Yene bestu

Yene bestu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yene bestu, Grocers, As, Addis Ababa.

24/05/2024
24/05/2024

ለችግሮች የማይበገር የለውጥ ጉዞ ፤ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት በሆነችው አዲስ አበባ!!

ከየትኛውም የአገራችን አካባቢ ፣ ከየትኛውም የዓለም ጫፍ ፣ ከየትኛውም አቅጣጫ በየብስም ሆነ በጠፈር ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሰዎች ታይቶ የማይጠገብ ፣ ጠዋት አይተው ማምሻውን ደግመው ለማየት የሚጓጉትን የልማት እንቅስቃሴዎችን ያያሉ።

ቁጭ ብለው አላፊ አግዳሚውን እያየ የሚውል የነበረው ጥቂት ወጣትን ጨምሮ ሌሎች በየትኛውም የከተማችን ክፍል ቀንም ሆነ ማታ የሚታትሩ ዜጎችን የማየት ዕድላቸው በእጅጉ ሰፍቷል።

የኮንስትራክሽን ዘርፉ በጥራትም በአፈፃፀምም አበረታች ለውጥ ላይ ይገኛል። ከለውጡ በፊት የሚቀመጡ የመሰረተ ድንጋዮች ከመብዛታቸው የተነሳ አይደለም ለመፈጸም የት የት እንደሆኑ ተረስተው የሚቀሩ ፕሮጀክቶች እንደነበሩ በተለይም ለከተማችን ነዋሪ ምስክር አያሻውም።

ፓርቲያችን የሚመራው መንግስታችን ካመጣቸው እመርታዊ ለውጦች ውስጥ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ መሆኑን በልበ ሙሉነት መናገር ይችላል ፤ ለልማት የፈካው የነዋሪዎቻችን ፈገግታም ይህንኑ ለውጥ ያሳብቃል። ብልፅግና ቃሉን ሳይሸራርፍ የሚፈፅም የተግባር ፓርቲ ነው። የጠራ አቅጣጫ ስላለን ፣ መዳረሻች ብልፅግና መሆኑን ስላስቀመጥን 7/24 እንተጋለን።

አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ እናደርጋታለን ብለን ስንነሳ ያረጁ የጎሰቆሉ ሰፈሮችን ቀለም በመቀባባት ብቻ ሳይሆን ፣ መቀየር ያለበትን እየቀየርን ፣ ታሪካዊ ይዘታቸውን ጠብቀው መሄድ ያለባቸውን ተጨማሪ ግብአት በመጨመር ለትውልድ ለማቆየት የተሰራው ስራ የፓርቲያችንን ተግባራትን ከፍ ባለ ደረጃ የመፈፀም አቅም የሚያሳይ ሲሆን ፤ የነዋሪዎችንም የአካባቢውንም ገፅታ በመቀየር የተሰራ መሆኑ የሚበረታታ ነው።

በአዲስ አበባ ትላንት የነበረ ዛሬ የማይገኝበት ግን ደሞ ከነበረዉ በላይ በሰዎች ልብ ዉስጥ የሚታተም ታሪክ ሆኖ የሚገኝበት፣ ዛሬ ያልነበረ ነገ የሚገኝበት አስደማሚ ለውጥ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

አዲስ አበባ እንደ ስሟ አበባ ሆና ትሰራለች ፣ ትገነባለች፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎችም ሆኑ ከውጭ ወደ አዲስ አበባ የሚመላለስ ማንኛውም ሰው በከተማችን ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ካስተዋለ በለውጥ እና በብልፅግና ጉዞ ላይ መሆኗን ያረጋግጣል።

ለውጡ አልጋ በአልጋ አይደለም። በኢኮኖሚም በቴክኖሎጂም ሀያላን የሆኑ ሀገሮችን ጭምር በእጅጉ የፈተነው እና የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈው ኮሮና ፣ ድርቅ እና ሌሎች በአየር ንብረት ለውጥ የተከሰቱ ተግዳሮቶች እኛንም ሳይፈትኑን ቀርተው ሳይሆን ፥ ለችግር ሳንንበረከክ ፣ ለፈተናዎች ሸብረክ ሳንል ፣ ከችግሮቹ ባሻገር እየተመለከትን አይናችንን ከራዕያችን ላይ ስላልነቀልን ችግሮችን ተቋቁመን ስኬቶችን አስመዝግበናል።

በውስጥ እና በውጭ ፀረ -ሰላም ሀይሎች በግልፅ እና በስውር በተከፈቱ ጦርነቶችና ግጭቶች እንዲሁም ታይተው የማይታወቁ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች የለውጥ ግስጋሴያችን ላይ እንቅፋት ቢደቅኑም ፤ በአስተውሎት ተራምደን ፣ ከፊታችን የገጠመንን ዳገት በብልሀት ተሻግረን ፣ ዋነኛው አቅማችን የሆነው ህዝባችን በፈተናዎች ሁሉ ከጎናችን ስለተሰለፈ ሁሉንም በድል እየተሻገርን መዳረሻችን ወደ ሆነው ብልፅግና መገስገሳችን ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የአዲስ አበባ ስኬታማ የብልፅግና ጉዞ ይቀጥላል...!!



24/05/2024
24/05/2024

የመደመር ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን ይገነባል!!

