Eyuel

Eyuel Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Eyuel, 0925922780, Addis Ababa.

05/09/2025
20/05/2025

የባህር በር ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ሕዝቡ ተገቢውን ድጋፍና ርብርብ ማድረግ አለበት - ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የታየውን ህዝባዊ ቁርጠኝነት በባህር በር ተጠቃሚነት ጥያቄ ላይ መድገም እንደሚገባ ምሁራን ተናግረዋል።

ምሁራኑ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የባህር በር ተጠቃሚነት ጊዜው የሚጠይቀው የህልውናና የብሄራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፖለቲካ ተንታኙ ሴኔሳ ደምሴ፥ ህዝቡ የኑሮ ሁኔታው ሳይበግረው የግድቡን ግንባታ ከጫፍ ማድረስ እንደቻለው ሁሉ የባህር በር ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ ድጋፍና ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ባለሙያው ጥላሁን ሊበን በበኩላቸው፥ አንድነትን በማጠናከር በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ጥያቄው የሚመለስበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የባህር በር ተጠቃሚነት ጥያቄ ብቻውን ግብ ሊሆን እንደማይችል የገለጹት ምሁራኑ፥ ዋና ግቡ የባህር በር ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በመቅደስ ከበደ

በዛሬው ዕለት ከካምባ ዙሪያ ወረዳ፣ ጋርዳ ማርታ ወረዳ እና ከካምባ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ምሁራን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር የምክክር ጉባዔ አካሂደናል። ከለውጡ ማግስት ወዲህ የመጣንባቸ...
15/05/2025

በዛሬው ዕለት ከካምባ ዙሪያ ወረዳ፣ ጋርዳ ማርታ ወረዳ እና ከካምባ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ምሁራን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር የምክክር ጉባዔ አካሂደናል።
ከለውጡ ማግስት ወዲህ የመጣንባቸው በጎ እርምጃዎች እውቅና ያገኙበት እና የህዝባችን የመልማት ፍላጎት በሰፊው የተንፀባረቀበት መድረክ ነው።

በስብሰባው ከታዳሚያኑ እጅግ ጠቃሚ ሀሳቦች ተንሸራሽረዋል። በይበልጥ ወደህዝባችን ሰርፀን ለመግባት ግብዓት የሚሆኑ ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋርም እየተመካከርን ለመስራት ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ አጀንዳዎች ተነስተዋል።

በተለይም በአሁኑ ሰዓት እየተናበብን የምንሄድበትን መንገድ መያዝ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይህም በጉባዔው ታዳሚ በኩል በሙሉ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን ፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን በቅርብ ዓመታት ውስጥ ውጤት እንደምናመጣ እርግጠኞች ነን።

በጋሞ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ሀኪመ አየለ የተመራ ልዑካን ቡድን ካምባ ከተማ ገባካምባ፦ ግንቦት 7/2017 ዓ.ም (ካምባ ከተማ አስ/ር መ/ኮሙኒኬሽን)፦ ከኃላፊው በተጨማሪ...
15/05/2025

በጋሞ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ሀኪመ አየለ የተመራ ልዑካን ቡድን ካምባ ከተማ ገባ

ካምባ፦ ግንቦት 7/2017 ዓ.ም (ካምባ ከተማ አስ/ር መ/ኮሙኒኬሽን)፦ ከኃላፊው በተጨማሪ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የመንግስት ሀብት አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኢንቁ ዮሐንስ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንተርፕራይዝና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ም/ማኔፋክቸርንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አይሶጼ ህሎታ እና የአርባምንጭ ከተማ አስ/ር በልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ልሳኔወርቅ ካሳዬ ይገኛሉ።

ልዑካን ቡድኑ ወደ ካምባ ከተማ ሲደርሱ የካምባ ከተማ አስ/ር ከንቲባ አቶ መስፍን ማኑቃ፣ የካምባ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ጎንችሬ፣ የጋርዳ ማርታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ዳንኤል፣ ሌሎችም የፓርቲ ኃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

06/05/2025
የህዳሴው ግድብ ዋንጫ አቀባበል   #በከምባ-----------------------------------------------------------ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ  በገረሴ ከተማ አ...
02/05/2025

የህዳሴው ግድብ ዋንጫ አቀባበል #በከምባ
-----------------------------------------------------------

