Great silte

Great silte Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Great silte, Grocers, Addis Ababa.

ኢማማችን በዱዐ እናስታውሳቸዉ-------------------------------------------------------የሸይኽ ሆጀሌ መስጂድ ኢማም ታላቁ አሊም ሸይኽ አብዱሰላም  አቢ በጠና ታመ...
04/01/2024

ኢማማችን በዱዐ እናስታውሳቸዉ
-------------------------------------------------------
የሸይኽ ሆጀሌ መስጂድ ኢማም ታላቁ አሊም ሸይኽ አብዱሰላም አቢ በጠና ታመው ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ይገኛሉ::

ሁላችንም አላህ አፊያቸውን እንዲመልስላቸው በዱዓ እናስታውሳቸው::
አላህ እድሜያቸውን ያርዝምልን!
አሚን🤲🏻🤲🏻🤲🏻

26/12/2023

ለሶስት ተከታታይ ቀናት ለገጠር ቀበሌና ለከተማ አባላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በስኬት መጠናቀቁን የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሳኒ ጀማል ገለፁ።

ታህሳስ 15/2016 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

በሁልባራግ ወረዳ ''ከእዳ ወደ ምንዳ'' በሚል መሪ ቃል ለተካታታይ ሶስት ቀናት ለቀበሌ አመራርና አባላት ለከተማ አባላት እንዲሁም ለኢንተርፕራዝ ግንባር ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በስኬት መጠናቀቁን የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳኒ ጀማል ገልፀዋል።

አቶ ሳኒ አክለውም የፓርቲ አባላትን አቅም በተለያዩ ስልጠናዎች ማሳደግ ለሀገራዊ የብልፅግና ጉዟችን መተኪያ የሌለው እንደሆነ አንስተው ስልጠናው በሀገራችን ለመላው አባላት መሰጠቱን በመግለፅ በወረዳችንም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል።
በተጨማሪም አባላቱ ሀብትና ብልፅግና መፍጠርና ማስተዳደር፣ ሀገራዊ ገዢ ትርክትን መፍጠር እና የሰላም ባህል ግንባታ በሚሉ ርዕሶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ማድረግ ተችሏል ብለዋል አቶ ሳኒ ጀማል።

ከስልጠናው ጎን ለጎን የተለያዩ በጎ ስራዎች መሰራታቸውን ያነሱት ሀላፊው ከአባላት በብር 120,146 ብር በአይነት 6ኩንታል በቆሎ፣ 01ኩንታል ጤፍ፣ 64 ቅጠል ቆርቆሮ፣ 9ፓኬት ሚስማርና ከ100 በላይ ቤት መስሪያ እንጨት መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል። በተጨማሪም ስልጠናው በፈጠረው ተነሳሽነት የሌማት ትሩፋትን ከመስራት አንፃር አባላቱ የዶሮ 538,725 ብር እና የ05 የተሻሻለ ጊደር ብር መሰብሰቡን ገልፀዋል።

በቀጣይም ለፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር ከታህሳስ 15—20/2016 ድረስ ስልጠናው የሚሰጥ መሆኑንም አቶ ሳኒ ጀማል ገልፃዋል።

26/12/2023

ዜና ሹመት ❗️

የተከበሩ ዶ/ ር ከይረዲን ተዘራ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ ተደርገው በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚንስትሩ ተሹመዋል!!

መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ!!

17/12/2023
17/12/2023
▣ለስልጤ በደልም፣ ትግልም አዲሱ አይደለም! ••••••••••••••••••••••••••••••Mujib Amino📌ከጥንት እስከ ዛሬ ከየትኛው እንጀምር? የቱን አንስተን የቱን እንተው? እስቲ ከ...
02/09/2023

▣ለስልጤ በደልም፣ ትግልም አዲሱ አይደለም!
••••••••••••••••••••••••••••••
Mujib Amino

📌ከጥንት እስከ ዛሬ ከየትኛው እንጀምር? የቱን አንስተን የቱን እንተው? እስቲ ከባህሩ ጥቂት ብቻ እንጨልፍና እንለፍ።

📌ከ8ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 14ኛው ክፍለ ዘመን!! የስልጤ ህዝብ የሀርላ ህዝብ፣ ከሀረር ፣ ከአሪጎባ፣ ከወለኔ፣ ከቀቤና፣ ከአላባ ህዝብ ጋር የሚጋራው ታሪክ አለው። እስከ ዛይላ እስላማዊ ሱልጣኔቶች ኮንፌዴሬሽን ድረስ በገናናውው ታሪክ ስልጤ ንቁ ተዋናይ ከነበሩ ህዝቦች ጋር የወል ታሪክ አለው።

