18/10/2026
ሰላም ማረጋገጥ የጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን የማይቀለበስ ቃል ኪዳን ነው
ሠራዊታችን የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር እያደረገ ላለው ታላቅ ተጋድሎ እና ሕግ የማስከበር አመርቂ ውጤቶች ያለውን ሙሉ ድጋፍ ከህዝብ አገኝቷል። የኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እኅታማችነት አርማ የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን እንደግፋለን! የመከላከያ ሠራዊታችን፣ የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎቻችን ለሀገር ሰላም እና ሕልውና የከፈሉት መሥዋዕትነት ሁልጊዜም በወርቃማ ታሪካችን ውስጥ ከፍ ያለ ክብር የሚሰጠው ነው።
የእስካሁኑ ድል የሀገራችንን የወደፊት ብሩህ ተስፋ እና የማይታጠፍ ራዕይ ግልጽ አድርገው ያሳዩ ናቸው። “ከግድቡ ወደ ወደቡ እንሸጋገራለን! የባሕር በር ባለቤትነታችን በልጆቿ መሥዋዕትነት እውን ይሆናል!” በሚሉ መፈክሮች የኢትዮጵያ ታሪካዊ የመልማት እና የታላቅነት ፍላጎት በጎላ ድምፅ ተንጸባርቋል።
የሀገራችንን ሰላም ለማወክ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር የተሰለፉ ኃይሎችን በጽኑ ያወገዙት ሰልፈኞቹ፣ የኢትዮጵያ አንድነት እና እድገት በፀረ-ሰላም ኃይሎች ሴራ በጭራሽ እንደማይደናቀፍ አረጋግጠዋል። ለድል የተወለደው መከላከያ ሠራዊታችን አለኝታችን ነው።
ሀገርን ለማጽናት እና ለማበልጸግ ከመንግሥት ጎን በጽናት መቆም፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በጀግኖች ልጆቿ ክንድ ሁልጊዜም ከፍ ብሎ ይህ ሕዝባዊ ደጋፍ እና አንድነት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ የማትሸነፍ እና የጀመረችውን የብኀ የሚያረጋግጥ ነው።
Former Ethiopian Armed Force-የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት