Ethio Nile River

Ethio Nile River የሀገራችን የዕድገት ምሰሶ ነው

21/04/2026
አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው “ሕገ-ወጥ” እገዳ የራሷን እና የዓለምን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚጎዳ ነው - ኢራን*********************************የአሜሪካው ፕሬዚዳንት...
13/04/2026

አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው “ሕገ-ወጥ” እገዳ የራሷን እና የዓለምን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚጎዳ ነው - ኢራን
*********************************

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ መርከቦችን በይፋ ማገድ መጀመሯን አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ‘ትሩዝ ሶሻል’ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢራን የባህር ኃይል ባለፈው ወር በተፈጸመበት ጥቃት መዳከሙን የገለጹ ሲሆን፤ ከጥቃቱ የተረፉ የኢራን መርከቦች አሜሪካ እገዳ ወደጣለችበት የውሃ አካል ከቀረቡ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስታውቀዋል።

ቴህራን በበኩሏ የአሜሪካ ድርጊት “ሕገ-ወጥ” ነው ስትል አውግዛለች። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋኢ፣ አሜሪካ ኢራንን ለመጉዳት እየፈጸመችው ባለው ድርጊት የራሷን እና የዓለምን ኢኮኖሚ እየጎዳች ነው ሲሉ ገልጸዋል። የአሜሪካ ድርጊት በተለይ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ቀውስ እንደሚያስከትልም አስጠንቅቀዋል።

በአሜሪካና በኢራን መካከል በኢስላማባድ የተደረገው የሰላም ድርድር ያለምንም ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የአሜሪካ ጦር ከሰኞ ጀምሮ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡና የሚወጡ ማናቸውንም መርከቦች እንቅስቃሴ ለማገድ መዘጋጀቱን አሳውቆ የነበር ሲሆን፤ የዚህ እርምጃ ዋና ዓላማ የኢራንን ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ሙሉ በሙሉ ለመገደብ እንደሆነ ተመላክቷል።

በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሀገራትም ሐሳባቸውን እየገለጹ ሲሆን፤ የዓለማችን ቀዳሚ የድፍድፍ ነዳጅ አስመጪ የሆነችው ቻይና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚደረግ ማንኛውም እገዳ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ጥቅም የሚጎዳ ነው ብላለች።

አያይዛም፣ እገዳው በራሷ የኢነርጂ ዋስትና ላይ ሊፈጥረው የሚችለው ጫና በእጅጉ እንዳሳሰባት ገልጻ፤ ሁሉም ወገኖች ትዕግሥትን እንዲላበሱ አሳስባለች።

የአውሮፓ ኅብረትም በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰበው ገልጿል።፤ የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካያ ካላስ፣ አሁን እየታየ ያለው ሁኔታ በቀጣናው “ጠንካራ ዓለም አቀፍ የባህር ላይ ደህንነት ጥምረት” አስፈላጊ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

ደቡብ ኮሪያ መርከቦቿ በሆርሙዝ ጥበቃ እንዲደረግላቸው የባህረ ሰላጤው ሀገራትን ጠየቀች*********************************በኢራን እየተካሄደ ያለው ጦርነት የባህር ላይ ትራንስ...
05/04/2026

ደቡብ ኮሪያ መርከቦቿ በሆርሙዝ ጥበቃ እንዲደረግላቸው የባህረ ሰላጤው ሀገራትን ጠየቀች
*********************************

በኢራን እየተካሄደ ያለው ጦርነት የባህር ላይ ትራንስፖርትን እያስተጓጎለ በመምጣቱ፣ የደቡብ ኮሪያ የፋይናንስ ሚኒስትር ኩ ዩን-ቼኦል በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገኙ መርከቦችን ደህንነት ለመጠበቅ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ላይ ሚኒስትር ኩ ለባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት (GCC) አምባሳደሮች እንደ ነዳጅ፣ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ፣ ናፍጣ እና ዩሪያ ማዳበሪያ ያሉ ወሳኝ ግብዓቶች የማያቋርጥ አቅርቦት እንዲኖር ጠይቀዋል።

በወሳኙ ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኮሪያ መርከቦችና ሠራተኞች ደህንነትም በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ መጠየቃቸውን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመልክቷል።

እንደ መግለጫው ከሆነ አምባሳደሮቹ ደቡብ ኮሪያ "ቀዳሚ ትኩረት" የሚሰጣት ሀገር መሆኑን በመግለጽ፣ የተረጋጋ የሃይል አቅርቦት እንዲኖር ከሴኡል ጋር በቅርብ ለመሥራት ቃል ገብተዋል።

ልክ እንደሌሎች የእስያ ኢኮኖሚዎች ሁሉ ደቡብ ኮሪያ በከፍተኛ ሁኔታ በሃይል ገቢ ምርቶች ላይ የምትደገፍ ሲሆን፣ ጦርነቱን ከመጀመሩ በፊት 20 በመቶው የዓለም ነዳጅ የሚጓጓዝበት የሆርሙዝ ወሽመጥ ዋነኛው የንግድ መስመር ነበር።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢራን የባሕር ላይ መተላለፊያውን በመዝጋቷ የሃይል ዋጋ እንዲንርና የዓለም ኢኮኖሚ ውድቀት ስጋት እንዲደቀን አድሯል።

በዚህ ወቅት ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኳታር፣ ኩዌት፣ ኦማን እና ባሕሬን የሚገኙበት የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያለው ትብብር ወሳኝ ሆኗል።

በመሀመድ ፊጣሞ

ከታሪካዊ ባለቤትነት እስከ ብሔራዊ ጥቅም ቀይ ባሕርና ደሴቶቹ******************ቀይ ባሕር በአፍሪካና በእስያ መካከል የሚገኝ ለዓለም ንግድና ለሥነ-ሕይወት ሚዛን ወሳኝ የሆነ ስልታዊ...
14/03/2026

ከታሪካዊ ባለቤትነት እስከ ብሔራዊ ጥቅም ቀይ ባሕርና ደሴቶቹ
******************

ቀይ ባሕር በአፍሪካና በእስያ መካከል የሚገኝ ለዓለም ንግድና ለሥነ-ሕይወት ሚዛን ወሳኝ የሆነ ስልታዊ የባሕር ወለል ነው።

ይህ ባሕር ከ1,000 በላይ ደሴቶች መገኛ ሲሆን፣ በተለይም ከ350 በላይ ደሴቶችን የያዘው የዳህላክ ደሴቶች ስብስብ የኢትዮጵያ የታሪክና የሉዓላዊነት አሻራ በጉልህ ያረፈበት ሥፍራ ነው።

የኢትዮጵያና የቀይ ባሕር ግንኙነት ከጥንታዊው አክሱም መንግሥት ንጉሥ ካሌብ ጀምሮ በመካከለኛው ዘመን እስከነበሩት እንደ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ያሉ ነገሥታት ድረስ የዘለቀ ጥልቅ የታሪክ መሠረት አለው።

በዘመናዊቷ ኢትዮጵያም ከ1950ዎቹ እስከ 1980ዎቹ ድረስ ሀገራችን የቀይ ባሕር ደሴቶች ባለቤት በመሆን በዳህላክ ከቢር ላይ ግዙፍ የባሕር ኃይል መሠረት ነበራት።

ኢትዮጵያ ከባሕር በር መራቋን ተከትሎም፣ የቀይ ባሕር የባለቤትነት መብት የትውልድ የቤት ሥራ እንደሚሆን የተረዱ ደራሲያንና አርቲስቶች በብዕራቸውና በዜማቸው ሲሞግቱ ቆይተዋል።

ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ “ዳህላክ ላይ ልሥራ ቤቴን...” በማለት የተጫወተው ዘመን ተሻጋሪ ዜማ፣ የብዙ ኢትዮጵያውያንን የልብ ቁጭትና ከባሕሩ ጋር ያላቸውን የነፍስ ትስስር የሚገልጽ ነው።

ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ደሴቶቹ በኢትዮጵያ ሥር ባይሆኑም፣ የኢትዮጵያ የታሪክና የሕግ የመብት ጥያቄ አሁንም በምሁራንና በፖለቲካ መድረኮች ላይ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሏል።

ይህ ከታሪካዊ ባለቤትነት እስከ ብሔራዊ ጥቅም የሚዘልቀው የቀይ ባሕር ጉዳይ፣ ዛሬም ድረስ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያልደበዘዘና ለትውልድ የሚሻገር የታሪክ አሻራ ነው።

ለዚህ ነው ይህ ትውልድ የህልውና ጉዳይ ነው ብሎ ኢትዮጵያን የባሕር በር ማግኘት እንዳለባት በማመን ጉዳዩን ብሔራዊ አጀንዳ በማድረግ እየሰራ ያለው።

በመሐመድ ፊጣሞ

28/02/2026

With Zinash Tayachew – I just made it onto their weekly engagement list by being one of their top engagers!

28/02/2026

I'm on the weekly engagement list for Zinash Tayachew and Getahun Wodalo.

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢራን ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሙሉ መብት እንዳላት አስታወቀች++++++++++++++++++++++++++++++ #የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢራን ጥቃት ምላሽ የመስ...
28/02/2026

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢራን ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሙሉ መብት እንዳላት አስታወቀች
++++++++++++++++++++++++++++++

#የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢራን ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሙሉ መብቷ የተጠበቀ መሆኑን አስታውቃለች።

የኢሚሬትስ የመከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ሀገሪቱ በኢራን ባላስቲክ ሚሳኤሎች ኢላማ እንደነበረች እና የአየር መከላከያዎች ጥቃቱን በተሳካ ሁኔታ እንደከሸፉ አረጋግጠዋል።

በአቡ ዳቢ በሚገኝ የመኖሪያ አካባቢ ላይ የደረሰው የፍንጣሪ ፍንዳታ የተወሰነ ቁሳዊ ጉዳት እና የአንድ የእስያ ዜጋ ሞት እንዳስከተለ በመግለጫው ተዘግቧል።

ሚኒስቴሩ ይህንን ጥቃት በጠንካራ መግለጫ ያወገዘ ሲሆን፣ የኢራን መንግሥት የሲቪል ንብረቶችንና ብሔራዊ ተቋማትን ኢላማ ማድረጉ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቋል።

እንደዚህ ያሉ ድርጊቶች የሲቪሎችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉና መረጋጋትን የሚያዳክሙ የፈሪ ተግባራት መሆናቸውን የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ መከላከያ በመግለጫው ጠቅሷል።

የኢራን ድርጊት የብሔራዊ ሉዓላዊነትን እና የዓለም አቀፍ ሕግን በግልጽ የሚጥስ በመሆኑ፤ ለዚህ ጥቃት ምላሽ ለመስጠትና ግዛቱን ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ የመውሰድ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን በመግለጫው አንስቷል።

የተባበሩ አረብ ኤሚሬትስ ማንኛውንም ስጋት ለመቋቋም ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኗንም ገልጿል። ዘገባው የአልጄዚራ ነው።

በክብረአብ በላቸው

+++++++++++++++++++++
#ዓለምአቀፍ #እስራኤል #ኢራን #አሜሪካ #መካከለኛውምስራቅ

15/02/2026

በሁለተኛው ቀን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን፤ ከጋና ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል።

Met with President John Mahama of Ghana today on the second day of the AU Summit to discuss strengthening bilateral relations.

🇪🇹 ብዝኃነታችንን እና ኅብረ-ብሔራዊነታችንን አክብሮ በኢትዮጵያዊ የጋራ ማንነታችን አንድ የሚያደርጉ የወል ትርክቶችን ማጎልበት የጋራ ኃላፊነታችን ነው።በዚህም ላይ፡- 🕊 ግንዛቤ መያዝ 🕊 ሰ...
02/02/2026

🇪🇹 ብዝኃነታችንን እና ኅብረ-ብሔራዊነታችንን አክብሮ በኢትዮጵያዊ የጋራ ማንነታችን አንድ የሚያደርጉ የወል ትርክቶችን ማጎልበት የጋራ ኃላፊነታችን ነው።

በዚህም ላይ፡-
🕊 ግንዛቤ መያዝ
🕊 ሰላምን ማፅናት
🕊 የወል ትርክቶችን ማስረፅ
🕊 ሰላምን በማይናጋ መሠረት መገንባት እና
🕊 ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ተግባራትን በተቀናጀ መንገድ ማከናወን ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል።

✅ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን የሚያጎድሉ ማንኛቸውንም ነገሮች በቁርጠኝነት መመከት ለነገ የማይባል የጋራ ጉዳይ መሆኑን በውል መረዳት ተገቢ ነው።

✅ የሀገራችንን ሰላም፣ ልማት እና ዕድገትን የማይፈልጉ ኃይሎች በሚነዙት ነጠላ እና ነጣጣይ ትርክቶች መጠመድ የለብንም፡፡

✅ ሀገራዊ ማንነታችንን ታሳቢ ያደረገ ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅ እና ማሳካት ከዚህ ትውልድ የሚጠበቅ ታላቅ ሀገራዊ አጀንዳ ነው፡፡

✅ ተግዳሮቶችን ተሻግራ፣ ከድህነትም ተላቃ የበለፀገች ሀገር ለትውልድ ለማስተላለፍ በፅናት፣ በአብሮነት እንዲሁም በአንድነት መቆም ከሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ጥብቅ ጉዳይ ነው።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

በ962 ነፃ የጥሪ መስመር በመደወል እና የግጭት
አመላካች መረጃዎችን ቀድሞ በመስጠት
የሀገራችንን ሰላም በጋራ እንጠብቅ

ታላቁ ከበባ፥ የኢትዮጵያ የባሕር መብት እና የግብፅ ያረጀ ስልት ************************የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በውስብስብ ጂኦፖለቲካዊ የለውጥ ሂደት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት...
31/12/2025

ታላቁ ከበባ፥ የኢትዮጵያ የባሕር መብት እና የግብፅ ያረጀ ስልት
************************

የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በውስብስብ ጂኦፖለቲካዊ የለውጥ ሂደት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፤ ግብፅ በሼልፍ ላይ የቆየ ያረጀ፣ ያፈጀ ስልቷን አቧራውን በማራገፍ እንደገና ይዛው መጥታለች።

ሀገሪቱ በቅርቡ ከሶማሊያ እና ከኤርትራ ጋር ፈጸምኩት ያለችው ወታደራዊ ስምምነት፤ በቀጣናው ውጥረትን አንግሷል።

በ“ሉዓላዊነት” እና በ“ቀጣናዊ መረጋጋት” ሽፋን የተፈጸመመውን ስምምነት ከታሪካዊ መዛግብት አንፃር ለመረመረው ከጀርባው ያለው ድብቅ ሴራ ፍንትው ብሎ ይታየዋል።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ ላይ የተዘጋውን የባሕር በር እስከወዲያኛው በመከርቸም ሀገራችንን ከማዳከም የዘለለ ዓላማ የለውም።

የባሕር በር የተዘጋበት ትልቅ ሕዝብ እና ሀገር

በዓለማችን የባሕር በር ከሌላቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ በሕዝብ ቁጥር ትልቋ መሆኗ ይታወቃል።

እናም የባሕር በር ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያ በመልክዓ ምድር መገለልም እንዲሁ “የታሪክ አጋጣሚ” ተብሎ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም።