📌ከ14ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን!! በ1270 ዓ.ል. የዛጉዌ ሥርወ-መንግሥት ወድቆ የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት ከተተካበት ጊዜ አንስቶ እስከ ኢማሙ አህመድ ኢብን ኢብራሂም እስከሚነሱበት ጊዜ ድረስ የሀላባ፣ የወለኔ፣ የስልጤና የቀቤና ህዝቦች በሰሜናዊው ክርስቲያናዊ መንግሥት ተደጋጋሚ ጥቃት የደረሰባቸውና በእምነታቸው የተነሳ ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ ህዝቦች ናቸው። ከምሥራቅ ኢትዮጵያ እንዳይገናኙ በመቁረጥ ከልክ በላይ እንዲሰቃዩ፣ እምነታቸውን በግድ እንዲለውጡ፣ ለመዕከላዊው ክርስቲያናዊ መንግሥት የተለያዩ ግብሮችን ከመገበር አልፈው ቆንጆ ልጃገረድ እንዲገብሩ ተደርገው ቆይተዋል። እናም ለ300 ዓመታት ያህል የድቅድቅ ጨለማና የሰቆቃ ጊዜ አሳልፈዋል።

📌ከ16ኛውን ክፍለ ዘመን እስከ 1881 ዓ.ል!! በ16ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ መንፈቅ የኢማሙ አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚን የነጻነት ትግል ከመሩና ካፋፋሙ ህዝቦች ስልጤ ነው። ለ300 ዓመታት ጨቋኙ አገዛዝ ያቆራረጣቸው ቤተሰቦች ተገናኝተው በህዳሴ የቀድሞውን የሚመስል አዲስ መንግሥት መሰርተዋል። ነገር ግን ኢማሙ አህመድ በፖርቹጋል ወታደሮች በመገደላየው የሰሜናዊው ክርስቲያን መንግሥት እንደገና በማንሰራራቱ የስልጤ የበደል ምዕራፍ እንደገና ጀመሯል። የሆነው ሆኖ ከሀዲ ገራድ ሀጂ አሊዬ ሀጂ ዑመር፣ ከሸነስረላ፣ ከኢማም ሲዴ፣ ከሸበርከሌ፣ ከከቢር ሃሚድ፣ ከሸ አሊኑር...ዘመን ጀምሮ እስከ ሙለ ገራድ ጤም ለዝቦ እስከ ኢማም ጉንፈሞ ድረስ የስልጤ ህዝብ በገራዳዊ ሥርዓተ-መንግሥት ራሱን በራሱ እያስተዳደረና ወራሪን በመታገል ነፃነቱን አስጠብቆ ቆይቷል።

📌ከ1881 እስከ 1983 ዓ.ል!!
አፄ ምኒሊክ በደቡብና በኦሮሚያ እንዳደረጉት ሁሉ በጠመንጃ የስልጤን መሪ በመግደል ግዛቱን በመዕከላዊው መንግሥት ስር እንዲተዳደር አድርገውታል። ህዝቡም ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱን ተነጥቋል። ይህ ሁኔታ በአፄ የኃይለስላሴም እና በደርጉም ዘመነ-መንግሥት ሳይሻሻል ቀጥሏል። ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት ከማጣቱም በተጨማሪ አንድነቱን በመሸራረፍና ግዛቱን በመቆራረስ በባህልም ሆነ በቋንቋ ከማይመሳሰሉት ከጎረቤት ህዝቦች ጋር ወስዶ በመለጠፍ እምነቱ እንዲዳከም፣ አንድነቱና ትብብሩ እንዲላላ፣ ባህልና ቋንቋው እንዲደበዝዝ፣ አከባቢውን በእኔነትና በተቆርቋሪነት ተነስቶ እንዳያለማ ተጨቁኖና ማንነቱ እንዲከስም ሲደረግ ቆይቷል።

