health tips and news

health tips and news የጤና መረጃ እና ወቅታዊ ጉዳይ

የእነ አባ ሳዊሮስ እግድ ተነሳ።የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶ...
24/02/2023

የእነ አባ ሳዊሮስ እግድ ተነሳ።

የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ እግድ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በቅርቡ የተፈጸመውን ዕርቅ ተከትሎ ፦

- የአባ ሳዊሮስ፣
- የአባ ኤዎስጣቴዎስ
- የአባ ዜና ማርቆስ የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቀሪዎቹ 26 ግለሰቦች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳይገቡ የተጣለው ዕግድ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ተገልጿል።

 #ቦረናበ  #ቦረና በታሪክ እጅግ አስከፊ በተባለው ድርቅ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት የምትፈልጉ በ "   " በኩል መርዳት ትችላላሁ።የዚህ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) የባን...
24/02/2023

#ቦረና

በ #ቦረና በታሪክ እጅግ አስከፊ በተባለው ድርቅ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት የምትፈልጉ በ " " በኩል መርዳት ትችላላሁ።

የዚህ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) የባንክ አካውንቶች ፦

👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000522499823 (Swift Code: CBETETAA)

👉 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ - 1011800084313 (Swift code: CBO RETAA)

👉 አዋሽ ባንክ - 013081084782900
(Swift code: AWINETAA)

👉 ኦሮሚያ ባንክ - 1548414100001
(Swift code: ORIRETAA)

ቁጥሮች ስለ ቦረና ምን ይናግሩናል ?

- በቦረና ዞን 807 ሺህ ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። ከነዚህ ውስጥ 167 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች አስቸኳይና ተከታታይ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው።

- በዞኑ ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል።

- በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85 % የቀንድ ከብቶች ናቸው።

- በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ሲሆን በዞኑ ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ ነው።

- የተከሰተው ድርቅ በዞኑ 13 ወረዳዎች አጥቅቷል ፤ በዞኑ ከሚገኘው 60 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ ድጋፍ ይፈልጋል።

ታዋቂው የፊልም ተዋናይ ብሩስ ዊልስ ዲሜንሺያ የተባለ የጤና ችግር እንደገጠመው ቤተሰቦቹ ይፋ አደረጉ።ቤተሰቦቹ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መግለጫ “በመጨረሻም ግልጽ የሆነ ምርመራ መኖሩ ...
17/02/2023

ታዋቂው የፊልም ተዋናይ ብሩስ ዊልስ ዲሜንሺያ የተባለ የጤና ችግር እንደገጠመው ቤተሰቦቹ ይፋ አደረጉ።

ቤተሰቦቹ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መግለጫ “በመጨረሻም ግልጽ የሆነ ምርመራ መኖሩ እፎይታ ሰጥቶናል” ብለዋል።

ብሩስ ዊልስ ያጋጠመው ይህ ዲሜንሺያ የተባለው የጤና ችግር አይነት እንቅስቃሴን እና ሌሎች ተፈጥሯዊ ሂደቶችን መቆጣጠርን አዳጋች የሚያደርግ ነው።

የ67 ዓመቱ ተዋናይ ባለፈው ዓመት አፋሲያ (aphasia) በተባለ ለንግግር እክል የሚያጋልጥ ህመም መያዙ ይፋ ተደርጎ ነበር።

ቤተሰቡ በመግለጫቸው ላይ አድናቂዎቹ ያልተገደበ ፍቅራቸውን ስለገለጹ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።

አክለውም ፍሮንቶቴምፖራል ዲሜንሺያ (frontotemporal dementia) የተባለው እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ የሚከሰት ህመም መሆኑን ገልጸዋል።

“ዛሬ ለዚህ በሽታ ምንም ዓይነት ሕክምና የለም። ወደ ፊት ይህ እውነታ ይቀየራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብሏል የቤተሰቡ መግለጫ።

ብሩስ ዊልስ ስሙ የገነነው እኤአ በ1980ዎቹ እና 90ዎቹ በዳይ ሀርድ፣ ዘ ሲክስ ሴንስስ፣ አርማጌዶን እና ፐልፕ ፊክሽን ፊልሞች ላይ ከተወነ በኋላ ነው።

ብሩስ ዊልስ ለአምስት ጎልደን ግሎብ ሽልማቶች ላይ ታጭቶ በአንዱ ማሸነፍ ችሏል።

በተጨማሪም ሦስት ለኤሚ ሽልማትም ታጭቶ ሁለቱን ማሸነፍ ችሏል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለጨፌው ሪፖርት እያቀረቡ ነው ************************* የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ...
17/02/2023

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለጨፌው ሪፖርት እያቀረቡ ነው
*************************

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለጨፌው ሪፖርት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

