኦት በመስጠት ነው የደገሙት።
"ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችው በአሜሪካ ገንዘብ ነው፤ በአብዛኛው" ሲሉ የተናገሩት ትራምፕ አገራቸው መቼ ገንዘቡን እንደሰጠች ወይም በምን መልኩ እንደሆነ ያሉት ነገር ግን የለም። ትራምፕ ሐምሌ ሐምሌ 7/2017 ዓ.ም. ከኔቶ (የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት) ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩተ ጋር በዋይት ሐውስ ባደረጉት ውይይት ስለ ግብፅ እና ግድቡ በጠቀሱበት ወቅት "አላውቅም፤አሜሪካ ለግድቡ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገች ይመስለኛል" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። አምስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ የተበጀተለት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ የተገነባው ሕዝቡ ባወጣው ገንዘብ እና አገር ውስጥ ባለ ሃብት እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የትራምፕን ይህንን "ሕዳሴ የተገነባው በአሜሪካ ገንዘብ ነው" የሚለውን ንግግራቸውን አስመልክቶ በይፋ ትክክል እንዳልሆነ ካለመግለጽ በተጨማሪ ዝምታን መርጠዋል። ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ ላይ ያላት ድርሻዋን ባረጋገጠ መልኩ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም ላይ ስምምነት እንዲደረስ እና ግንባታው የግብፅን የውሃ ደኅንነት ላይ አደጋ እንደማይጋርጥ ስታስታውቅ ቆይታለች።
ግድቡን በሚመለከት በተከታታይ ሲካሄዱ የነበሩ የሦስትዮሽ ድርድሮች አንዱ ወገን ሌላኛውን ለድርድሩ አለመሳካት ተጠያቂ በማድረግ ያለውጤት መበተናቸው ይታወሳል።
በግድቡ የውሃ ሙሌት እና ከግድቡ በሚለቀቀው የውሃ መጠን ላይ ሕጋዊ እና አስገዳጅ ሦስትዮሽ ስምምነት ካልተፈረመ ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌቱን ማከናወን እንደሌለባትም ስትወተውት የቆየችው ግብፅ ከሰሞኑም ይህንኑ በመድገም አስጠንቅቃለች።
በአምስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከአስር ዓመታት በላይ አስቆጥሮ በመጪው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ በይፋ እንደሚመረቅ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

ጎንደር ዩኒቨርስቲ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 14 የቀድሞ ምሩቃን ልዩ ዕውቅና ሰጠ !ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 2500 ተማሪዎችን አስመርቋ...
19/07/2025

ጎንደር ዩኒቨርስቲ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 14 የቀድሞ ምሩቃን ልዩ ዕውቅና ሰጠ !

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 2500 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ምስረታን በትላንትናው ዕለት የፋ ሲያደርግ በዛሬው ዕለት ደግሞ በ13 ዘርፎች ለ14 የቀድሞ ምሩቃን ልዩ ዕውቅና ሰጥቷል።

የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያውን ምረቃ ያካሄደው ሰኔ 30 ቀን 1949 ዓ.ም እንደነበር እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 66 ዓመታት 107 ሺ 860 ሙህራንን ማፍራቱን አስታውሰዋል።

ከእነዚህ ሙህራን መካከል በ13 ዘርፎች በሙያቸው በጎ ትፅዕኖ የፈጠሩ 14 ሙህራንን ዩንቨርስቲው ዕውቅና ለመስጠት መወሰኑን አስረድተዋል።

ጎንደር ዩኒቨርስቲ በምን ዘርፍ ለየትኞቹ የቀድሞ ተመራቂዎች ልዩ ዕውቅና ሰጠ ?

1. የፕሬዚዳንታዊ ሌጋሲ ከፍተኛ ሽልማት ዘርፍ
- ፕ/ር መንገሻ አድማሱ (የቀድሞው የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት)
- ፕ/ር ያሬድ ወንድምኩን (የመጀመሪያው የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት)

2. የማኅበረሰብ ተጽዕኖ የላቀ ሽልማት (Community Award)
- ፕ/ር ብሩክ ላጲሶ

3. ዓለም አቀፋዊ የመሪነት ዘርፍ (Global Leadership Award)
- ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ (የቀድሞ የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ (ጤና) ሚኒስትር

4. ወጣት ሥራ ፈጣሪና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዘርፍ
- አቶ ጃለታ ሙላቱ

5. በጎንደር ዩኒቨርስቲ ድጋፍ እና አጋርነት ዘርፍ
- ዶ/ር ካሱ ከተማ

6. በትምህርት እና ምርምር ልኅቀት ዘርፍ
- ዶ/ር ኤርሚያስ ዲኖ

7. በህዝባዊ አገልግሎት ዘርፍ (Public Service Award)
- ዶ/ር ተዋበች ቢሻው (የመጀመሪያዋ ሴት ጤና መኮንን)

8. በህይወት ዘመን አበርክቶ ዘርፍ
- ፕ/ር ጉታ ዘነበ

9. በጤናና ሰብዓዊ አገልግሎት ዘርፍ
- ዶ/ር ፈቀደ አጉዋር

10. በባህል፤ በመገናኛ ብዙኀን እና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ
- አቶ ስለሺ ግርማ ( በአሁኑ ወቅት የቱሪዝም ሚኒስትር ሚ/ዴኤታ)

11. በሥራ ፈጠራና ኢንቨስትመንት ዘርፍ
- ዶ/ር ግርማ አባቢ

12. በዲያስፖራ አምባሳደርነት ከፍተኛ ተሸላሚ
- ዶ/ር ኑሩ አብሲኖ

13. ልዩ የሰብዓዊ አገልግሎት ሽልማት (Social Humanitarian Impact Award)
- ወጣት ዳዊት አየነው

እጩዎችን የማሰባሰብ እና ድምጽ የማሰባሰብ ሥራ ተሰርቶ ተሸላሚዎቹ መለየታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር

ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የመንግስት ደጋፊ ነህ ተብሎ በዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደ ባለው ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ የአልበም ምርቃት በፌስቡክ ፔጁ ሼር በማድረግ ደስታውን የገለፀ ሲሆን የህዝቡ ተ...
19/07/2025

ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የመንግስት ደጋፊ ነህ ተብሎ በዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደ ባለው ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ የአልበም ምርቃት በፌስቡክ ፔጁ ሼር በማድረግ ደስታውን የገለፀ ሲሆን የህዝቡ ተቃውሞ እያየለ ሲመጣ ግን ከግል ፌስቡክ ገፁ አንስቶታል !

ድምፃዊ ያደረገው ድርጊት ትክክል ነው ብለው ያስባሉ

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Frut posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category