Dursa Biyyaaf

Dursa Biyyaaf Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dursa Biyyaaf, Grocers, Hawwii Guddinaa, Addis Ababa.

19/08/2025
19/08/2025

የደመወዝ ማሻሻያውን ተከትሎ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች…

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የደመወዝ ማሻሻያውን ምክንያት በማድረግ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል፡፡

የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወንድሙ ፍላቴ ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት፥ የደመወዝ ማሻሻያው መንግስት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የወሰደው ርምጃ ነው፡፡

የደመወዝ ማሻሻያ ውሳኔው ከንግድ ስርዓቱ ጋር ምንም የሚያገናኘው ጉዳይ እንደሌለ ገልጸው፥ ምርትና አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት ማሻሻያውን በማሳበብ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

መንግስት ዋጋ እስከሚጨምር በሚል ምርት በመደበቅ በገበያ ላይ እጥረት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ነጋዴዎች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፥

ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌላቸው ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ እንቅስቃሴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ምርት የሚደብቁና ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ አስፈላጊውን ርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል ህብረተሰቡ ለሚመለከታቸው ተቋማት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መንግስት ለሰራተኛው የደመወዝ ማሻሻያ ተጨማሪ 160 ቢሊየን ብር በጀት መመደቡን መግለጹ ይታወቃል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

19/08/2025
29/07/2025

ጉባኤው ኢትዮጵያ ልምድ ያካፈለችበትና የመፍትሔ አካል ሆና የቀረበችበት ነበር - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ያስተናገደችው 2ኛው የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ ልምዷን ያካፈለችበትና ለምግብ ሥርዐት መስተካከል መፍትሔዎችን ያቀረበችበት ነው አለ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፡፡

አገልግሎቱ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ከተባበሩት መንግሥታት ጋር በመቀናጀት ያዘጋጁት የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ በርካታ የሀገራት መሪዎች፣ የግብርናው ዘርፍ ተመራማሪዎችና ተቋማት እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በታደሙበት በአዲስ አበባ ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡

በጉባኤው ባለፉት ዓመታት በምግብ ስርዓት ለውጥ ረገድ የታዩ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ተገምግመው ቀጣይ አቅጣጫዎች ተመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጉባኤዉን ከማስተናገድ ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሄደችበትን ርቀት በመልካም ተሞክሮነት አካፍላለች፡፡

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በየዓመቱ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የምትተክለውን በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ችግኞችና ከምግብ ስርዓት መረጋገጥ ባሻገር ያስገኛቸው ውጤቶች በልምድነት ቀርበዋል፡፡

ጉባኤዉ የ2030 (እ.አ.አ) የዘላቂ ልማት ግብን ለማሳካት በምግብ ስርዓት ረገድ ስኬት ሊመዘገብ በሚችልበት አግባብ ላይ በስፋት የመከረ፣ በርካታ አማራጭ ተሞክሮዎችን የዳሰሰና ቀጣይ ትኩረቶችን ያመላከተ ሆኖ ተጠናቅቋል፡፡

በሌማት ትሩፋት፣ በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በከተማ ግብርና፣ በአረንጓዴ ዐሻራ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበችው ኢትዮጵያ ከጉባኤዉ ጎን ለጎን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶችን ለማጠናከር መድረኩን በእጅጉ ተጠቅማበታለች፡፡

በተጀመረዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በግብርናዉ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን አሳይታበታለች፡፡
ባለፈው በጀት ዓመት ከ150 በላይ አህጉራዊና ዓለማቀፍ ጉባኤዎችን ያስተናገደችዉ ኢትዮጵያ በጀመረችዉ ብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የዓለም የኮንፈረንስ ቱሪዝም የትኩረት ማዕከል ሆና ቀጥላለች፡፡

የከተሞችን ገጽታ በእጅጉ መለወጧና የአገልግሎት ዘርፉ እየጎለበተ መምጣት፣ የሕዝቧ እንግዳ ተቀባይነት ባህል የዳበረ መሆን፣ ተስማሚ የአየር ንብረት ያላት መዲና ባለቤት መሆን፣ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ዐቅም እየጎለበተ መምጣት መሰል ትልልቅ ጉባኤዎችን ለማስተናገድ ዕድሎችን እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

ለጉባኤዉ በስኬት መጠናቀቅ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፀጥታ ተቋማት፣ አገልግሎት ሰጪ የንግድ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም እንግዶች ለጉብኝትና ለልምድ ለውውጥ በተንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች በክብር ላስተናገዱ ኢትዮጵያውያን ሁሉ መንግሥት የላቀ ምስጋና ያቀርባል፡፡

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

29/07/2025
29/07/2025
29/07/2025

ኢትዮጵያ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ምገባ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት እየሰራች ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በኋላ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ምገባ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት እየሰራች ነው አሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፡፡

ሚኒስትሩ በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በትምህርት ቤት ምገባ ላይ የሚደረግን ኢንቨስትመንት አስመልክቶ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አቅርበዋል።

በትምህርት ቤት ምገባ አማካኝነት የተመጣጠነ ምግብ ለህጻናት ማቅረብ በተባበሩት መንግስታት የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦች ከተቀመጡ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው ብለዋል።

ከምግብ ሥርዓት ጋር በተገናኘ ሀገራት በትምህርት ቤት ምገባ እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራት ላይ ኢትዮጵያ ያሳየቻቸውን ለውጦችና ሂደቶችም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ በትምህርት ቤት ምገባ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ካደረጉ ሀገራት አንዷ መሆኗን ጠቅሰው፥ በዕቅዱ መሰረት በ2030 ሁሉንም የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በመመገብ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነች ነው ብለዋል።