የመደመር ትውልድ በሀገራችን ህብረ-ብሄራዊ አንድነት፣ ወንድማማችነትና እህታማማችነትን በአሰባሳቢው ገዥ ትርክት የሚመራ እና በሁለተኛ የአርበኝነት ምዕራፍ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋግጥ እየተጋ ያለ የነገዋን የሃገራችንን መፃዒ ዕድል የሚተነብይ ባለራዕይ ትውልድ ነው።

የመደመር ትውልድ የኢትዮጵያ እና የህዝቦችዋ ምሰሶ የሆነው የህብረ-ብሄራዊ አንድነት ትርክት ገዥ ዕሳቤ ሆኖ እንዲወጣ፣ ሚዲያዎች ወንድማማችነትና እህትማማችነትን የሚያስተጋቡ ትክክለኛ የኢትዮጵያዊያን ድምፅ እንዲሆኑ በማድረግ እየተገነባ ነው።

ይህ ትውልድ በሁሉ ለሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት የአብሮነት፣ የህብረ-ብሄራዊ አንድነት፣ የወንድማማችነትና እህታማማችነትን ትርክት በህዝቡ ውስጥ የሚስረፅ በተቃራኒው ደግሞ ዘርፈ ብዙ የጥላቻና አፍራሽ ትርክቶችን የሚገራ ነው።

አባቶቻችን በአድዋ ድል የውጭ ወረራን በአንድነት በመመከት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ያስከበሩበትና የጥቁር ሕዝቦችን የነፃነት ቀንዲል ያረጋገጡበትን ደማቅ ታሪክ የሰሩ ሲሆን የመደመር ትውልድ ደግሞ በሁለተኛው የአርበኝነት ግንባር፥ በልማት እና ድህነትን በመታገል ኢትዮጵያን ከልመና፣ ድህነት እና ጉስቁልና በማላቀቅ የበለፀገች ኢትዮጵያን በመገንባት የራሱን ደማቅ አሻራ ለማኖር የሚተጋ የዛሬው የሃገር ባለውለታ እና የነገው አርበኛ ትውልድም ነው።

24/05/2024

ዘላቂ እና አዎንታዊ ሰላም ፤ ሁለንተናዊ ብልፅግናዋ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ላይ እየሰራ ያለ ፓርቲ - ብልጽግና!

ፓርቲያችን ሀገራችን ህልውናዋ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ትቀጥል ዘንድ ሰላሟ ሊጠበቅላት ይገባል ብሎ ያምናል። በመሆኑም ማህበራዊ ሀብቶቻችንን በመጠቀም ህዝብና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍና በማስተባበር የሰላም ባህል በመገንባት፤ የህግ የበላይነትን በማስከበርና ፍትህን በማስፈን እንዲሁም ሀገራዊ መግባባትን በማጎልበት ፓርቲያችን ግጭትን ማስቆም፣ ዕምቅ ግጭቶችን ለማምከን እና ዘላቂ አዎንታዊ ሰላምን ለማስፈን ይሰራል።

ፓርቲያችን ከህብረተሰብ ውስጥ የሚጀምር የሰላም እንቅስቃሴ ከየትኛውም መንግስታዊ ኃይል በላይ ሀገርን በሰላም የመምራት ታላቅ ጉልበት አለው ብሎ ያምናል። በመሆኑም ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እንዲቻል በህብረተሰቡ ውስጥ የግጭት ቀስቃሽ አስተሳሰቦችና ተግባራትን የሚጠየፍ ህዝባዊ ባህልን ለማዳበር በተቀናጀ መልኩ ይታገላል፡፡

ፓርቲያችን ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ግብ ከዴሞክራሲ፣ ከመልካም አስተዳደር እና ከልማት ፕሮግራሞቻችን ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንደሆነ ያምናል። በመሆኑም አዎንታዊ ሰላምን ለማረጋገጥ የልማት ስራዎችና ፍትሃዊነት ማረጋገጥ፤ ያልተማከለና አካታች የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት ብዝሃነትን ማክበር እንዲሁም የጋራ ህልምና ራዕይ በመፍጠር ለጋራ ዓላማ ስኬት በጋራ መንቀሳቀስ የሚያስችል የሀገረ-መንግስት ግንባታ ስራዎችን አቀናጅቶ በመስራት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ይሰራል::

የህግ እና የፍትህ ተቋማት ተፈጥሯዊ ተግባራቸው የሆነውን ህግና ስርዓት ለማስፈን የሚያገለግሉ ዓላማን ያነገቡ ቢሆንም ዜጎችን አፍኖ እና ጨቁኖ ለመግዛትና የገዥዎች ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ እንዳይውሉ ፓርቲያችን የህግና የፍትህ ተቋማት መሰረታዊ ዓላማ እና ተግባር የዜጎችን መሰረታዊ ነፃነት፣ መብት፣ እኩልነት በሚያከብር እና የጋራ ጥቅም፣ ማህበራዊ ፍትህ፣ ብልጽግና፣ ሰብአዊ ደህንነትን በሚያረጋገጥ መልኩ ህግና ስርዓትን ለማስፈን ይታገላል፡፡ የህግ ገዥነት መርሆች ማስከበር የሚያስችል እንዲሁም መንግስት ማህበራዊ እና ተቋማዊ የሆነ የህግ ገዥነት ባህል መፍጠር እንዲችል የሚያግዝ ንቁ የሆነ የህብረተሰብ ተሳትፎ እንዲኖር ይታገላል፡፡

ዘመናዊና ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በጣምራ በመጠቀም፣ ዕምቅ ግጭትን ማወቅ፤ የቅድመ ዝግጁነትና የምላሽ አቅምን በማዳበር ግጭትን ማምከን እና በትምህርትና በሚዲያ የታገዘ የህብረተሰብ ሰላማዊ ባህልን በማዳበር ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ፓርቲያችን ይታገላል ፤ መሰረታዊ ለውጦችንም ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በማሳየት ለሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ምቹ መደላድል እየፈጠረ ይገኛል።



Address

As
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yene bestu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category