በሪፖርታቸውም በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ እንደ ሸኔ ያሉ ኃይሎችን በንግግር ወደ እርቅ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ብሔር እና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ወንድማማችነትን ለማደፍረስ በግል እና በተደራጀ መልኩ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ኃይሎችን ማሳፈር የሚያስችል ሥራ መከናወኑንም ገልጸዋል።

ይልቁኑም ወንድማማችነትን ለማጠናከር በአጎራባች ክልሎች 5 የቡኡራ ቦሩ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።

በግብርናው ዘርፍም ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ሥራ ተከናውኗል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በዚህም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አንሥተዋል።

በክልሉ በመኸር እና በመስኖ በክላስተር ከለማው ስንዴ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደተቻለም ጠቁመዋል።

በ2014/15 የምርት ዘመንም የምርት ማሳደጊያ ግብአቶች እና ምርጥ ዘሮች ለአርሶ አደሩ ቀርቧል።

አርሶ አደሮች ተፈጥሮአዊ ማዳበሪያን በማዘጋጀት እንዲጠቀሙ ተደርጓል።

በክልሉ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በተከናወነው የስንዴ ምርት በንቃት በመሳተፍ ውጤታማ መሆን ተችሏል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

ለዚህም ሥራ ስኬት የበኩላቸውን ላበረከቱ የዘርፉ ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ታዋቂው የፀጉር መንከባከቢያ ምርት የሆነው የኦላፕሌክስ ምርቶች ፀጉራችንን በመነቃቀል፣ ቁስለት እና ሌሎችንም ችግሮች አስከትሎብናል ያሉ 28 ሴቶች በአሜሪካ ክስ መሰረቱ።ይህ ኦላፕሌክስ የተባ...
17/02/2023

ታዋቂው የፀጉር መንከባከቢያ ምርት የሆነው የኦላፕሌክስ ምርቶች ፀጉራችንን በመነቃቀል፣ ቁስለት እና ሌሎችንም ችግሮች አስከትሎብናል ያሉ 28 ሴቶች በአሜሪካ ክስ መሰረቱ።

ይህ ኦላፕሌክስ የተባለው የፀጉር መንከባከቢያ አምራች የተጎዳ ፀጉርን “የሚጠግኑን እና መልሶ እንዲያገግም የሚያደርጉ ናቸው” የሚላቸውን የፀጉር መንከባከቢያ እና መታጠቢያዎችን ያመርታል።

ነገር ግን የቀረበበት ክስ እንደሚለው የኦላፕሌክስ ምርቶች ጎጂ ኬሚካሎችን የሚጠቀም በመሆኑ የሴቶችን የጭንቅላት ቆዳ እና ፀጉርን አደገኛ ሁኔታ ላይ ጥሏል ተብሏል።

በኦላፕሌክስ ላይ ክስ የመሠረቱት ሴቶች ለደረሰባቸው ጉዳት በጋራ የ75,000 ሺህ ዶላር ካሳ ጠይቀዋል።

የመንግስት ሚዲያዎች የቤተክርስቲያኒቱን ጉዳይ ሳይዘግቡ መቅረታቸውን በተመለከተ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማሕበር መግለጫ አወጣ።በመግለጫው "በፌዴራል መንግስትና በክልል መንግስታት...
16/02/2023

የመንግስት ሚዲያዎች የቤተክርስቲያኒቱን ጉዳይ ሳይዘግቡ መቅረታቸውን በተመለከተ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማሕበር መግለጫ አወጣ።

በመግለጫው "በፌዴራል መንግስትና በክልል መንግስታት ቁጥጥር ስር ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ህዝብ አንድ ጉዳይ የሆነውን አጄንዳ አለመዘገባቸውን ማህበራችን ታዝቧል" ብሏል።

ማህበሩ "የመገናኛ ብዙኃኑ ላይ የተስተዋለው ችግር በወቅታዊ ጉዳይ ዘገባን አለመስራታቸው ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያኗ ላይ ስለተፈጠረው ምንም አይነት ዘገባ ሳይሰሩ መንግስት ከእምነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የሚሰጣቸውን መግለጫዎች ማስተላለፋቸውም ጭምር ነው፡፡ የተከሰተውን ችግር ሳይዘግቡ መንግስት የሚሰጠውን መግለጫ እና አቋም ብቻ ተከትለው መዝገብ ከሙያዊ ሥነ ምግባር እና አሰራር ማፈንገጥ መሆኑን ማሕበራችን ይረዳል። ይህ ተግባርና ልማድ በአስቸኳይ እርምት ሊወሰድበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ማህበሩ ያምናል።" ብሏል በመግለጫው።

ማህበሩ "...የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ጋዜጠኛ የሆነው ዮሴፍ ከተማ መታሰሩን ማህበራችን አረጋግጧል። ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት መታሰራቸው እጅግ አሳሳቢና ሀገርን ወደኋላ የሚጎትት እንደሆነ መረዳት አያዳግትም።" ብሏል