📌ከ1983-1993 ዓ.ል.
ደርግ ግንቦት 20/1983 ዓ.ል ሲወድቅ
የስልጤ ህዝብ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲታገልለት የቆየው ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱን መልሶ የሚቀዳጅበት ወቅት መጣ። የሽግግር መንግሥት ሊቋቋም የትጥቅ ታጋዮች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች፣ የነፃነት ተጋዮች...ወዘተ እንዲቀርቡ ጥሪ ተደረገ።

እነአክመል ሸይኽ ሳሎና ጓዶቹ ፤ አርቀው የተመለከቱ ወጣቶች የተተኪውን መንግሥት አቅጣጫ ቀድመው ያውቁ ስለነበር 'ጎጎት' የሚባል ድርጅት በማቋቋምና ፕሮግራም በመንደፍ ላይ ነበሩ። ነገር ግን እዚህ

ግልጽና አጭር መልዕክት ለፌደራሉ መጅሊስ አዲስ አበባ          ለሴት ተማሪዎች ኒቃብ ለብሶ ትምህርት መማር ክልክል ነው የሚል ግልጽ ሃገር አቀፍ አዋጅ በሌለበትና በሌሎች አካባቢዎች ላይ...
02/09/2023

ግልጽና አጭር መልዕክት ለፌደራሉ መጅሊስ አዲስ አበባ


ለሴት ተማሪዎች ኒቃብ ለብሶ ትምህርት መማር ክልክል ነው የሚል ግልጽ ሃገር አቀፍ አዋጅ በሌለበትና በሌሎች አካባቢዎች ላይ ኒቃብ አድርገው እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች ባለበት ተጨባጭ ላይ…የጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ሙስሊም ጠሎች ግን የግል ጥላቻቸውን ተቋማዊ በማድረግ የበርካታ ሙስሊም የእህቶቻችንን ህገ መንግስታዊና ሰብዓዊ መብት በማን አለብኝነት ስሜት እየጣሱ ይገኛሉ !!

ይህም አሳዛኝ ግፍና ጥቃት ከአካባቢው የሙስሊም ተወካዮችና ማህበረሰብ አቅም በላይ መሆኑም ተደጋግሞ ታይቷል !!

በመሆኑን ይህን መሰሉ የጉንችሬ ከተማ የሙስሊም ጠሎች አስነዋሪ ተግባርና ድርጊት በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የተቃጣና የተፈጸመ በደል መሆኑን የፌደራል መጅሊሡ ግንዛቤ ወስዶ እንደ አንድ ግዙፍ ማህበረሰብ ተወካይነቱ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን በደልና ግፍ ለሚመለከታቸው ተቋማት በማሳወቅና ብርቱ ክትትል በማድረግ ከዚህ በተጨማሪም በተቋሙ የህግ ክፍል አስቸኳይ የህግ ተጠየቅ እንቅስቃሴን በማስጀመር ህጋዊ መብትን የማስከበር እርምጃ ይወሰድ ዘንድና በየግዜው የተሄደበትን አቅጣጫና የተገኘውን ምላሽ በይፋዊ መግለጫ ያሳውቅ ዘንድ አጥብቀን እንጠይቃለን !!
___________________________

17/08/2023

አልሀምዱሊላህ!
በጠሮ መስጂድ ጉዳይ ታስረው የነበሩ አባቶች መፈታታቸው ተገለፀ።

ሃሩን ሚድያ ነሀሴ10/2015

በጠሮ መስጂድ በተከሰተው ችግር ምክንያት በሀሰት ታስረው
በሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ይገኙ የነበሩ ሁሉም አባቶች ከእስር ተፈተው አ.አ ገብተው ከቤተሰብ ጋር ተቀላቅለዋል።

ሃሩን ሚድያ በቅርቡ የጠሮ መስጂድ ጉዳይን አስመልክቶ የሚመለከታቸውን የአካባቢው ነዋሪዋች አናግሮ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል የአዲስ አበባ መጅሊስም የጠሮ መስጂድ የተፈጠረውን ያለመግባባት በቅርቡ እንደሚፈታ የአዲስ አበባ መጅሊስ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ሼህ ሁሴን በሽር ለሀሩን ሚድያ ገልፀዋል።

©ሃሩን ሚድያ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Great silte posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category