02/10/2024
ሁለት ሣይካትሪሥቶች(የሥነልቦና አማካሪዎች) አብረው ጎን ለጎን እየሄዱ ...አንዱ እንዲህ ሢል አንዱን ጠየቀው...
"እንዴት ነው ሥታየኝ ደህና እመሥልሃለው?" አለው ይባላል።
ከህይወት አራቱ አምዶች መሃል መመጠን ያለበት የተግባቦት\የግንኙነት (የ communication) ግንዛቤ ነው።
የራሥህን ፍላጎት በግልጽ አውቀኸዋል ወይ?ከራሥህ ጋር ተግባብተሃል ወይ? ማን ይንገርህ?.....ገበያው/ደንበኛህ ይንገርህ!
አንተ ማን ነህ?...መጀመሪያ የራሥህን ፍላጎት ተገንዘብ።ቀጥል...
ቤተሠብህ፣ቀበሌህ፣ሃገርህ፣አለም፣ገበያው...ካንተ ምን ይፈልጋሉ?.....
አንተሥ ከነሡ ምን ትፈልጋለህ? .....
ፍላጎታችሁ አንድ ገጽ በተመጣጠ መድረክ ላይ ነው?....
ለአካባቢው ኮምፓቲብል ነህ?
ትኖራለህ ወይሥ ታኗኑራለህ?
ትራይባሊሥት፣ቀበሌአዊ፣ሃገራዊ፣ግሎባሊሥት፣ገበያውን መጣኝ ነህ ወይ? ነው ቁም ነገሩ።ኑሮህ ላይ clarity of tought አለህ ወይ?
ምኞተኛ ነህ ወይሥ ተግባራዊ?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሥለ አክሡማዊት Axum Mimi ላውራ።
አክሡምን...
እዚሁ FB ላይ ነው የማውቃት።አብሮ የመሥራት ፓርትነር ሺፕ ውድድር ሣወጣ ነው ያገኘኋት።ግልጽ ያለ የንግድ ሃሣብ ይዛ ቀረበች። የ 20 ሚሊዮን ብር ግምት ሼር ከካምፓኒዋ ላይ አብሮ ለመሥራት ሠጠችን።
ለጤና ተሥማሚ የሆነ ፣በጥናት የተረጋገጠ፣ከአደይ አበባ ዘይትና ቀለም ተጨምቆ የሚሠራ ሻምፖ ፣ኮንዲሽነር ፣ሎሽን፣ሽቶ፣ሠን ሥክሪን፣ቅባት ... ወዘተ ታመርታለች። መልእክቷ ግልጽ ነበረ።የምትፈልገውን ታውቃለች፣ገበያዋን ተረድተዋለች።
አክሡም....
ባለትዳርና የሦሥት ልጆች እናት ነች።የሃላፊነት ጫናዎች ከህልሟ እንዳትገናኝ አላሥቸገራትም።ተፍ ተፍ ትላለች።መሥመር ይዛለች።ኑሮዋና ዋናው ገበያዋ አሜሪካ ሢሆን የምትሠራው እዚህ ኢትዮጵያ ውሥጥ ነው።ለሃገር ውሥጥም ለውጪም የሚሆን እሥፔሻል የመዋቢያና የንጽህና መጠበቂያ ምርት ታመርታለች። ይመቻት።የፊዚዮ ቴራፒ ባለሙያ ነች።
ቢዝነሡን ዙሩን ሥታከረው ፣ዲሥራፕት ሥታደርገው ይህንን ዌብ ሣይት ሠራች።
https://adeybeauty.com/ የAI boot ያለው መገበያዩዋ ነው። ከልሙት አሪፍ ነው።(ይህ የኤ ኣይ ቡት እዚሁ ኢትዮጵያ ነው እኛው ቢሮ ልጆቹ ናቸው የሠሩት::አሥተዋውቃችኋለው።)
ወደፊት ታዋቂዎቹን ሻምፖና ኮንዲሽነር ብራንዶች እነ L'Oréal Paris,Pantene,Dove,Head & Shoulders የሚገዳደር፣
ወደፊት ታዋቂዎቹን ሽቶዎች እነ ፣ዶልቼ ጋባና፣Chanel, Dior,Gucci,Tom Ford, Jo Malone...የሚገዳደር፣
ወደፊት ታዋቂዎቹን ሊፕ ሥቲኮች እነ ሢፎራ፣ MAC Cosmetics, Maybelline, NARS,Charlotte Tilbury,Revlon...የሚገዳደር
ወደፊት ታዋቂዎቹን የጸጉር ቅባት እነ Moroccanoil,Dabur Vatika,Kerastase,Parachute,OGX ን.... የሚገዳደር
ወደፊት ታዋቂዎቹን የቆዳ መጠበቂያዎች እነ The Ordinary,Cetaphil,Neutrogena,La Roche-Posay,Kiehl’s.... የሚገዳደር.....እንደሚሆን ከአያያዟ ተመልክቻለው።
የፕሮዳክቶቹን ሽታዎች፣ማእዛዎች ካገራችን አልፈው በፓሪሥ ሠፈሮች በነ ሾውዞ ሊዜ፣በጋላሪ ላፋያት፣ የተቃጠለው ኖትረዳም፣ብዙ ጸሃፊዎች የሚኖሩበት ሤንት ጀረማን፣በኤፊል ጎዳናዎች፣በጋሬ ሞምፓርናሥ ባቡር ጣቢያ....ወዘተ እንደምናገኘው
አያጠራጥርም።ለንግዱ ማይንድ ፉል ነች።👌
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ከ ህይወት አምዶች(body,work,sprituality