የማህበራችን አባል የሆነው ጋዜጠኛ የሴፍ ስራን በአግባቡ የሚሰራ፤ ከጠንካራ ዜጠኞች መካከል አንዱ ነው። የመንግስት የጸጥታ አካላት ግን በስራ ላይ የነበረውን አባል ማሰራቸው እጅግ አሳዛኝ ነው ብሏል።

በመሆኑም የማህበሩ አባል ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከተማ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ እንጠይቃለን ሲል ማህበሩ አስታውቋል።

https://t.me/tenayeinfo

በአማራ ክልል ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ዳግም ስራ ጀመሩ ተባለየትምህርት ሚኒስቴር  ዛሬ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል በጦርነቱ ሳቢያ ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 347 ትምህርት ቤቶች ዳግ...
16/02/2023

በአማራ ክልል ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ዳግም ስራ ጀመሩ ተባለ

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል በጦርነቱ ሳቢያ ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 347 ትምህርት ቤቶች ዳግም ስራ ጀምረዋል።
ዳግም ትምህርት ከጀመሩት ትምህር ቤቶች ውስጥ 329ኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ 18ቱ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ሕዝቅኤል ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ገልፀዋል።

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በ30 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ፍ/ቤቱ ወሰነየኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራቹ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በ30 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ...
16/02/2023

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በ30 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ፍ/ቤቱ ወሰነ

የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራቹ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በ30 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ፍ/ቤቱ ዛሬ መወሰኑን ጠበቃው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ችግር ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ፤ ፖሊስ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የግዜ ቀጠሮ ችሎት ያቀረበው ሲሆን ፣ በተለያዩ ወንጀሎች እንደጠረጠረውም ለችሎቱ መግለፁን የተጠርጣሪው ጠበቃ አክለው ገልፀዋል።
ፓሊስ ተጠርጣሪውን ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እንዲሁም ከአልሸባብና ከኦነግ ሸኔ ጋር በመገናኘት ጠርጥሬዋለው በሚል ምርመራውን ለማጠናከር ተጨማሪ የ 14 ቀን ግዜ መጠየቁን ጠበቃው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል ።
የተጠርጣሪው ጠበቃ ደንበኛቸው ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የቀረበበት የግዜ ቀጠሮ መጠየቂያ፤ ወንጀል ስለፈፀሙ የሚያስረዳ አይደለም ብለዋል። ጠበቃው አያይዘውም ደንበኛችን ጋዜጠኛ እንደመሆኑ ሀሳቡን በነፃነት ገለፀ እንጅ ወንጀል ስለመፈፀሙ ፖሊስ ምንም አይነት ማሳያ አላቀረበም በማለትም ፤የደንበኛችን ዋስትና ይፈቀድልን ሲሉ መጠየቃቸውን ጠበቃ ሰለሞን ተናግረዋል ።
የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ችሎት ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ በ30 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲወጣ ሲል ብይን ሰጥቷል ።ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው የካቲት 7 ቀን 2015 ዓም ከመኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ሀይሎች መታሰሩ ይታወሳል።

በባሕር ሲጓዙ የነበሩ ከ380 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከመስመጥ አደጋ መታደግ ተቻለየጂቡቲ ባለሥልጣናት በሕገወጥ መንገድ በባሕር ላይ ለመሻገር ሲሞክሩ የመስመጥ አደጋ ተጋርጦባቸው የነ...
16/02/2023

በባሕር ሲጓዙ የነበሩ ከ380 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከመስመጥ አደጋ መታደግ ተቻለ
የጂቡቲ ባለሥልጣናት በሕገወጥ መንገድ በባሕር ላይ ለመሻገር ሲሞክሩ የመስመጥ አደጋ ተጋርጦባቸው የነበሩ 383 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከአደጋ መታደጋቸው ተገለጸ።

ባለሥልጣናቱ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያኑን የታደጉት የኤደን ባሕረ ሰላጤ ተብሎ በሚጠራው የባሕር ክፍል ላይ መሆኑን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታውቋል።

ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በጅቡቲ፣ በየመን እና ሶማሊያ በሚዋሰነው የውሃ አካል ላይ ከመስመጥ የዳኑት ባለፈው ሳምንት ውስጥ መሆኑም ተነግሯል።

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአገሪቱ የባሕር ዳርቻ ጥበቃ ኃይል ዜጎቹን ለመታደግ ለሚያደርገው ጥረት ምስጋና አቅቦ፣ 383 ስደተኞቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ አዘዋዋሪዎች ሕግ ፊት ቀርበዋል ብሏል።

አይኦኤም የስደተኞች ፍልሰት የዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመቀስቀሱ በፊት ወደነበረበት ተመልሷል ያለ ሲሆን፤ ለስደተኞች ፍልሰት ዋነኛ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል ድህነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ግጭት ናቸው ብሏል

Address

22
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when health tips and news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category