መንግስት ዕቅዱን ለማሳካት የትምህርት ቤት ምገባን በበጀቱ ውስጥ በማካተት እየሰራ ሲሆን ክልሎችም አላማውን በመረዳት ትኩረት እንደሰጡት ተናግረዋል።

የትምህርት ቤት ምገባ ቀጣዩ ትውልድ የሚቀረጽበት እንዲሁም ከድህነት መውጣት የሚቻልበት መርሐ ግብር እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

24/06/2025

Pireezidaanti Taayyee Atsiqasillaaseen Afrikaatti gorsaa Olaanaa Pireezidaanti Tiraampi wajjin mari’atan

Finfinnee, Waxabajjii 17, 2017 (FMC) - Pireezidaantiin FDRI Taayyee Atsiqasillaaseen Afrikaatti gorsaa Olaanaa Pireezidaanti Tiraampi Maasaad Boloos waliin mari’ataniiru.

Maree kana yaa’ii daladalaa Afrikaa fi Ameerikaa Angoolaatti taa’amaa jiru cinaatti kan mari’atan.

Hariiroo seena qabeessa biyyoota lameenii barootaaf ture jabeessuun haala danda’amu irratti kan mari’atan.

Misoomaa fi nageenya naannawaa irrattis mari’achuu isaanii Ministeera Dhimma Alaatti Daayrekterri Jeneraalaa Dhimmoota Ameerikaa fi Awurooppaa Ambaasaaddar Mulee Taarraqeenyi ibsaniiru.

Keessumaa damee dippilomaasii, investimentii fi daldalaan tumsa biyyoonni lamaan qaban haala ittin caalmaatti cimsuu fi bal’isuun danda’amu irratti waliigaluu isaanii TOI gabaaseera.



Odeeffannoowwan waqtaawaa dabalataa argachuuf;

Teelegiraama t.me afanoromofana

Yuutiyuubii Afaan Oromo: www.youtube.com/

Marsariitii www.fanamc.com/afaanoromoo

Tiwiitara https://twitter.com/fanatelevision

Feesbuukii: FBC Afaan Oromoo

Tiktok https://www.tiktok.com/

Yeroo maraa nu waliin waan taataniif isin galateeffanna

23/06/2025
23/06/2025

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስችላል- ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከሰሞኑ በተለያዩ መገናኛ ብዘሃን የሚሰራጩ መረጃዎች ተገቢነት የላቸውም አለ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያቀረበው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት መቅረቡ እና ምክር ቤቱ ለሰው ሃይል፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ይታወሳል።

ረቂቅ አዋጁ በውጭ ሀገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንን መብት፣ ደህንነት እና ዘላቂ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሕጋዊ የሥራ ስምሪቱን ለማበረታታትና የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንዲሁም ሀገር ከዘርፉ የምታገኘውን ጥቅም ለማሳደግ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱን ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

የረቂቅ አዋጁ ግብና ዓላማም የዜጎችን መብት፣ ደህንነት፣ ክብርና እና ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤ በዘርፉ የሚስተዋሉ ሕገወጥነቶችን መግታት እና ሀገራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ መሆኑን ነው የተገለጸው፡፡፡

ደረጃ ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሲሆን÷ ኤጀንሲዎች በሚያሰማሩት የሰው ኃይል ብዛት፣ ክህሎት፣ የሙያ ዘርፍ፣ መነሻ ካፒታል እንዲሁም ተያያዥ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ደረጃ የሚሰጥ ነው።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ኤጀንሲዎች በባንክ ዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ የሚገደዱት ዝቅተኛ ገንዝብ ከ100 ሺህ ወደ 50 ሺህ ዶላር ዝቅ እንዲል አድርጓል።

እንዲሁም ጥብቅ የፋይናንስ ቁጥጥሮች ኤጀንሲዎች ለዋስትና የሚያስይዙት ገንዘብ በካሽ በባንክ እንዲቀመጥ የሚያስገድድ ሲሆን÷ ይህ ገንዘብ የዜጎችን ደህንነት ለማስከበር የሚውል እንደሆነ እና ኤጀንሲዎች ለላኳቸው ዜጎች ተገቢውን ሃላፊነት እንዲወስዱ የሚያደርግ ነው።

ረቂቅ አዋጁ በዘርፉ የሚደረገው የሥራ ስምሪት፣ የስልጠና ምደባ፣ የብቃት ምዘናን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች ግልጽና ከሰው ንክኪ ነጻ በሆነ የአሰራር ሥርዓት እንዲኖራቸው ያደርጋል።

በአጠቃላይ በዜጎች መብት፣ ክብርና ደህንነት ላይ በመደራደር ሃብት ያጋብስ የነበረውን ሃይል የሚገታ ብቻ ሳሆን በየደረጃው የዜጎችን እና የሀገርን ጥቅም ሲጎዱ የነበሩ ሕገወጥ የጥቅም ማጋበሻ ሰንሰለቶችን በመበጣጠስ ሕጋዊ አሰራርን የሚያሰፍን መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ሰሞኑን ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ በተለያዩ የመገናኛ ብዘሃን አውታሮች የተሰራጩ መረጃዎች ተገቢነት የሌላቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Address

Hawwii Guddinaa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dursa Biyyaaf posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category