Dimaa Dachasa

Dimaa Dachasa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dimaa Dachasa, Grocers, Adaba, sole oromia, Addis Ababa.

19/08/2025
27/07/2025

"እኔ እኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ!" - የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ሀገር ባህል ልብስ ደመቁ

ለኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር በተለያዩ መንገዶች ከሚገልጹና ከሚያንፀባርቁ የአገራት መሪዎች አንዷ የሆኑት የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ጄሲካ ሮዝ ኤፔል አሊፖ (Jessica Rose Epel Alupo)፣ ለሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ለመካፈል ዛሬ አዲስ አበባ ሲገቡ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ክብርና ፍቅር በግልጽ አሳይተዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቷ በኢትዮጵያ ሸማ የተሰራና በአገራቸው የቀለም ፈርጥ (Color tone) የተጠለፈ ቀሚስ ለብሰው በመምጣት ትኩረትን ስበዋል። ወ/ሮ ጄሲካ ሮዝ ኤፔል አሊፖ ባለፈው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ለመሳተፍ ሲመጡም ለተቀበሏቸው ሚኒስትር "እኔ እኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ!" ማለታቸውን ኃይለሚካኤል ዴቢሳ ከዘገበው መረጃ መረዳት ይቻላል። እኚህ ምክትል ፕሬዝዳንት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር ደጋግመው ሲገልጹ መሰማታቸውም ታውቋል።

28/05/2025

የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም የሥልጣን ዘመናቸውን የመሠረተ ትምህርት ዘመቻን በተመለከተ ላበረከቱት አስተዋፅዖ በ'Ethiopian society partnership' ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል። ሽልማቱ በሐራሬ፣ ዚምባብዌ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተሰጥቷቸዋል።

የመሠረተ ትምህርት ዘመቻና የፕሬዝዳንቱ አስተዋፅዖ

ሽልማቱን ሲቀበሉ የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም ባደረጉት ንግግር፣ መሃይምነትን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የተደረገው ጥረት እሳቸው ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት በንጉሡ ዘመን "የፊደል ሠራዊት" በሚል ለጎልማሶች ትምህርት ይሰጥ እንደነበረ አስታውሰዋል። የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ ሲጀመር በመላው አገሪቱ በርካታ ሰዎች ተሰማርተው ባከናወኑት ሥራ አመርቂ ውጤት እንደተገኘበት ገልፀዋል።

ሽልማቱ የሁሉም ተሳትፎ ውጤት

ፕሬዝዳንት መንግሥቱ "ሽልማቱ የኔ ብቻ ሳይሆን በወቅቱ የነበሩ አብዮታውያን ጓዶች፣ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ በጎ ፈቃደኞችና መላው ኅብረተሰብ በንቃት የተሳተፈበት ስለሆነ የነሱም ነውና ክብርና ምስጋናውን እነሱም ይውሰዱ" ብለዋል። አክለውም "በዚያን ጊዜ ይህ መሃይምነትን ለማጥፋት የሠራውን መልካም ሥራ አስታውሰው ዕውቅና ለሰጡት ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ" ሲሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የቤተሰብ ምስክርነት ለትምህርት ፍቅር

በዚሁ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት ልጃቸው ዶክተር ትዕግሥት መንግሥቱ፣ "ለትምህርት ያለህ ጥማትና ፍላጎት ያኔ ገና በወጣትነትህ የተገለጠው የመጀመሪያ ልጅህን 'ትምህርት' ብለህ ስትሰይማት ነው። 'መማር መማር አሁንም መማር' የሚለው መፈክር የሁላችንም ትዝታ ነው። ትምህርት ለሁሉም እንዲዳረስ ያደረግከውን ጥረት በዚያ ተጠቃሚ የነበሩት ብቻ ሳይሆኑ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እኛም ቤተሰቦችህ እናደንቃለን" ብለዋል።
ይህ ዘገባ የገነት አየለ ነው።

Address

Adaba, Sole Oromia
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dimaa Dachasa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category