ይልቁንም ከስምንት አስርት ዓመታት በፊት በዋናነት በግብፅ አቀነባባሪነት ሆነ ተብሎ የተጋረጠባት ስልታዊ መሰናክል ነው።

ግብፅ ይህን ያደረገችው በናይል ተፋሰስ እንዲኖራት ትመኘው ለነበረው የበላይነት “ባለባሕር በሯ ኢትዮጵያ” ስጋት መስላ ስለታየቻት ነበር።

የግብፅ የአሻጥር ሌጋሲ

ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ አሻጥር መፈጸሟ በተደጋጋሚ ያጋጠመ እና የተለመደ ነው።

ለአብነትም እአአ በ1950ዎቹ ኢትዮጵያ የባሕር በሯን መልሳ በምታገኝበት ሁኔታ ላይ በተመድ ጉባዔ በተደረገበት ወቅት ሀሳቡን ተቃውማ ቆማለች።

በተመሳሳይ፥ በ1960ዎቹ ኢትዮጵያን ለመገንጠል ይዋጉ ለነበሩ ባንዳዎች ምሽግ ሆና ከማገልገል በተጨማሪ እና የበጀት ምንጫቸው ነበረች።

በ1977ቱ የኢትዮ - ሶማሊያ ጦርነት ወቅት ደግሞ የግብፅ ስልታዊ ከበባ ይበልጥ ይፋ ሆነ። በወቅቱ ግብፅ ለሶማሊያ ወራሪ ኃይል በርካታ የጦር መሳሪያ አስታጥቃለች።

ምኞቷም ኢትዮጵያ ስትከፋፈል እንዲሁም ከተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ የባሕር ወሰኗ ስትነጠል ማየት ነበር።

እንሆ ዛሬም ቴአትሩ ቢቀየርም፣ ተዋናዮቹ እና ዓላማቸው ግን አንድ ነው፤ በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉት የከባበ ፖሊሲም ከስምንት አስርት ዓመታት በኋላ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

የባሕር በር ጥያቄ የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ ነው ታህሳስ 21/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚ...
30/12/2025

የባሕር በር ጥያቄ የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ ነው

ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ፣ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

ከምክር ቤት አባላቱ ለሚኒስትሩ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል፤ ኢትዮጵያ በታሪካዊ ስህተትና ግፍ የተነፈገችውን የባሕር በር ለማስመለስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን እየሠራ እንደሆነና ከዜጎች ምን ይጠበቃል የሚሉት በዋናነት ተነስተዋል።

ሚኒስትሩ ለቀረበው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ የባሕር በር ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚያስከብር መልኩ በስፋት እየተሠራበት መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁንም የኢትዮጵያ ጥያቄ እና የፍላጎቷ ምንነት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በግልጽ ማስረዳት መቻሉን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያን ፍላጎት የማስገንዘቡ ሥራ ውጤት ማስገኘቱን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ አሁን ላይ ጥያቄው እንዴት ይመለስ? ወደሚለው ተግባራዊ ምዕራፍ መሸጋገሩን አብራርተዋል።

የባሕር በር የአንድ ፓርቲ፣ የወገን ወይም የግለሰብ ጥያቄ ሳይሆን የሀገርን ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥና የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ በመሆኑ፤ ጥያቄው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ሁሉም ዜጋ ያለልዩነት በአንድነት ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይም የኢትዮጵያን መዳከምና መኮስመን ለሚመኙና ለዚህም ሌት ተቀን ለሚሠሩ አካላት መጠቀሚያ ላለመሆን ሁሉም ዜጋ በተጠንቀቅ ሊቆም እንደሚገባ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Morocco 🇲🇦 is  the only African country with coastlines on both the Atlantic Ocean and the Mediterranean Sea. Morocco ha...
22/11/2025

Morocco 🇲🇦 is the only African country with coastlines on both the Atlantic Ocean and the Mediterranean Sea.

Morocco has one of the longest coastlines on the mainland, with a length of approximately 1,835 km.

Did you know that from Morocco to Spain is about 15h 36m (1,310 km) (By land)

Credit: Great Africa

Address

Cairo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Nile River posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category