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በገረሴ ከተማ አስተዳደር እና በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ቆይታውን በማጠናቀቅ በዛሬው እለት ሽኝት ተደርጎለት የካምባ ከተማ አስተዳደር እና የካምባ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል አድርገዋል ።

(ካምባ: 24/8/2017 ዓ.ም) በኢትዮጵያዊያን የተጀመረውና በኢትዮጰያዊያን ብቻ ለሚጠናቀቀው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ የሚመጥን አቀባበልና የማጠቃለያ የሀብት አሰባሰብ ሥራ በመስራት ላይ የሚገኘው የየካምባ ከተማ አስተዳደር እና የዙሪያ ወረዳ አስተዳደር በቅንጅት ለህዳሴው ግድብ ዋንጫ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅታቸውን አጠናቀው መንገድ ወተው ተቀብለዋል።

"በህብረት ችለና" በሚል መሪ ቃል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ለመቀበል የካምባ ዙሪያ ወረዳና ከተማ አስተዳደር በቅንጅት በጋራ ዝግጅት ጨርሰው ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

የጋሞ ዞን ካምባ ዙሪያ ወረዳ እና ከተማ አስተዳዳር በቅንጅት የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫን ለመቀበል ቀደም ተብለው በጋራ ምዕራፍን ጨረሰው በዛረው ዕለት ዋንጫውን በነቅስ ወተው ተቀብለዋል።

14/04/2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 98.66 ከመቶ አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን ስድስት ዩኒቶቹም ወደ ስራ ገብተዋል − የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
**********************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የአፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረዋል።

ግምገማው ታላላቅ የመሠረተ ልማት እና ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶችንም አፈፃፀም ተመልክቷል፤ ለአብነትም ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 98.66 ከመቶ አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን ስድስት ዩኒቶቹም ወደ ስራ መግባታቸው ተመላክቷል።

መርሐ ግብሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም አቅርቦትን በመመልከት የጀመረ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያ በሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ተፅዕኖ አጠቃላይ ምልከታ እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ርምጃ ወቅታዊ መረጃ እንደቀረበበት ተገልጿል።

የዓለም ኢኮኖሚ በ2025 በ3.3 በመቶ የሚያድግ መሆኑ የተተነበየ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ከሰሃራ በታች ያለውን የአፍሪካ ክፍል ጨምሮ አብዛኛው የዓለም ክፍል አዎንታዊ እድገት እንደሚያስመዘግብም ተነስቷል። የኢትዮጵያም ኢኮኖሚ 8.4 በመቶ እንደሚያድግ ተተንብይዋል።

ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም መርሐ ግብር የተረጋጋ ሆኖ የቁጠባ እና የኢንቬስትመንት እድገትም አሳይቷል ተብሏል።

የውጭ ዕዳ ከሀገራዊ የምርት መጠን (ጂዲፒ) ያለው ምጣኔ 13.7 ከመቶ በመድረስ ትርጉም ባለው መጠን የቀነሰ ሲሆን፤ በተጨማሪም አዲስ የውጭ ምንዛሬ አሰራር መዘርጋቱ ከውጭ የሚላክ የውጭ ምንዛሪ እንዲጨምር በማድረግ የሀገራችንን የውጪ ምንዛሬ ክምችት መጨመሩ ተገልጿል።

ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም ከግብርና፣ ከማዕድን፣ ከኢንደስትሪ እና ኤሌክትሪክ የተገኙ የውጭ ንግድ ገቢዎችም እድገት አሳይተዋል የተባለ ሲሆን ቡና፣ ወርቅ፣ ጥራጥሬ፣ የዘይት ምንጭ ፍሬዎች፣ አበባ እና ኤሌክትሪክ አምስቱ ቀዳሚ የውጭ ንግድ ምርቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ግምገማው ታላላቅ የመሠረተ ልማት እና ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶችንም አፈፃፀም ተመልክቷል፤ ለአብነትም ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 98.66 ከመቶ አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን ስድስት ዩኒቶቹም ወደ ስራ መግባታቸው ተመላክቷል።

የዛሬ ጠዋቱ ግምገማ የዘላቂ የልማት ጥረቶች በተለይም አካታችነትን እንደ ቁልፍ የስኬት መለኪያ በመውስድ ተጠናቅቋል። ለዘላቂ ልማት ሥራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ የሥራ ተግባራትም እንደቀረቡበት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

14/04/2025

Address

0925922780
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eyuel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share